እንተ ይእቲ channel

እንተ ይእቲ channel እግዚአብሔር እረኛዬ ነው🙏

+ ሰው ቢኾኑም ክንፎች ነበሯቸው +አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለም ዙሪያ የሚዘከሩ እና ተዓምራታቸውም በሁሉ እየታወቀ የመጣ ቅዱስ ናቸው። በግብጽ ሀገር ካይሮ ከተማ ለሚኖሩ አቶ ኦሳማ ማህር ለተ...
30/08/2025

+ ሰው ቢኾኑም ክንፎች ነበሯቸው +

አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለም ዙሪያ የሚዘከሩ እና ተዓምራታቸውም በሁሉ እየታወቀ የመጣ ቅዱስ ናቸው። በግብጽ ሀገር ካይሮ ከተማ ለሚኖሩ አቶ ኦሳማ ማህር ለተባሉ ሰው በቅርብ ዘመን የፈጸሙላቸውን ተዓምር እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ። አቶ ኦሳማ ማህር እንዲህ ብለው ሁኔታውን ገልጸውታል፦

እኔ የከበሩ ድንጋዮችን የመሰብሰብ ልማድ ነበረኝ። በዚህም የተነሳ በግብጽ አል-ሚንያ ከተማ የጌጣጌጥ መሸጫ የነበረው አቶ አህመድ የተባለ ሰው ተዋወቅሁ። አንድ ጊዜ አንድ ወዳጁ የከበረ ድንጋይ የመሸጥ ፍላጎት እንዳለው ነገረኝ እና ከካይሮ ተነስቼ ወደ አል-ሚንያ ሄድኩኝ። በጉዞ ወቅት ሌላ ጊዜ እንደማደርገው ሁሉ የአባ አንጌሎስን ቆብ በኪሴ አደረግሁ። ኾኖም ግን ታሪካቸውን አንብቤ ነበረና፤ ባልተለመደ ሁኔታ አቡነ ተክለሃይማኖት በጉዞዬ እንዲረዱኝ በጸሎት ተማጸንኳቸው።

በመሸጫ ሱቁ ውስጥ እያለሁ አንድ አቶ መሐመድ የተባለ ሰው ወደ ሱቁ ገባ። ይህ ሰው ደልደል ያለ ሰውነት ያለው ሲኾን፥ ዕይታውም የሚያስፈራ ነበር። ገና እኔን ከማየቱ አስተያየቱ ጥሩ አልነበረም። እጅግ ባልተለመደ እና በሚያስፈራ ሁኔታ ይመለከተኝ ጀመረ። እኔም ፈራሁና፥ እጄን በኪሴ ወደያዝኩት የአባ አንጌሎስን ቆብ እና የአቡነ ተክለሃይማኖትን ሥዕለ አድኅኖ ሰደድኩ። ይህንን ባደረግሁበት ቅጽበት ምክንያቱን በማላውቀው ሁኔታ የጭንቅላቴ ኋላ ደነዘዘ። አቶ መሐመድም ወደ መሬት ወደቀና በኃይል መንፈራገጥ ጀመረ፤ ትንሽ ቆይቶ ግን ሰውነቱ ተረጋጋ።

የሱቁ ባለቤት የኾነው አቶ አህመድም ወደ አቶ መሐመድ ሄዶ ይቀሰቅሰው ጀመረ። አቶ መሐመድም እንደተነሳ ወዲያው ቆመና "በኪስህ የያዝከው ቆብ እንደ እሳት ይነዳል!" አለኝ። ከዚያም አባ አንጌሎስ ምን እንደሚመስሉ ይነግረኝ ጀመረ። እኔም ግራ ተጋብቼ "ምንም አልገባኝም" አልኩት። እርሱም "ለብዙ ዓመታት በእርኩስ መንፈስ ተይዤ ነበር። አንተን እንዳየሁህ በአካባቢው እሳት እንዳለ ተሰማኝ፤ የእሳቱ ምንጭም በኪስህ እንዳለ ተረዳሁ። በላዬ ላይ ያለው እርኩስ መንፈስ በእጁ የብረት ዘንግ ይዞ ነበር፤ ጭንቅላትህንም ከኋላ ሊመታህ ነበር። ከዚያ አባ አንጌሎስን አየኋቸው፤ አብረዋቸውም ሌላ ሰው ነበሩ። እኚህ አብረዋቸው የነበሩት ሰው ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያለቸው ሲኾን፤ ፊታቸውም ያበራ ነበር። ሰው ቢኾኑም ክንፎች ነበሯቸው። በእኔ ላይ ያደረው እርኩስ መንፈስ ሊመታህ ሲል፤ እኚህ ሰው "አንተ እርኩስ መንፈስ፥ እኔ ተክለ ሂባቦት፥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እገስጽሃለሁ! ከልጄ ዘወር በል!" ብለው ገሰጹት እና በእጃቸው የያዙትን መስቀል ወደ እኔ አዞሩት" አለኝ።

እኔም "ስማቸው ተክለ ሂባቦት ሳይኾን ተክለ ሃይማኖት ነው" አልኩት። እርሱም "እርሱ ለእኔ ችግር የለውም። ስለ ስም አልጨነቅም። ዋናው ነገር በስተመጨረሻ ከእርኩስ መንፈሱ ነጻ መኾኔ ነው" አለኝ። የዚያን ቀን ልገዛው የሄድኩትን የከበረ ድንጋይ ባልገዛም፤ እግዚአብሔር ቅዱሳኑን ወደ እኛ የሚልክ ኃያል አምላክ መኾኑን ግን ተረድቼ ተመለስኩ።

ምንጭ፦ Orthodox Saint Stories FB Page

Address

Addis Ababa

Telephone

+251948015928

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እንተ ይእቲ channel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to እንተ ይእቲ channel:

Share