05/11/2024
የእውነት ለመኖር....
#ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ስማ
#ለሰው ከመኖር ለእግዚአብሔር ኑር
#መፅሐፍ ቅዱስን በመንፈስ ቅዱስ አብሮነት በማጥናት ከአብላጫ ድምፅ ተፅዕኖ (majority influence) ራስህ አላቅቅ
#የሰው ጭብጨባ ሳትጠብቅ ያመንክበትን ኑረው
#ከእውነተኞች ምክርን፣ ልምድን፣ ትምህርትን፣ ፀጋንና ፀሎትን ተካፈል
#ከትህትና ጎዳና አለመውጣትህንና በትዕቢት ወይም በበታችነት ሰንሰለት አለመያዝህን ሁልጊዜ ፈትሽ
#በልክህ የተስፋ ኑሮና ልምምድ ይኑርህ
#ከዝሙትና ከሌሎች የኃጥያት ልምምዶች ፈፅመህ ራቅ
#በገንዘብ ፍቅር እንዳትያዝ ዕለት ዕለት ነፍስህን በቃሉና በመንፈሱ አፅዳ!!
#"የጌታ ቀን" የሚባል መኖሩንና ዕወቅ፤ በዚህ ቀንም በኢየሱስ ክርስቶስ እና በአባቱ ፊት እንዳታፍር በምድር ቆይታህ ፍሬ ያለው ህይወት ይኑርህ
#መንፈስ ቅዱስን በየዕለቱ ተሞላ!!