Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council EIASC is a legal entity as per proclamation 1207/2020 that represents the spiritual and developmental interests of Ethiopian Muslims at the Federal level.
(1)

It has branch offices at all the regional states.

የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) መውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ ተከበረ።••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••ነሀሴ 19 /2018 ዓ.ል| ...
25/08/2026

የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) መውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ ተከበረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 19 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 12/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

1 ሺህ 5 መቶ 1ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

​በክብረ በዓሉ ላይ የፌዴራልና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዒማሞች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎ ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በክብረ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር የመውሊድ በዓልን ማከበር የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ከማስታወስ ባለፈ አስተምህሯቸውንና ሱናቸውን በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ መተግበር መሆኑን ገልጸዋል።

ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን በኢስላም ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን የመመካከር (ሹራ) እሴት በመጥቀስ ምክክር በቤተሰብ፣ በንግድና በማህበራዊ ህይወት አዎንታዊ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

በሀገር ደረጃ የተካሄደው ምክክርም ሊበረታታ የሚገባው መልካም ጅምር መሆኑን የገለጹት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንቱ የምክክሩ ውጤቱ ለሀገርና ለህዝብ የሚበጅ እንዲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ዱዓ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሀመድ ሸሪፍ ሐሰን በበኩላቸው ሕዝበ ሙስሊሙ የነብዩ ሙሀመድን ፈለግ በመከተል ብቻ መውሊድን ሊያከብር ይገባል ብለዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በከተማዋ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ሥራዎች የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ሸይኽ ሙሀመድ ሸሪፍ አስገንዝበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የነቢዩን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) መልካም አርአያነት የሚያስታውሱ መንዙማዎች፣ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ለ6 ሺህ አቅመ ደካማ ወገኖችም የምግብ ማብላት መርሀ ግብር ተከናውኗል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

በታላቁ አንዋር መስጂድ "ፍትሃዊው ነቢይ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሄደ።••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••ነሀሴ 17/2018...
23/08/2026

በታላቁ አንዋር መስጂድ "ፍትሃዊው ነቢይ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሀሴ 17/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 10 /1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​በነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ውልደት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በታላቁ አንዋር መስጂድ ተካሄደ።

ፓናል ውይይቱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀምዓ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የውይይት መርሃ ግብሩ 1ሺህ 5መቶ 1ኛውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዓ.ወ.) መውሊድ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።

ውይይቱን የታላቁ አንዋር መስጂድ ምክትል ኢማምና የብሔራዊ መውሊድ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሐሚድ አህመድ በንግግር ያስጀመሩት ሲሆን በመድረኩ ላይ "መውሊድ በሀበሻ እና ሁለተናዊ ፋይዳው" የሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ሸይኽ አብዱልሀሚድ በንግግራቸው ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሯቸው የፍትህ፣ የፍቅር እና የሰላም እሴቶች ለሀገር ግንባታና ለህዝቦች አብሮነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።

ሸይኽ አብዱልሀሚድ አክለውም መውሊድ ማህበራዊ አንድነትን፣ አብሮነትን እና የእርስ በርስ መደጋገፍን ያጠናክራል ብለዋል።

ዶክተር እድሪስ ሙሀመድ በዚሁ መድረክ ላይ ባቀረቡት "መውሊድ በሀበሻ እና ሁለተናዊ ፋይዳው" የተሰኘ ጥናታዊ ፅሁፋቸው መውሊድ በሀበሻ ምድር ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ እና ሁለተናዊ ፋይዳ አብራርተዋል።

የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም፣ ኻጢብና የብሔራዊ መውሊድ በዓል ኮሚቴ አስተባባሪ ሸይኽ ጧሀ ሙሀመድ ሀሩን በጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ኮሚቴ አባልና የሀላል ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ አህመድ አወሉ፣ የአዲስ አበባ እስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሸይኽ ኑርሁሴን ሸይኽ ሙስጠፋን ጨምሮ መሻዒኾች እናጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በውይይቱ ላይ ታዳሚ ሆነዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

የ2019 ዓ.ል የሐጅ በረራ አገልግሎትና መስተንግዶን ለማሻሻል ከሳዑዲ አየር መንገድ ጋር ውይይት ተደረገ።••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••ነሐሴ 1...
22/08/2026

የ2019 ዓ.ል የሐጅ በረራ አገልግሎትና መስተንግዶን ለማሻሻል ከሳዑዲ አየር መንገድ ጋር ውይይት ተደረገ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 16/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 09/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የ2019 ዓ.ል (1448 ዓ.ሒ) የሐጅ ጉዞን በተሻለ ሁኔታ ለማስፈጸምና ለኢትዮጵያ ሁጃጆች ቀልጣፋና ምቹ የበረራ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ውይይት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ቢሮ ተካሄደ።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ቢሮ የተካሄደውን የሁለቱ ተቋማት ውይይት በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ የመሩት ሲሆን ውይይቱ የ2019 ዓ.ል የሐጅ ተጓዦች የሚያገኙትን የበረራ አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ ማድረግን ለማድረግ ዓላማ ያደረገ ነው።

የሳዑዲ አየር መንገድ በ2018 ዓ.ል የሀጅ ወቅት ለሁጃጆች ላቀረበው ቀልጣፋ እና ምቹ አገልግሎት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣዩ የሐጅ ወቅት ሁጃጆች ካለፉት ዓመታት የተሻለ የጉዞ አገልግሎት እንዲያገኙ የሁለቱ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጠናከር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም በውይይቱ ተመላክቷል።

በውይይቱ ላይ የሳዑዲ አየር መንገድ GSA ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው፣ የአዲስ አበባ ሽያጭ ኃላፊ ወ/ሮ ሀያት አብደላ እና የዓመቱ የሐጅ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ወንድወሰን አሰፋ ተገኝተዋል።

የሳዑዲ አየር መንገድ ተወካዮች የኢትዮጵያ ሁጃጆች የተሻለ የበረራ አገልግሎትና መስተንግዶ አግኝተው መንፈሳዊ ጉዟቸውን በሰላም፣ በምቾትና በእርካታ አጠናቀው እንዲመለሱ የአገልግሎት ማሻሻያ ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የ2019 ን የሐጅ ምዝገባ ከባለፈው ዓመት ቀደም ብሎ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሐጅ ለማድረግ ንያ ያላቸው ከወዲሁ ለጉዞው አስፈላጊ የሆኑ የጉዞ ሰነዶችን አዘጋጅተው እንዲጠብቁም ጥሪ ቀርቧል።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

22/08/2026
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሃጅና ኡምራ ዘርፍ የስራ ልዑክ በሁጃጆች የበረራ አገልግሎትና መስተንግዶ ዙሪያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዬ።••••••••••••••••••••••...
21/08/2026

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሃጅና ኡምራ ዘርፍ የስራ ልዑክ በሁጃጆች የበረራ አገልግሎትና መስተንግዶ ዙሪያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዬ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 14 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 07/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ1448 ዓ.ሒ. (2019 ዓ.ል) የሀጅ ምዝገባ አገልግሎት ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራት መጀመሩ ይታወቃል።

የዘርፉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሀጅ አገልግሎቱን በተቀናጀ መልኩ ስኬታማ ለማድረግ የሚያግዝ የሁለትዮሽ ውይይት ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች ጋር ያደረጉ ሲሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋርም ተመሳሳይ ውይይት አድርገዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ የተመራው የስራ ልዑክ ከበረራ ጋር በተያያዘ የ2019 የሀጅ ተጓዦች የተቀላጠፈ አገልግሎትና መስተንግዶ ማግኘት በሚችሉባቸው ነጥቦች ዙሪያ ነው ሁለቱ ተቋማት ውይይት ያደረጉት።

የ2018 የሀጅ ጉዞ የበረራ አገልግሎት እና መስተንግዶ ስኬታማ እንደነበረ ያወሱት የሀጅና ዑምራ ዘርፉ ኃላፊው ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ አየር መንገዱ ላደረገው ሁለንተናዊ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአዲስ አበባ ሽያጭ ክፍል ኃላፊ አቶ አዲሱ ለይኩን በበኩላቸው አየር መንገዱ የሀጅ ተጓዦች ምቾታቸው ተጠብቆ መንፈሳዊ የሀጅ ጉዟቸውን እንዲፈጽሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረት ይሰራ ብለዋል።

የአየር መንገዱ የኢቲ ሆሊደይ ኃላፊ ወይዘሮ ዘቢባ ሚፍታህ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀጅ ተጓዦች የሚሰጠውን አገልግሎት በየ ጊዜው እያሻሻለ የመጣ ሲሆን በቀጣይም የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ ከወዲሁ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።

የሁለቱን ተቋማት ተቀናጅቶ መስራት ለሁጃጆች የአገልግሎት እርካታ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በውይይቱ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን የሀጅ ምዝገባ ከባለፈው ዓመት ቀደም ብሎ እንደሚጀመርና ንያ ያላቸው ሙስሊሞች ከወዲሁ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን አዘጋጅተው እንዲጠብቁም ጥሪ ቀርቧል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

20/08/2026

የ1 ሺህ 5 መቶ 1ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መውሊድ መግለጫ።

"ዓለማችን በግጭት፣ በስግብግብነት እና በግድየለሽነት እየተናጠች በሚገኝበት በዚህ ወቅት ለሰላምና ለአብሮነት የነቢዩ ሙሀመድን (ሶ.ዐ.ወ) የሕይወት ፈለግ መከተል መፍትሄ ነው" - ጠቅላይ ም...
20/08/2026

"ዓለማችን በግጭት፣ በስግብግብነት እና በግድየለሽነት እየተናጠች በሚገኝበት በዚህ ወቅት ለሰላምና ለአብሮነት የነቢዩ ሙሀመድን (ሶ.ዐ.ወ) የሕይወት ፈለግ መከተል መፍትሄ ነው" - ጠቅላይ ምክር ቤቱ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 14 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 07/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው ህዝበ ሙስሊም ለ1 ሺህ 5 መቶ 1ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የመውሊድ ብሔራዊ አብይ ኮሚቴ አባል እና የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሸይኽ ጠሐ ሙሐመድ ሐሩን በዓሉ የነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ) የህይወት መርህ እስልምናን ለመማማርና እስልምናን ወደሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ መሐመድ ሸሪፍ በበኩላቸው ህዝበ ሙስሊሙ መሪዎቹን በመረጠበት ማግስት የሚከበር መሆኑ የዘንድሮውን መውሊድ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ሸይኽ መሐመድ ሸሪፍ አክለውም የሚያከብረውም የማያከብረውም ምርጫው የእራሱ በመሆኑ የልዩነት ምክንያት ሊሆን አይገባም ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱን ጋዜጣዊ መግለጫ በንባብ ያቀረቡት የመውሊድ ብሄራዊ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ ሲሆኑ የመውሊድ በዓል የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ዘመን አይሽሬ ነቢያዊ ተልዕኮ፣ አስተምህሮ እና ሰብዓዊ አርአያነት የሚታሰብበት ልዩ አጋጣሚ መሆኑን በመግለጫው ተጠቅሷል።

ዕለቱ የሰው ልጆች በእርሳቸው መወለድ ያገኙትን መለኮታዊ ብርሃን በማውሳት የሚደሰቱበትና ስታ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት የሚወርድበት መሆኑ መግለጫው አስረድቷል።

​ዓለማችን በግጭት፣ በስግብግብነት እና በግድየለሽነት እየተናጠች በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ በሰላምና በአንድነት አብሮ ለመኖር የነቢዩ ሙሀመድን (ሶ.ዐ.ወ) የሕይወት ፈለግ መከተል ወሳኝ መሆኑንም ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመግለጫው አሳስቧል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅመ-ደካሞችን፣ ተፈናቃዮችን እና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ይቅር መባባል (አውፉታ) ኢስላማዊ እሴቶች መሆናቸውን በመገንዘብ ሀገራዊና ውስጣዊ አንድነቱን ሊያጠናክር እንደሚገባም ተጠቅሷል።

በግለጫው አያይዞም ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ውጤታማ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ህዝበ ሙስሊሙ አዎንታዊ ድጋፍ እና ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በብሔራዊ ደረጃ በታላቁ አንዋር መስጂድ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አመራሮች የክብር ሽኝትና የእውቅና መርሃ ግብር አካሄደ።••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••...
19/08/2026

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አመራሮች የክብር ሽኝትና የእውቅና መርሃ ግብር አካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 06/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለቀድሞው የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት የክብር ሽኝት መርሃ ግብር አካሄደ።

​ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትላንትናው ዕለት በከናወነው የሽኝት መርሃግብር ላይ የቀድሞዎቹ አመራሮች በስራ ዘመናቸው ለነበራቸው አገልግሎት እና የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ አዋጅ እንዲሻሻል ለተጫወቱት በጎ ሚና እውቅና ሰጥቷል።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ አዋጅ መሻሻል የወቅቱን ሁኔታ ያገናዘበና የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ የመለሰ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሸሪአ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጥ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በጎ ሚና እንደሚጫወትም ፕሬዝደንቱ አንስተዋል።

​በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ መከተ ሙሄን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

በዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር ውይይት አደረገ።••••••••••••••••••••••••••••••••••••••...
18/08/2026

በዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር ውይይት አደረገ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 12 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 05/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ1448 የሀጅ ምዝገባ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ዘርፉ በላቀ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የሀጅ አገልግሎቱን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በውጤት ለማጠናቀቅ ከሃገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ጀምሯል።

በዛሬው ዕለትም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ የተመራ የስራ ኃላፊዎችና የባለሙያዎች ልዑክ የ1448ን የሀጅ አገልግሎት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ በ1447 የሀጅ አገልግሎት ስኬትና በቀጣዩ የሀጅ ጉዞ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በሀጅ አገልግሎት ዘርፍ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ላበረከተው በጎ አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል።

የሁለቱን ተቋማት ትስስር የበለጠ ለማጠናከር እና ሁጃጆች በቀጣይም ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉባቸውን መንገዶች በተመለከተም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ በበኩላቸው መስሪያ ቤታቸው ዜጎችን በእኩልነት ማገልገል ቀዳሚ ዓላማው መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ጊዜ በቢሮና በመሶብ አገልግሎት ከ40 በላይ ማዕከላትን አደራጅቶ የፓስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አብራርቷል፡፡

አቶ ቢቂላ መዝገቡ አክለውም ህዝበ ሙስሊሙ በአካባቢው ወደሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሄድ የሚፈልገውን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ገልጸዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ልዑክ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤትን የአገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን አገልግሎት አሰጣጡ በግብዓትና በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ አገልግሎት ፈላጊዎች ያለ ወረፋ ሲስተናገዱ መመልከትም ተችሏል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሐጅ ከባለፈው ዓመት ቀደም ብሎ የሁጃጅ ምዝገባ የሚጀምር ሲሆን ንያ ያላቸው አማኞች የተመቻቸውን አጋጣሚ በመጠቀም ከወዲሁ ፓስፖርትና መታወቂያቸውን ጨምሮ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን አዘጋጅተው እንዲጠባበቁ ጥሪ ቀርቧል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ።•••••••••••••••••••••••••••••••••ነሐሴ 12 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 05/144...
18/08/2026

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
ነሐሴ 12 /2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 05/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው ያለፈውን ዓመት ልዩ ልዩ ሪፖርቶች መርምሮ ለቀጣይ ሥራ ጠቃሚ የሚሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎችን አጽድቋል።

ተቋማዊ አሰራር፣ ወንድማማችነት እና ሁለንተናዊ ልዕልና በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ይህ ጉባኤ የ2018ን የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሪፖርቶች ለይ ተወያይቶ የ2019 ዓ.ል. ዓመታዊ ዕቅድና በጀት እንዲሁም የተቋሙን የአምስት ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በማጽደቅ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

የጉባኤው አባላት በጉባዔው ማጠቃለያ ዕለት ደም በመለገስ የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ያዘጋጀውን ከተማ አቀፍ የደም ልገሳ ንቅናቄ አስጀምረዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Address

Tor Hayloch, Next To Holland Embassy
Addis Ababa
28441

Opening Hours

Monday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:00
Tuesday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:00
Wednesday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:00
Thursday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:01
Saturday 08:30 - 12:30

Telephone

+251113729965

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council:

Shortcuts

Share