Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - Children and Youth Ministry

Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - Children and Youth Ministry This is the Official page of EECMY Head Office -Department of Children and Youth Ministry

14/05/2026

የጥንቃቄ መልዕክት❗️❗️❗️

ዋትሳፕ እና ቴሌግራምዎ እየጠለፉብዎት ነው? የተለመዱ የጠለፋ ዘዴዎች እና መፍትሄዎቻቸው

አሁን አሁን የጓደኛዎ፣ የቤተሰብዎ ወይም የምታውቁት ሰው አካውንት ተጠልፎ በስማቸው ብር ሲጠየቁ፣ የሆነ አሳሳች መልእክት ሲላክላችሁ ማየት የተለመደ ሆኗል። ይህን የመሰለ የሳይበር ጥቃት በየቀኑ በብዙዎች ላይ እየደረሰ ነው።

ታዲያ እነዚህ ጠላፊዎች (ሀከሮች) ምን ዘዴዎችን ይጠቀማሉ? እንዴትስ መጠለፉን ማወቅ እንችላለን? የኢትዮቴሌኮም ክሪኤቲቭ ኤክስፐርት እና የአይ ቲ ባለሙያ ዩሀንስ ሀለፎም ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሞዛይክ ረፋድ ቀጣዩን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋናዎቹ የመጠለፊያ ዘዴዎች የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ስርቆት፡- ብዙ ጊዜ "ኮድ ልኬልሃለሁ፣ አሳየኝ" በሚል ማታለያ ኮዱን በመውሰድ አካውንትዎን ይቆጣጠራሉ። የላኩትን ኮድ በፍጹም አያጋሩ!አሳሳች ሊንኮች (Phishing Links)፡ ከሚያውቁት ሰው "ፎቶህን እዚህ ላይ አየሁት" ወይም "ይህንን ሊንክ ተጫን" የሚሉ መልእክቶች ይላካሉ። አንዴ ከተጫኑት ግን አካውንትዎ ለጠላፊው ክፍት ይሆናል።

አካውንትዎ መጠለፉን የሚያሳዩ ምልክቶች (Red Flags)

* እርስዎ ያላኳቸው መልእክቶች በድንገት መላክ።

* ቴሌግራም ወይም ዋትሳፕ ላይ እርስዎ ሳይከፍቱት መልእክቶች 'Seen' መደረግ።

* ሴቲንግ ውስጥ ባለው 'Devices' ዝርዝር ውስጥ እርስዎ የማያውቁት ስልክ ወይም ላፕቶፕ መኖር።

* ስልክዎ ምንም ሳይጠቀሙ ባትሪው በፍጥነት ማለቅ ወይም ዳታው ያለ ምክንያት መውረድ (ይህ ስፓይዌር/ሰላይ ሶፍትዌር እንደተጫነ ሊያመላክት ይችላል)።

እራስዎን እንዴት ይከላከላሉ? ዜሮ ትረስት (Zero Trust) ይኑርዎት፦ የቅርብ ጓደኛዎ ቢሆን እንኳ አጠራጣሪ ሊንክ ከላከልዎ አትክፈቱ። የተጠለፈው የእሱ አካውንት ሊሆን ይችላል።

Two-Step Verification (የሁለትዮሽ ማረጋገጫ)፦ ይህንን ሴቲንግ ማብራት እንደ ቤትዎ በር ሁለተኛ ቁልፍ መቆለፍ ነው። ይህን ካደረጉ ፓስወርድዎን ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ሁለተኛ ኮድም ስለማያውቁ ጠላፊው መግባት አይችልም።

አካውንትዎ ከተጠለፈ ምን ያድርጉ?

* ወዲያውኑ ወደ *Settings > Devices

* በመሄድ የማያውቁትን መሳሪያ 'Terminate/Log out' ያድርጉ።

* ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ሙሉ በሙሉ (Uninstall) አድርገው በድጋሚ በመጫን በስልክ ቁጥርዎ በኩል እንደ አዲስ ለመግባት ይሞክሩ።

* የሚችሉትን ሁሉ በሌላ መንገድ (ለምሳሌ በስልክ በመደወል) ለጓደኞችዎ አካውንትዎ እንደተጠለፈ እና እንዳይጭበረበሩ ያሳውቁ። ማሳሰቢያ፦ የመንግስት ኃላፊ ከሆኑ ወይም የመንግስት መረጃዎች ካሉዎት፣ ወዲያውኑ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ማሳወቅ ያስፈልጋል።

#ኢንሳ #የሳይበርደህንነት

14/05/2026

🛡️ የልጆችዎን የሳይበር ደህንነት እንዴት ይጠብቃሉ?

በዚህ የዲጂታል ዘመን ልጆቻችንን ከሳይበር አደጋዎች መጠበቅ የነገዋን ሀገር እንደመገንባት ይቆጠራል። በመሆኑም ወላጆች እነዚህን 4 አጫጭር ነጥቦች በመተግበር ልጆቻቸውን ሊጠብቁ ይገባል፦

🔹 1. ግልጽ ውይይት ያድርጉ፡- ቴክኖሎጂን ከመከልከል ይልቅ፤ ልጆች በቲክቶክ፣ ቴሌግራም ወይም ጌሞች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ያልተገቡ ምስሎችም ሆነ ትንኮሳዎች ሳይደብቁ እንዲነግሩዎት የጓደኝነት ድባብ ይፍጠሩ።

🔹 2. የቁጥጥር መተግበሪያዎችን ይጠቀሙ (Parental Controls)፡- እንደ “Google Family Link” ያሉትን በመጠቀም ልጆችዎ የሚጎበኙትን ድረ-ገጽ እና በስልክ የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቆጣጠሩ።

🔹 3. የግል መረጃ አያያዝን ያስተምሩ፡- ልጆች ሙሉ ስማቸውን፣ ትምህርት ቤታቸውን፣ ያሉበትን ቦታ (Location)፣ እንዲሁም የቤተሰብ መረጃን በኢንተርኔት ለማያውቁት ሰው እንዳይሰጡ በጥብቅ ያስጠንቅቁ።

🔹 4. ከአጭበርባሪ ሊንኮች ይጠብቁ (Phishing)፡- "ነፃ ሽልማት ደርሶሃል" በሚሉ አጭበርባሪ መልዕክቶች እንዳይታለሉ እና የይለፍ ቃላቸውን (Password) ለማንም እንዳይሰጡ ያስተምሩ።

በሀገራችን የዲጂታል ክፍያዎች (እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ቴሌብር ወዘተ) አጠቃቀም በፍጥነት እያደገ ነው። ልጆች ባለማወቅ የወላጆችን ስልክ ወስደው ለተለያዩ የኢንተርኔት ጌሞች ክፍያ እንዳይፈጽሙ ወይም ለአጭበርባሪዎች የባንክ መረጃ እንዳያጋልጡ የስልክዎን የይለፍ-ቃል (Password/PIN) ሚስጥራዊነት ይጠብቁ!


ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933

13/05/2026

A historic milestone for theology in Ethiopia.
We are proud to announce the launch of the Ethiopian Theological Journal — a new platform for theological scholarship, research, and global academic engagement from Ethiopia.

Explore the journal here: https://ethiopiantheologicaljournal.com/index.php/ethiopiantheologicaljournal

May this initiative serve the Church, academia, and the Kingdom of God for generations to come.

EECMY Children Ministry - MY Sunday School
13/05/2026

EECMY Children Ministry - MY Sunday School

13/05/2026
26/04/2026

EECMY Youth Ministry

ልዩ የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ቆይታ በኢትዮጵያ ወንጌላዊው ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዋናው ጽ/ቤት: በኢቫንጄሊካል ቴሌቪዥን ...EECMY Youth Ministry EECMY Child...
26/04/2026

ልዩ የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ቆይታ በኢትዮጵያ ወንጌላዊው ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ዋናው ጽ/ቤት: በኢቫንጄሊካል ቴሌቪዥን ...
EECMY Youth Ministry EECMY Children Ministry - MY Sunday School

2 likes. "ልዩ የበአል ቆይታ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ አመራሮች ጋር"

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus Evangelical MEDIA/Council 🙏!
12/04/2026

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus Evangelical MEDIA/Council 🙏!

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus
12/04/2026

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus

EECMY Youth Ministry
09/04/2026

EECMY Youth Ministry

Address

P. O. Box 2087 Jomo Kenyatta Road
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - Children and Youth Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - Children and Youth Ministry:

Share