ዘ - ኢ ትዮጵያ

ዘ - ኢ ትዮጵያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዘ - ኢ ትዮጵያ, Religious organisation, Addis Ababa.

27/08/2026
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! መስከረም ፲መስከረም ፲፩መስከረም ፲፪   የምሥጋና ቀን ነው✍🏼 ዮም ወርኀ መስከረም ፲/፯/፳፻፳፬/ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሔኖክ : የመስቀለ እ...
27/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!

መስከረም ፲
መስከረም ፲፩
መስከረም ፲፪
የምሥጋና ቀን ነው

✍🏼 ዮም ወርኀ መስከረም ፲/፯/፳፻፳፬/ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሔኖክ : የመስቀለ እግዚእ ወርኀዊ ክብረ በዓል ዕለት ... ይሄውም ለሦስት ቀን የሚከበረው ፡ ሰማይ እና ምድርን የፈጠረ አምላከ የሚመሰገንበት: ወላዲተ አምላክ የምትወደስበት: ቅዱሳን መላእክት : ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ነቢያት ሐዋርያት ሁሉንም በየማዕረጉ: እንደየ ክብር ቅደም ተከተሉ!
ምስጋና የሚቀርብበት ቀን
ዛሬ "ቀዳማይ " የምስጋና ቀን ነው።

የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን እንኳን አደረሰን ።

“እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ÷
ለአሕዛብ ሥራውን ንገሩ፤
ተቀኙለት፣ ዘምሩለት፣ ተአምራቱንም፣ ሁሉ ተናገሩ፤
በቅዱስ ስሙም ትከብራለችሁ።
እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው ፤
እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችላችሁም፤
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
መዝ [፻፬፥፩~፬]

✍🏼 እንዲሁም የጸደንያ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው ።
የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን እንኳን አደረሰን

ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን የፈወሰ'ች'በት ፣ በስዕለ ማርያም ታላቅ ተዓምር የታየበት ፣ እውራን የበሩበት: ድውያን የተፈወሱበት ፣ ነውና,,,,, ከቅዱሳን ልብስ፣ ጥላ ይልቅ የእርሷ የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከወላዲተ አምላክ ከ ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ ጸደንያ ማርያምን በታላቅ ድምቀት በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡

ዛሬ በምድር ኢትዮጵያ በማኅበራዊ ድኅረ ገጽ ያቃጠሏት,,, ሥዕለ ማርያም,,, መልስ ትሰጥ ዘንድ ኀይሏን ትገልጥ ዘንድ እያሳሰብን የሰማይ አምላክን እየጠየቅን,,,,

የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም እናትነት ፤ ፍቅር ፣ የል'ጇ' የመድኅነ ዓለም ምሕረት በረከት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል !
ወለመስቀሉ ክቡር!

ይምሐረነ ወይሠሃለነ በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ያጽንዓነ
ለይኩን! ለይኩን ! ለይኩን።

26/08/2026

ወደ ዘ-ኢ ትዮጵያ፪ ትዕይንተ መስኮት እንኳን በደህና መጣ'ች'ሁ!!! ይህ ትዕይንተ መስኮት የሰማይ መልእክ...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! ዮም ወርኀ መስከረም ፯ /፯/፳፻፳፬ // ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሔኖክ የወላዲተ አምላክ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ነው። የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖ...
24/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! ዮም ወርኀ መስከረም ፯ /፯/፳፻፳፬ // ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሔኖክ የወላዲተ አምላክ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ነው።

የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን እንኳን አደረሰን። ንጉሥ ዳዊት በትንቢቱ ስለ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ እንዲህ ብሎ ነበር ... [መዝ ፹፮(86) ቁጥር (1-7)፩ - ፯] «መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን" "መሠረቷ በተቀደሱ ተራሮች ነው » ሲል .. ቅድስት ድንግል ማርያም በአባቷ ከንጉሡ ዳዊት ወገን ስትሆን ... በእናቷ በኩል ደግሞ ከካህኑ አሮን በኩል ከተቀደሱት ከቅዱስ ኢያቄም እና ከቅድስት ሐና የመሆኗን ነገር ሲያመለክት ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢት ምዕራፍ ፲፩(11) ከቁጥር ፩(1) «ከእሴይ ስር በትር ትወጽዕ፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል »ሲል በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ከነገደ እሴይ ...እርሷም አበባ የተባለ መድኅንን በድንግልና እንደምትወልድ ተገልፆለት ነው። ይህንንም መሠረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም «መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ተፈሥሒ ፣ የእሴይ ስር የዘር ሐረግ ጥዑም መዓዛ ፣ ያማረ አበባ አንቲ ውእቱ» በማለት በውዳሴው «የምንመካባት ዘውድ የንጽሕናም መሠረት » ብሎ ያወደሳት ፣ ያመሰገናት ወላዲተ አምላክን ቅድስት ድንግል ማርያምን ነው። ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ «ፀሐይን ተጎናፅፋ ከእግሯ ስር ወርኅ ያላት አሥራ ሁለት የከዋክብት አክሊል በራሷ ላይ የሆነላት " ...ብሎ የመሰከረላት! የብርሃን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክን ነው። የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን!..."ወላዲተ አምላክ " ከፊት መርታ ፣ ጥላ ከለላ ፣ አምባ መጠጊያ ሆና...በመድኅን መስቀል አጥራ! በመቀነቷ አስራ ትያዘን ፤ በእምነት አጽንታን እስከ ፍጻሜው ትጠብቀን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ! ይምሐረነ ወይሠሃለነ በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ያጽንዓነ! ለይኩን ለይኩን ለይኩን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! ✍🏼ዮም መስከረም ፭/፯/ ፳፻፳፬ ዘመነ ሔኖክ: የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው ። የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን እንኳን አደ...
22/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!

✍🏼ዮም መስከረም ፭/፯/ ፳፻፳፬ ዘመነ ሔኖክ: የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው ።

የርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን እንኳን አደረሰን።

«የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ
በገናናውና በቅዱሱ በጌትነቱ ፊት ከሚያቀርቡ ከሰባቱ ቅዱሳን መላእክት አንዱ መልአክ
እኔ ሩፋኤል ነኝ»
[መጽሐፈ ጦቢት .፲፪ ፥ ፲፭]

እግዚአብሔር አምላክም ከባህሪው ቅድስና ፣ ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦና አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ጸጋ ከሰጠው ቅዱሳን መላእክት መካከል “ቅዱስ ሩፋኤል ” ሲሆን ..ሲመቱም :-
~የፍጥረታትን ማኅጸን የሚፈታ [ፈታሄ ማኅጸን]
~በሌሊት የሚጠብቀን፤
~በመንገድ የሚመራን፤
~ዓይነ ስውራንን የሚያበራ፤
~አጋንንትን የሚያባርር፤
~ድውያንን የሚፈውስ ፤
~አቃቤ ኆኅት => [ዐውደ ምሕረትን የሚጠብቅ]
~የቅዱሳንን ጸሎት የሚያሳርግ
መልአክ ነው ።

በድጋሚ እንኳን አደረሰን!

የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከት ተራዳይነት አይለዬን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!

ይምሐረነ ወይሠሃለነ በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ያጽንዓነ!
ለይኩን! ለይኩን ለይኩን! ።

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 02:00 - 16:00
Wednesday 08:00 - 16:00
Thursday 08:00 - 16:00
Friday 08:00 - 16:00
Saturday 08:00 - 16:00
Sunday 08:00 - 16:00

Telephone

+251925761959

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዘ - ኢ ትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ዘ - ኢ ትዮጵያ:

Shortcuts

Share