WudaseTube - ውዳሴ

WudaseTube - ውዳሴ ውዳሴTube-የኢትዮጵያና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤክ ትምህርተ ወንጌልንና ስብከተ ወንጌልን፣ያሬዳዊ መዝሙራትና መንፈሳዊ ፊልሞች ለምዕመናን ያቀርባል!
(484)

ውዳሴ ቲዩብ-የኢትዮጵያና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን፣ ስብከተ ወንጌልን፣ ያሬዳዊ መዝሙራትና እንዲሁም መንፈሳዊ ፊልሞችን: ቅዳሴ፣ተሰጥኦ፣ ጉባኤዎች፣ የገዳማትና አድባራት ታሪኮችን፣ ንግሶች፣ ክብረ-በዓላት እና ወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ዜናዎች ለምዕመናን በየግዜው የሚያቀርብ ድረ-ገጽ ነው! WudaseTube.com is an Ethiopian and Eritrean Orthodox Tewahdo Church's Mezmur (Hymn), Gospel, Orthodox Teachings and Preaching Video Audio Sharing Website.

መልክአ ሕማማት
13/04/2020

መልክአ ሕማማት

ሰበር ዜና!ቅዱስ ሲኖዶሱ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት በተወሰኑ ካህናት ብቻ እንዲሰጥ ወሰነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ስርአተ ቅዳሴን ጨምሮ መንፈሳዊ ...
01/04/2020

ሰበር ዜና!

ቅዱስ ሲኖዶሱ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት በተወሰኑ ካህናት ብቻ እንዲሰጥ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ስርአተ ቅዳሴን ጨምሮ መንፈሳዊ አገልግሎት ከነገ ጀምሮ በተወሰኑ ካህናት እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ።

ሲኖዶሱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አገልግሎቱን ከሚሰጡት የተወሰኑ ካህናት ውጭ ሌሎች አገልጋዮች እና ምዕመናን በቤታቸው እንዲቆዩ መወሰኑን አስታውቋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አሁን የያዝነውን የጾምና የጸሎት ጊዜ ምክንያት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራትና በመባረክ መቆየታቸውን ቋሚ ሲኖዶስ ተገንዝቧል፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያለው ወረርሽኝ በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑና የተለየ አባታዊ ጸሎትና ሱባኤ የሚያስፈልግ ሆኖ በመገኘቱ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ከዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለዓለም ሰላምና ለሕዝቦች ደህንነት ሲባል ለጊዜው ለብቻቸው በልዩ የጾምና የጸሎት የሱባኤ ጊዜ እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጓን ገልፃለች።

በመግለጫው ህብረተሰቡ በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦችን እና መመሪያዎችን በአግባቡ እንዲተገብርም ጥሪ ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜንበመላው ዓለም የተስፋፋውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታትከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫበሀገራችን ኢትዮጵያ ...
24/03/2020

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን

በመላው ዓለም የተስፋፋውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታት
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር፣ በከተማና በመላው ዓለም ለምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ!

ወቅታዊ የሰው ልጅ ሥጋት በመሆን በመላው ዓለም በፍጥነት በተስፋፋው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ሥጋት ስለተከሰተ መንግሥታት ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከሞት ለመጠበቅ አዋጆችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ እምነትና ቀኖናን ጠብቆ ሃይማኖታዊ መመሪያ የመስጠት ሐዋርያዊ ኃላፊነት አለባት፡፡

ስለዚህ ቋሚ ሲኖዶስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መሠረተ እምነትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ለሁሉም ካህናትና ለሕዝበ እግዚአብሔር ደኅንነት ሲባል የሚከተሉትን መመሪያዎች አስተላልፏል፡-

1. በሰሙነ ሕማማት እንደምናደርገው የእርስ በርስ መሳሳም ቀርቶ ራስን ዝቅ በማድረግ፣ እጅ በመንሳት ወይም በእማሄ ሰላምታ በማቅረብ እንዲፈጸም፣

2. ወረርሽኙ በሰዎች መሰባሰብ የሚስፋፋ ስለሆነ ማናቸውም መንፈሳዊ ጉባኤያት፣ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት፣ ወደ ገዳማትና አድባራት የሚደረጉ ጉዞዎች እና ምዕመናን የሚሳተፉባቸው ታላላቅ መርሐ ግብሮች ለጊዜው እንዲቋረጡ፣

3. ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባም ሆነ አሰፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ እጆቻንን በመታጠብና ዘርዘር ብሎ በመቆም ሥርዓተ አምልኮ እንዲፈጸም፣

4. ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓላት በቅዳሴና በማኅሌት ታስበው ክብረ በዓላቱ በሌላ ጊዜ እንዲከበሩ፣

5. የጉንፋን ምልክት ያለባቸው ለሌሎች እንዳያስተላልፉ በቤታቸው በጥንቃቄ ተለይተው በጸሎትና በሕክምና እንዲቆዩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋቸውን መንፈሳዊ አገልግሎትም በልዩ ሁኔታ እንዲያገኙ፣

6. በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የተስፋ ልዑክ በመሆን እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ተደራጅቶ ተልዕኮውን በአስቸኳይ እንዲጀምር

7. ሥርዓተ ቅዳሴን በተመለከተ፡-

• በቤተ መቅደስ ቀዳስያን በሆኑት ልዑካን ብቻ ሥርዓተ ቅዳሴው እንዲፈጸምና ሌሎች አገልጋዮች በቅድስቱ ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያገለግሉ፣

• በዕለቱ ለሚቆርቡ ምዕመናን ለአረጋውያን፣ ለወጣቶችና ለሕፃናት የፈረቃ ተራ በማዘጋጀት ቆራቢዎች ብቻ ወደ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያስቀድሱ፣

• ሌሎች ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ቢያንስ ሁለት የትልቅ ሰው እርምጃ ያህል በመራራቅ ቆመው እንዲያስቀድሱ፣

• የቅዳሴ ጠበል በየግል መጠቀሚያ ምእመናን በየቆሙበት ቦታ በጥንቃቄ እንዲሰጥ፣

• ሌሎች ከቅዳሴ ጋር የተያያዙ ዝርዝር የአፈፃፀም ጉዳዮችን ግብረ ኃይሉ አዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ በማጸደቅ ለአህጉረ ስብከት በሚልከው መመሪያ መሠረት ተግባራዊ እንዲደረግ፤

8. ከሥርዓተ ቅዳሴ በተጨማሪ እንደ ስብሐተ ነግሕ፣ ሰዓታት፣ ቁመተ ማኅሌት፣ ጥምቀተ ክርስትና፣ ጸሎተ ፍትሐት፣ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለሥርዓቱ በሚያስፈልገው ቁጥር ብቻ እና በውሱን ሊቃውንት በተራ እንዲፈፀም፣

9. ወረርሽኙ ከዓለም እንዲጠፋ ካህናት ብቻ በቤተ መቅደስ፣ በዐውደ ምኅረትና በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ጸሎተ እጣን በማድረስ ማዕጠንት እንዲፈጽሙ፣

10. በማኅበራዊ ግንኙነት በደስታ፣ በሐዘን፣ በእድር፣ በሥርዓተ ቀብር አፈፃፀምና በመሳሰሉት መሰባሰቦች በሽታው እንዳይሠራጭ አገልግሎቱ በውስን የሰው ቁጥር በጥንቃቄ እንዲፈፀም፤

11. ምዕመናን ራሳቸውን እየጠበቁ በቫይረሱ የተጠቁና አገግመው የወጡ ወገኖችን፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ከሃይማኖትና ከምግባር የወጣ መገለልና ጥቃት እንዳይደርስባቸው በክርስቲያናዊ ፍቅርና በኢትጵያዊ ጨዋነት እንክብካቤ እንዲደረግላቸው፣

12. ለነዳያን እና ለተቸገሩ ወገኖች አስፈላጊው ማኅበራዊ እና ቁሳዊ እገዛ በሁሉም አጥቢያዎች እንዲደረግ፣

13. ቤተ ክርስቲያንን ከማይወክሉና ቀኖናዊ ካልሆኑ አሳሳች መረጃዎች በመቆጠብ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጡ መመሪያዎችን በየአጥቢያችሁና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንድትፈጽሙ እና እንድታስፈጽሙ ተወስኗል፡፡

በአጠቃላይ በበሽታው እስካሁን ለተያዙት፣ በጊዜያዊ ማቆያ ለሚገኙት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን ምህረቱን እንዲሰጥልን እንጸልያለን፤

በመላው ዓለም ዜጎቻቸውን በበሽታው ለተነጠቁ ሁሉ መጽናናቱን እንዲሰጥልን ያረፉትንም እንዲምርልን እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቃለን፤

በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን የራሳችሁና የሌሎች ሕይወት ከወረርሽኙ እንዲጠበቅ እንዲሁም የበሽታው ሥርጭት እንዲቆም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን የተሰጡት መመሪያዎች ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ የጸኑ እንዲሆኑ በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ዓለማችንን ከጥፋት የሰውን ልጅ ሁሉ ከመከራ ሞት ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ/ም
አዲስ አበባ

22/03/2020

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እና መስፋፋትን ለመግታት ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ ማብራሪያ።

በመላው ዓለም ለምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ!

የወቅቱ የዓለማችን ሥጋት በመሆን በፍጥነት እየተስፋፋ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት በርካታ ሀገሮች ብሔራዊ ሥጋት ስላደረባቸው እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ናቸው፡፡

በሽታውን እንዳይዛመት ከመከላከል ውጭ የሚፈውስ መድኀኒት ስለሌለው፣ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ስለሚዛመት፣ ጾታና የዕድሜ ክልል ሳይለይ ይልቁን አረጋውያንን ስለሚያጠቃ፣ ሁሉም ሀገሮች የመተላለፊያ መንገዶች በመለየት ሥርጭቱን ለመግታት ዝርዝር መግለጫ በማውጣት ሕዝባቸው ከሞት፣ ሀገራቸውን ከጥፋት ለመከላከል እየጣሩ ይገኛሉ፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጸሎትና ምሕላ አጠናክሮ ከማድረግ በተጨማሪ ጤነኞችን የመጠበቅ፣ ሕሙማን የመንከባከብና የማጽናናት ኃላፊነት ስላለባት ቋሚ ሲኖዶስ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡-

1. ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በየደረጃው የሚዋቀር ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከጤና ባለሙያዎች የተውጣጣ ግብር ኃይል ተቋቁሟል፤
2. ግብረ ኃይሉ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰናዳት በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰነ ተግባራዊ እንዲያደርግ፣
3. ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና ጋር የማይጋጩ የመከላከያ መንገዶች ማለትም የእጅ ለእጅ መጨባበጥን ማቆም፣ እጅን በሚገባ መታጠብ፣ ሳይጠጋጉ ዘርዘር ብሎ መቆም፣ በመሳልና በማስነጠስ ጊዜ መጠንቀቅ፣ በመሳሳም ምትክ እማሄ ወይም ሰላምታ መስጠት በየአጥቢያው፣ በየገዳማቱና በያለንበት ሁሉ ተግባራዊ እንዲደረጉ፤
4. መንፈሣዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት፣ የመንፈሳዊ ጉዞ መርሐ ግብሮች ለጥቂት ቀናት እንዲቆሙ፣ በቅዳሴና በምሕላ ጸሎት ጊዜ በውስጥም ሆነ በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዘርዘር ብሎ በመቆም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲፈጸሙ፣
5. ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ ከተሳሳቱ መረጃዎች ተቆጥባችሁ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ መመሪያዎችን በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንድታስፈጽሙ፣
6. ለራሳችንና ለወገኖቻችን በመቆርቆርና በመተዛዘን፣ አረጋውያንን በመጠበቅ፣ ነዳያን በማሰብ የበሽታውን ሥርጭት ተባብረን እንድናስቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ይኽንን አስከፊ በሽታ ከዓለማችን እንዲያጠፋልን በማያልቅ ቸርነቱና በቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም አማላጅነት በምኅረቱና በይቅርታው ብዛት ይማረን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በአዲስ አበባ በፖሊስ የተገደሉት ሁለት ወጣት ክርስቲያኖች የቀብር ስነ ሥርዓት ተከናወነ፡፡
06/02/2020

በአዲስ አበባ በፖሊስ የተገደሉት ሁለት ወጣት ክርስቲያኖች የቀብር ስነ ሥርዓት ተከናወነ፡፡

Ethiopia: Funeral ceremony of the two Ethiopian youth victims of the police and christians clash in...

የተዋህዶ መዝሙሮች በሞባይልዎ ያዳምጡ!ውዳሴ መዝሙር አፕ
04/02/2020

የተዋህዶ መዝሙሮች በሞባይልዎ ያዳምጡ!
ውዳሴ መዝሙር አፕ

ማፍያው ፓስተር ===ሰዎች ሆይ ከማፍያ እና አታላይ ፓስተሮች ራሳችሁን ጠብቁ! እነሆ ገልባጭ መኪናቸውን በፓስተሩ የተቀሙት እና ከፍተኛ ማጭበርበር የደረሰባቸው ተበዳዮች ሮሮ ያዳምጡ!
18/12/2019

ማፍያው ፓስተር
===
ሰዎች ሆይ ከማፍያ እና አታላይ ፓስተሮች ራሳችሁን ጠብቁ! እነሆ ገልባጭ መኪናቸውን በፓስተሩ የተቀሙት እና ከፍተኛ ማጭበርበር የደረሰባቸው ተበዳዮች ሮሮ ያዳምጡ!

Take care of Ethiopian pastors - they are scammers...

የመናፍቃን(ፕሮቴስታንት) ፓስተሮች እና ነቢያት የስርቆት እና የማጭበርበርያ ዘዴ ጌታ ነግሮኛል በሚል የ3 ሚሊየን ብር ቤቷን በ370 ሺህ ብር እንድትሸጥ አልያ ልጅሽ ትሞታለች በሚል የተጭበረ...
14/12/2019

የመናፍቃን(ፕሮቴስታንት) ፓስተሮች እና ነቢያት የስርቆት እና የማጭበርበርያ ዘዴ

ጌታ ነግሮኛል በሚል የ3 ሚሊየን ብር ቤቷን በ370 ሺህ ብር እንድትሸጥ አልያ ልጅሽ ትሞታለች በሚል የተጭበረበረችው አሳዛኝ ወጣት ታሪክ በቤቴል ወንጌላዊት ቤ/ክ ፕረዚደንት በሆኑት በቄስ ግርማ ዘውዴ ይነገራል ይመልከቱት!

Breaking news - Testimony about the falsehood of Ethiopian protestant pastors (prophets)...

PART TWOየጣልያን ሙያተኞች ታሪካዊው የማርያም ደንገላት ገዳም አስደናቂ በሆነ ሁኔታ እንዴት መወጣጫ እንደሰሩለት እና አሁን ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል እነሆ ይመልከቱ!
03/12/2019

PART TWO
የጣልያን ሙያተኞች ታሪካዊው የማርያም ደንገላት ገዳም አስደናቂ በሆነ ሁኔታ እንዴት መወጣጫ እንደሰሩለት እና አሁን ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል እነሆ ይመልከቱ!

How the Italian Engineers make the Ethiopian monastery, Mariam Dengelat Accessible by rope up a sheer cliff.

The Eve of Axum Hidar Tsion -  የሕዳር ጽዮን ዋዜማ በዓል!
01/12/2019

The Eve of Axum Hidar Tsion - የሕዳር ጽዮን ዋዜማ በዓል!

From Axum Hidar Tsion Celebration -Part Two የዛሬው የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል በዚህ መልኩ እይተከበረ ነው
01/12/2019

From Axum Hidar Tsion Celebration -Part Two የዛሬው የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል በዚህ መልኩ እይተከበረ ነው

የ የዘንድሮ 2012 ዓ/ም ህዳር ጽዮን በዓል አከባበር
01/12/2019

የ የዘንድሮ 2012 ዓ/ም ህዳር ጽዮን በዓል አከባበር

2019 Aksum Hidar tsion Celebration in Tigray Ethiopia

Address

Addis Ababa
ADDISABABA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WudaseTube - ውዳሴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to WudaseTube - ውዳሴ:

Share