27/08/2026
በ 2019 ዓ.ም ከቃርሚያ ኑሮ ወደ ነዶ የምትገቡበት አመት ይሁንላች!ወገኖች የቃርሚያ ኑሮ ማለት የባዶነት የድህነት የብቸኝነት የስደት የበታችነት ሕይውት ምልክት ነው:: ለዚህም ማስረጃ ከፈለጋችሁ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል::
ኦሪት ዘሌዋውያን 19
10፤ የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሆችና ለእንግዶች ተወው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ኦሪት ዘዳግም 24
21፤ የወይንህን ፍሬ በቈረጥህ ጊዜ ቃርሚያውን አትልቀመው፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን።