19/02/2026
እሁድ የካቲት 8/2018 ዓ.ም ምሥራቅ የአምላክ ክብር መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የአምልኮ ፕሮግራም።
በፀሎት እንዲሁም በማስተባበር እህት ሀና ግርማ በአምልኮ ወ/ም በፀጋው ጋር እግዚአብሔርን አምልከናል ቃለ እግዚአብሔር በእህት ገነት ተካፍለናል።
ርዕስ:- የሚያመሰግን አይዘገይም!
የመፅሐፍ ክፍል -ዘፍ 24፥ ከቁ1 ጀምሮ
አብርሐም ለልጁ ለይስሐቅ የምትሆን ሚስት ያመጣለት ዘንድ በቤቱ ሁሉ ላይ አስተዳዳሪ የነበረውን ሎሌውን ላከው።
በአብርሐም ሕይወት እግዚአብሔር ምንም እንኳ የዘገየ ቢመስልም: እግዚአብሔር በራሱ ዘመን ይሰራል።
የአብርሃም ሎሌ የእግዚአብሔርን ምሪት ጠየቀ።
1. እግዚአብሔርን ምሪት መጠየቅ!
✨ ሎሌውም
- ተንበርክኮ ፀለየ
- የአብርሃም አምላክ አለ! (የአብርሃምን አምላክ ያውቀው ነበር)
▪️የያዕቆብ ሚስት ራሄል ምንም እንኳን ከያዕቆብ ጋር ብዙ አመት ያሳለፈች ብትሆንም ከአባቷ ቤት ሲወጡ አማልክትን ደብቃ ይዛ ነበር።
▪️እግዚአብሄርን የሚያሳይ ህይወት ጌታ ይሰጠን! ሎሌው የአብርሀምን አምላክ ኤሎሂምን እንዳወቀው ማለት ነው።
2. ለምነን ከተቀበልን በኋላ እግዚአብሔርን ማመስገን ይኖርብናል።
- እንደለመነ ወዲያው ሴቲቱን አገኘ (እግዚአብሔር ወዲያውኑ ይስማን)
- ከዚያም ተንበርክኮ ሰገደ (አመሰገነ)
- ወላጆችዋሞ ከፈቀዱ በኋላም አመሰገነ።
▪️አስሩ ለምፃሞች ከተፈወሱ በኃላ ለምስጋና የተመለሰው አንዱ ብቻ ነበረ: ለምስጋና የተመለሰውን እንሁን!
3. እግዚአብሔር ካቀናው መንገድ የሚያዛገየውን እምቢ ማለት።
- ወላጆችዋ ማታ ፈቅደው ጥዋት 10 ቀን ትቆይ አሉት: እሱን ግን አታዘግዩኝ አላቸው ።
▪️ጳውሎስ ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልጌ ነበር ሰይጣን ግን አዘገየኝ አለ: ዳንኤልም 21 ቀን ፀሎቱ እንደዘገየ መልአኩ አሳውቆት ነበረ።
▪️ፀሎታችንን: ነገራችንን: ሥራችንን የሚያዘገይ ይመታል! ያዘገያችሁን እግዚአብሔር ይመታዋል! ትግል ያበቃል!
8/06/2018 ዓ.ም
📍 ምሥራቅ የአምላክ ክብር መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ
Telegram:- https://t.me/misrak_mkc_adama
Facebook:- https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
Instagram:- http://Instagram.com/misrak_mkc
TikTok:- https://vm.tiktok.com/ZMA5wBynN/