Christ Centered Missionary Gospel Ministry

Christ Centered Missionary Gospel Ministry Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christ Centered Missionary Gospel Ministry, Religious organisation, wholeworld, Hossana.
(6)

በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ ፣በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን አሜን🙏
ይህ ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሚስዮናዊ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ነው።

👉 ወንጌል ስርጭት እናደርጋለን
👉 ለቤተክርስቲያን ድምጽ እንሆናለን
👉 ክርስቲያን ዜናዎችን እንሰራለን
👉 ወቅታዊና አዳዲስ ጠቃሚ ነገሮችን እናስተላልፋለን

14/09/2026

በእርግጥ መሽቷል....🌸

ግን አንድ ጊዜ ላስቸግራችሁ
መዳን በእምነት ብቻ ነው ብላችሁ ጻፉና.. ✍ ተኙ

  ‼️የቀጠለ...1.   ፦መከራን መቀበል ፈቃደኛ መሆን ማለት ራሱ መከራን ከመቀበል ጋር ተመሳሳይ እንዳልሆነበግልጽ ሊታወቅ ይገባል። መከራን ለመቀበል የተዘጋጀ ልብ አለኝ ማለት በቀላል ቋን...
14/09/2026

‼️የቀጠለ...

1. ፦መከራን መቀበል ፈቃደኛ መሆን ማለት ራሱ መከራን ከመቀበል ጋር ተመሳሳይ እንዳልሆነበግልጽ ሊታወቅ ይገባል። መከራን ለመቀበል የተዘጋጀ ልብ አለኝ ማለት በቀላል ቋንቋበእግዚአብሔር ፊት ለጌታ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ወይም ፈተናዎችን ለመታገስ ፈቃደኛ ነኝማለት ነው። አገልጋይ እንዲህ ዓይነት ልብ ሊኖረው ይገባል።

2. ፦ ትጋት ማለት ታካች አለመሆን፣ ከሥራ አለመሸሽ፣ የሚሠሩ ነገሮች እንደሚጠፉ ተስፋአለማድረግና ለሥራ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየት ማለት ነው። ብዙን ጊዜ የአገልጋይ የግል ሕይወትየአገልግሎቱን ስፋትና ጥልቀት የመወሰን አቅም አለው። በዚህ መለኮታዊ የአገልግሎት መንገድያደጉና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ወጣት አገልጋዮችን እናያለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ማቴ 25፡18-30 ላይ እንደምንመለከተው ትጉነት እግዚአብሔር ከአገልጋዮችመሠረታዊ ባሕሪ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ጌታችን ኢየሱስ በወቀሰው በዚህ አገልጋይ ባሕሪውስጥ ጌታ በግልጽ ሁለት መሠረታዊ ጉድለቶችን ወይም እንከኖችን አሳይቶናል።

የመጀመሪያው ክፉ መሆኑ ሲሆን፣ ሁለተኛው ሃኬተኛ መሆኑ ነው። ጌታውን ካልዘራበት የሚያጭድና ካልበተነበት የሚሰበስብ ጨካኝ አደርጎ መክሰሱ ክፉሲያስብለው፣ መክሊቱን ወስዶ መቅበሩ ታካችነቱን ያሳያል። መክሊቱን መሬት ውስጥሲቀብረው ልቡ ያሰላስል የነበረው “ክፋትን” ሲሆን፣ እጁ ግን ይሠራ የነበረው “ሃኬትን” ነው።እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ከታካችነት ሌላ ምን ስም ሊሰጠው ይችላል?

በአዲስ ኪዳን ከጴጥሮስ እስከ ጳውሎስ ያሉ ሐዋርያትን ስንመለከት በአንዱም የስንፍና ሕይወትአንመለከትም። እነዚህ የወንጌል አርበኞች ጊዜያቸውን ከንቱ ስለማሳለፍ የሚያስቡ አልነበሩም።አገልግሎታቸውን በትጋት የሚፈጽሙና እያንዳንዱን አጋጣሚ ጌታን ለማገልገል የሚዋጁእንጂ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች በጊዜውም አለጊዜውም ቃሉን መስበክ፣ ትጉ መሆንአለባቸው(2ኛ ጢሞ 4፡2)።

እኛም ዛሬ በወንጌል ሥራ ላይ የተሰማራን የመጀመሪያዎቹን አርአያበመከተል ያለመታከት እግዚአብሔርን ልናገለግል ይገባናል። የጳውሎስን በተናጠል ስንመለከትያለ ዕረፍትና ያለመታከት ለረጅም ሰዓታት ራሱን በሥራ ይጠምድ ነበር፣ ስንፍና የሚባል ነገርፈጽሞ አይታይበትም።

ጳውሎስ ግን እንዲህ አይደለም። በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንኳ የፊልጵስዩስን አማኞች ያጽናናቸው ነበር(ፊል 4፡4)። እውነቱን ለመናገር ታካቾች የእግዚአብሔርን ሥራ ብቻ ሳይሆን የሰውንም ሥራ መሥራት እንደማይችሉ መናገር ይቻላል። ሰነፎች በምግባራቸው ከማንኛውም ሰው የተሸሉ እንደሆኑ በማስመሰል ራሳቸውን “የእግዚአብሔር አገልጋይ” እያሉ ያወድሳሉ።
ራሳቸውን የእግዚአብሔር አገልጋይ ብለው በማሳመናቸው ማንም ሊቆጣጠራቸው አይችልም።እንደ አገልጋይ የእግዚአብሔር ልጆችን ለማገልገል ደስ እያለን ጊዜያችንን መጠቀምና ራሳችንንምመስጠት ይኖርብናል(ሐዋ 20፡35)።

3. ፦ ቤተሰብ የሚለው ሀሳብ እንደ ባህሉና እንደ አካባቢው ሁኔታ የሚወሰን ቢሆንም በአብዛኛውግን ወላጆችና ልጆችን የሚያጠቃልል ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ በቅርብ አብረዋቸው በዕለትተእለት ኑሮ ውስጥ በቅርበት ተሳታፊ የሆኑ የቤተሰቡ አባላት አድርገው ይተረጉማሉ። ጋብቻደግሞ የቤተሰብ መሰረት እንደሆነ የታመነ ነው።

አሁን በዓለማችን ላይ ቤተሰብ መስርቶ መኖርፋሽኑ ያለፈበት ተደርጎ የሚቆጥር ማህበረሰብ እየተፈጠረ ሲሆን በሌላ አንጻር ደግሞ ከጋብቻመፍረስ ጋር ተያይዝ ብዙ ቤተሰብም እየተበተነ ነው። አገልጋይ እግዚአብሔርን ሲያገለግልበቅርቡ ላሉ ቤተሰቦቹ ምን ማድረግ እንዳለበት ሊገነዘብ የተገባ ነው። ስለዚህ የትኛውምአገልጋይ በቅርቡ ላሉ ቤተሰቦቹ ግብረ ገባዊ የሆኑ ግዴታዎች አሉት።

4. ፦ ሁልጊዜ የጳውሎስ፣ የጴጥሮስን ሕይወት ተከታዮች እንዲሆኑ የሚጠቁም ብቻ ሳይሆንለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በከፍተኛ ደረጃ ሕይወቱን በመስጠት የክርስቶስን ሕይወት በገዛሕይወቱ በማንጸባረቅ ምሳሌነቱን ሌሎችን ማካፈል አለበት። ተማሪዎቻችንን በተብራራትምህርት ብቻ ከመሪያቸው ያላዩትን ሕይወት ሊኖሩና ሊተገብሩት አይችሉም ስለዚህ ኤፌ 4፡13 እንደተጻፈው መልካም የሆነ ተግባራዊ ሕይወት ልናሳያቸው የተገባ ነው። አገልጋይ ምሳሌያዊማንነቱ የሚስብ ወይንም የሚታይ ነገር ከሌለው የሚከተለው ሊያገኝ አይችልም።


 አገልጋይ ሁለንተናውን ለእግዚአብሔር ያስገዛ ሰው ነው(ሮሜ 6፡12-14፣ 12፡11-12)።
 አገልጋይ በተቃዋሚዎች ምክንያት የማይደነግጥና ስፍራውን የማይለቅ ሰው መሆን አለበት(ነህ 2፡19-20፣ 4፡1-6፣ ሮሜ 8፡35-39)።
 አገልጋይ በጌታ የሚተማመንና ራሱን የካደ ሰው ሊሆን ይገባል(ፊል 2፡17-30)።
 አገልጋይ ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ዓይን የሚያይ ከአድልዎ ነጻ አቋም ያለውና ክፉውን በመልካም ለማሸነፍ የሚተጋ ሰው ነው(ሮሜ 12፡21)።
 አገልጋይ ብድራቱን ከእግዚአብሔር እየጠበቀ ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን ለማድረግ የሚተጋ ሰው ነው።

‼️🥰🙏

ሁሉንም ለማንበብ የሚትፈልጉ ተለግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ ፦ https://t.me/ccmgm7

 ይህንን ፖስት የሚትችሉት ሁላችሁም ሼር አድርጉ። 🙏 ኮመንት ላይ ገብታችሁ   እያላችሁ ጻፉ ‼️👍✝️ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ነው‼️💗🙏
14/09/2026


ይህንን ፖስት የሚትችሉት ሁላችሁም ሼር አድርጉ። 🙏 ኮመንት ላይ ገብታችሁ እያላችሁ ጻፉ ‼️👍✝️

ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ ነው‼️💗🙏

14/09/2026

በእርግጥ Busy ናችሁ ....

ግን አንድ ጊዜ ላስቸግራችሁ " ኢየሱስ አማላጄ ነው ።" ብላችሁ ጻፉና !🙏
የሚክድ መንፈስ አለና 👹

13/09/2026

በእርግጥ መሽቷል....

ግን አንድ ጊዜ ላስቸግራችሁ
"ኢየሱስ ጌታ ነው።" ብላችሁ ጻፉና ተኙ!🙏
የሚናደድ መንፈስ አለና 👹

12/09/2026

Jesus is a king of king‼✝👌

 ❌🚫 የተሰኘ መጠጥ በድብቁ ማህበር  አዘጋጅነት የሚመረት ምርት እንደሆነ እየተደረሰበት ይገኛል‼ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ስዘዋወር እንዳየነው ፤ ኮካኮላ ከኦንላይን የሚገዙ ሰዎች ትዕዛዝ በሚ...
12/09/2026

❌🚫 የተሰኘ መጠጥ በድብቁ ማህበር አዘጋጅነት የሚመረት ምርት እንደሆነ እየተደረሰበት ይገኛል‼

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ስዘዋወር እንዳየነው ፤ ኮካኮላ ከኦንላይን የሚገዙ ሰዎች ትዕዛዝ በሚሰጡበት ወቅት ፤ አምራች ድርጅቱ በኮካኮላ ላይ የወደዱትን ስም እንዲያስጽፉ የሚገዙ ሰዎችን በሚጠይቅበት ጊዜ ፤ የሚገዙ ሰዎች የኢየሱስን ስምና በክርስትና አስተምህሮ ፤ የትኛውንም መንፈሳዊ ቃላቶችን ፤ በዋናነት እግዚአብሔርን የሚያወዲሱ ቃላቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ በቀጥታ እምቢ ነው የሚላቸው።

ነገር ግን ከእርሱ በተቃራኒ ፣ ማንኛውንም ሌላ ነገገር ኢየሱስን የሚሳደብ ፣ ሰይጣንን የሚያሞግስ እንዲሁም ከክርስትና እምነት ውጭ ያሉ ሃይማኖት እና አስተምህሮአቸውን ስም በነጻነት ይጽፋል ማለት ነው።

ስለዚህ አማኞች ከእንዲህ ዓይነት የኢየሱስን ክብር ከሚያዋርድ ድርግት መጠንቀቅ አለባቸው።

ወደ ሮሜ ሰዎች 13
¯¯¯¯¯¯¹¹ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
¹² ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
¹³ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
¹⁴ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።

 ‼✝ኢየሱስ ክርስቶስ “የአብ ልጅ” ተብሎ መጠራቱ በክርስትና እምነት በጣም ጥልቅ የሆነ እውነት ነው። ይህን በቀላሉና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እንመልከት።1. “ ” ማለት ምን ማለት ነው?ኢየ...
12/09/2026

‼✝

ኢየሱስ ክርስቶስ “የአብ ልጅ” ተብሎ መጠራቱ በክርስትና እምነት በጣም ጥልቅ የሆነ እውነት ነው። ይህን በቀላሉና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እንመልከት።

1. “ ” ማለት ምን ማለት ነው?
ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ተብሎ ሲጠራ፣ እንደ ሰው ልጅ በኋላ ተወልዶ የአብ ልጅ ሆነ ማለት አይደለም። ይህ ስም ከአብ ጋር ያለውን ልዩና ዘላለማዊ ግንኙነት ያሳያል።

ዮሐንስ 1፥1 እንዲህ ይላል፦ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”

ከዚያም ዮሐንስ 1፥14 ይህ ቃል ሥጋ ሆኖ በመካከላችን እንደኖረ ይናገራል። ይህም የሚያመለክተው ኢየሱስ ከዘላለም ጀምሮ ከአብ ጋር የነበረ እንደሆነ ነው።

2. ‼

ኢየሱስ ራሱ፦
“እኔና አብ አንድ ነን።” — ዮሐንስ 10፥30 ብሎ ተናግሯል።

ይህ ማለት አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው ማለት ሳይሆን፣ በመለኮት አንድ ናቸው ማለት ነው። ክርስቲያናዊ ትምህርት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት አማልእክት ሳይሆኑ አንድ እግዚአብሔር በሶስት አካላት እንደሚገለጥ ያስተምራል።

3. ‼

ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ፣ የአብ ድምፅ ከሰማይ መጣ፦
“ይህ የምወደው ልጄ ነው፥ በእርሱም ደስ ብሎኛል።”
— ማቴዎስ 3፥17

🤌 ይህ ኢየሱስ በአብ ዘንድ ያለውን ልዩ ልጅነት ያሳያል።

4. “ #ልጅ” ማለት ከአብ ያነሰ ነው ማለት አይደለም‼

ይህን ነጥብ በተለይ መረዳት አስፈላጊ ነው። ሰዎች “ልጅ” ሲሉ ብዙ ጊዜ ከአባቱ በኋላ የተወለደ እና ከአባቱ ያነሰ ሰው ይመስላቸዋል። ነገር ግን ስለ ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ሲባል ይህን ዓይነት የሰው ልጅነት አያመለክትም።

ዮሐንስ 5፥18 እንደሚያሳየው፣ ኢየሱስ እግዚአብሔርን “አባቴ” ብሎ በመጥራቱ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እያደረገ እንደሆነ አይሁድ ተረዱ።

5. ‼

ኢየሱስ፦ “እኔን ያየ አብን አይቷል።”
— ዮሐንስ 14፥9 ብሏል።

ይህ ኢየሱስ አብ ራሱ ነው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ኢየሱስ አብን ፍጹም በሆነ መንገድ የሚገልጥ ነው ማለት ነው።

ቆላስይስ 1፥15 ደግሞ ክርስቶስን “የማይታየው አምላክ ምሳሌ” ብሎ ይገልጸዋል።

6. ⁉

#በአጭሩ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ዘላለማዊ ልጅ ነው። እርሱ ከአብ ጋር በመለኮት አንድ ነው፤ ነገር ግን አብ አይደለም። እርሱ ወልድ ነው። ለድነታችንም ሰው ሆኖ ወደ ዓለም መጣ፣ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፣ ከሙታንም ተነሣ።
ስለዚህ “የአብ ልጅ” የሚለው ስም የኢየሱስን መለኮታዊ ማንነት፣ ከአብ ጋር ያለውን ዘላለማዊ ግንኙነት እና አብን ፍጹም መግለጡን ያሳያል።

“ይህ የምወደው ልጄ ነው” የሚለው የአብ ምስክርነትም የክርስቶስን ልዩ ማንነት በግልጽ ያሳያል። ማቴዎስ 3፥16

🤌🥰✝

  ⁉️ትክክለኛውን መልስ በግልጽ ለመረዳት፣ “ኢየሱስ አምላክ ነውን?” እና “ኢየሱስ አብ ነውን?” የሚሉትን ሁለት ጥያቄዎች መለየት ያስፈልጋል።1. ኢየሱስ አምላክ ነው?አዎን። መጽሐፍ ቅዱስ...
12/09/2026

⁉️

ትክክለኛውን መልስ በግልጽ ለመረዳት፣ “ኢየሱስ አምላክ ነውን?” እና “ኢየሱስ አብ ነውን?” የሚሉትን ሁለት ጥያቄዎች መለየት ያስፈልጋል።
1. ኢየሱስ አምላክ ነው?
አዎን። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን መለኮታዊ መሆኑን ያስተምራል።
📖 ዮሐንስ 1፥1፣ 14 — «ቃልም እግዚአብሔር ነበረ… ቃልም ሥጋ ሆነ።»
2. ኢየሱስ አብ ራሱ ነው?
በተለመደው የሥላሴ ክርስቲያናዊ ትምህርት፣ አይደለም።
ኢየሱስ ወልድ ነው፤ አብ ደግሞ አብ ነው። አብና ወልድ አንድ ማንነት አይደሉም።
ለምሳሌ፦ ኢየሱስ ወደ አብ ይጸልይ ነበር (ዮሐንስ 17፥1)፤ ስለዚህ ከአብ የተለየ ማንነት እንዳለው ያሳያል።
3. “እኔና አብ አንድ ነን” ማለትስ?
📖 ዮሐንስ 10፥30
ይህ ጥቅስ ኢየሱስና አብ አንድ ሰው ናቸው ማለት አይደለም፤ በመለኮት፣ በባሕርይና በክብር አንድ መሆናቸውን ያሳያል።
በአጭሩ፦
አብ አምላክ ነው።
ወልድ (ኢየሱስ) አምላክ ነው።
መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው።
ነገር ግን አብ ወልድ አይደለም፤ ወልድም አብ አይደለም። በባሕርይ አንድ አምላክ ሲሆኑ፣ በማንነት ግን ተለያይተው ይገለጣሉ።
ስለዚህ፦ ኢየሱስ አብ ራሱ አይደለም፤ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ወልድ ነው፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም አንድ መለኮት ያለው ነው። 🙏✝️

12/09/2026

Christ Centered Missionary Gospel Ministry
ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሚስዮናዊ የወንጌል አገልግሎት

Address

Wholeworld
Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ Centered Missionary Gospel Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Christ Centered Missionary Gospel Ministry:

Shortcuts

Share