ሃሌሉያ Christian Media Network-HCMN

ሃሌሉያ Christian Media Network-HCMN This page is mainly created to show, the way of God, and help followers how to know God's way, and walk along the right way
(2)

30/04/2026

ወንጌል 👏

እግዚያብሄርን ማወቅ ማትረፊያም መትረፊያም ነው:: እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ::ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እ...
30/04/2026

እግዚያብሄርን ማወቅ ማትረፊያም መትረፊያም ነው::
እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ::

ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር። --------------ኤርምያስ 9:24
ውበት ረጋፊ
ሃብትም ጠፊ ነው
ሹመትም ይሻራል
ሰው ጌታን ካገኝ
ለዘላለም ያርፋል::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"
-----------------ማቴዎስ 11:28
ኢየሱስ በሁሉም ነገር እረፍታችን ነው::

28/04/2026

ኢየሱስ ይመጣል! 👏

ወንድማችን አክሊሉን እንምረጥ...በበጎ ስራዎቹ የምንወደውና የምናከብረው ወንድማችን አገልጋይ አክሊሉ ተስፋዬ Crown of humanity ለተሰኘው 1,000,000 ብር ለሚያሸልመው የበጎ አድ...
28/04/2026

ወንድማችን አክሊሉን እንምረጥ...
በበጎ ስራዎቹ የምንወደውና የምናከብረው ወንድማችን አገልጋይ አክሊሉ ተስፋዬ Crown of humanity ለተሰኘው 1,000,000 ብር ለሚያሸልመው የበጎ አድራጎት ሽልማት ታጭቷል።
ከታች የተቀመጠውን link እየተጫናችሁ ወንድማችንን ምረጡት።
https://crownofhumanityawards.org/vote

27/04/2026

ስለ ኢየሱስ አዳኝነት ማውራት ሱሴ ነው!
👏

የጴንጤ መቃብር 80 ሴ.ሜ ብቻ እንዲሆን ተወሰነ! በኢትዮጵያ የወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የነጌሌ አርሲ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ባደረገዉ የመካነ መቃብር አጠቃ...
27/04/2026

የጴንጤ መቃብር 80 ሴ.ሜ ብቻ እንዲሆን ተወሰነ!

በኢትዮጵያ የወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የነጌሌ አርሲ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ባደረገዉ የመካነ መቃብር አጠቃቀምና ሐዉልት ጉዳይ ዉይይት የቀብር ስፍራ የመቃብር ምልክት እንዲሆን ብቻ ወደ ላይ 80 ሴ.ሜ ብቻ ቁመት እንዲኖረዉ በጋራ ዉሳኔ በማጽደቅ ከዚህ በኋላ በመቃብር ስፍራ ትልልቅ የሐዉልት ግንባታዎችን ከመገንባት እንዲቆጠብ ሲሉ ወስነዉ ህብረተሰቡም ይህን አውቆ አላስፈላጊ ከሆነ ወጪና የገንዘብ ብክነት ራሱን እንዲጠብቅ ማስተማርና መምከር የአጥቢያ መሪዎች ድርሻ መሆኑን ገልጸዋል።

ቄስ ጉዲና ቱምሳ በትውልድ ከተማቸው የመታሰቢያ ሃውልት ቆመላቸው።በምዕራብ ወለጋ ቦጂ ወረዳ፣ ቢላ ከተማ በ1929 ዓ.ም በተወለዱባት ከተማ ሃውልት ቆሞላቸዋል። በሃውልቱ ምረቃ ወቅት የአብያተ...
24/04/2026

ቄስ ጉዲና ቱምሳ በትውልድ ከተማቸው የመታሰቢያ ሃውልት ቆመላቸው።

በምዕራብ ወለጋ ቦጂ ወረዳ፣ ቢላ ከተማ በ1929 ዓ.ም በተወለዱባት ከተማ ሃውልት ቆሞላቸዋል። በሃውልቱ ምረቃ ወቅት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የቢላ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሪነት እና ስነመለኮት እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ትልቅ አበርክቶት መዋላቸው ይታወሳል። በሃውልቱ ምረቃ ወቅት የጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን መሪ እና የቄስ ጉዲና ቱምሳ ልጅ ወ/ሮ ሌንሳ ጉዲና “ይህ ሃውልት ለትውልዱ፣ ስላለፈው በእውነት፣ ስለ ወደፊቱ ደግሞ ስለ ብርታት፣ በፍርሃት ፊት ስለ እምነት ይናገራል ብለዋል።”

ቄስ ጉዲና ቱምሳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ጠቅላይ ጸሃፊ ሆነው ያገለገሉ እና በደርግ ዘመን በግፍ የተገደሉ የቤተ ክርስቲያን መሪ ናቸው።
በኦቦሌሳ አዶላ - GTF እንዳስነበበው

23/04/2026

የምስራች! 👏

23/04/2026

ካንሰርን አሸንፈው ወደ ሥራቸው የተመለሱት
አምባሳደር ክብርት " - ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ እግዚአብሔርን አመሰገኑ! 👏

ሰሞኑን መነጋገሪያ የነበረው የተወዳጁ ዘማሪ ሳሙኤል ኦዳን ጉዳይ ነበር፤ይሄ ዘማሪ በተለይ በ90ዎቹ ከተነሱ ድንቅ ዘማሪያን መሀከል ስሙ ይጠቀሳል ወደ ሶስት የሚደርሱ የመዝሙር አልበሞችን ለቤ...
22/04/2026

ሰሞኑን መነጋገሪያ የነበረው የተወዳጁ ዘማሪ ሳሙኤል ኦዳን ጉዳይ ነበር፤ይሄ ዘማሪ በተለይ በ90ዎቹ ከተነሱ ድንቅ ዘማሪያን መሀከል ስሙ ይጠቀሳል ወደ ሶስት የሚደርሱ የመዝሙር አልበሞችን ለቤተክርስቲያን አበርክቶአል! በህዝብ ዘንድ ከሚታወቁ መዝሙሮቹ መሀከል 👉 ፍቅር የተሞላ እዉነተኛ
ወረት የማያዉቀዉ እዉነተኛ
ስከዱ ማትከዳ እዉነተኛ
እታመንሃለሁ ታማኝ ነህና፤ ሌሎች በርካታ መዝሙሮች አሉት! ነገር ግን ላለፉት ረጅም አመታት በአሜሪካ እንደሚኖርና በህመም ምክንያት ከሚዲያና ከአገልግሎት ርቆ መቆየቱን ሰምተናል፤አሁን ጤናው ተመልሶ አራተኛ የመዝሙር አልበም ለመስራት ኢትዮጵያ በመጣበት ሰአት አንድ ቤተክርስቲያን ተገኝቶ ያለ እርሱ እውቅናና ፍላጎት በተለቀቀበት ቪዲዮ ልቡ ማዘኑን ገልፆአል!
ሁላችንም በተለይ እኛ አማኞች መፈላለግ የት ጠፋ የት ጠፋች ምን ላይ ነው ያለችው/ያለው መባባልን ዋና ስራችን ማድረግ ይኖርብናል
Via አምልኮ ቲዩብ

22/04/2026

ኢየሱስ ጌታ ነው! 👏

22/04/2026

አምንሃለሁ! 👏

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሃሌሉያ Christian Media Network-HCMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሃሌሉያ Christian Media Network-HCMN:

Share