Gspel Army Media

Gspel Army Media ለድጋፍ ይህን ይጠቀሙ 1000578951157
ESKINDIR ENDIRAS ANJULO I Am Pastor
(1)

24/08/2026

ጴንጤ ምን አይነት ሠለማዊ
ሕዝብ ነው ግን ?

“ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ”  — ማቴዎስ 5፥12
22/08/2026

“ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ”
— ማቴዎስ 5፥12

ከታዳሚዎች ብዛት የተነሳ "ጠጠር መጣያ የጠፋበት" የተባለዉ ታላቁ የዚምባብዌ ወንጌል አማኞች መንፈሳዊ ኮንፍራንስ በምስል
22/08/2026

ከታዳሚዎች ብዛት የተነሳ "ጠጠር መጣያ የጠፋበት" የተባለዉ ታላቁ የዚምባብዌ ወንጌል አማኞች መንፈሳዊ ኮንፍራንስ በምስል

አዲስ የውድድር ዘመን። ያው ኢየሱስ። ❤️‍🔥 ቡካዮ ሳካ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ጎል አስቆጥሮ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጸለየ።እግርኳስ ተጫዋቾች በጌታ ገፅ
22/08/2026

አዲስ የውድድር ዘመን። ያው ኢየሱስ። ❤️‍🔥

ቡካዮ ሳካ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ጎል አስቆጥሮ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጸለየ።

እግርኳስ ተጫዋቾች በጌታ ገፅ

የአሜሪካ ጦር ዋና ፀኃፊ ፕተ ሄግሰት በካምፕ ተገኝተዉ ለወታደሮች ፀለዩ::
21/08/2026

የአሜሪካ ጦር ዋና ፀኃፊ ፕተ ሄግሰት በካምፕ ተገኝተዉ ለወታደሮች ፀለዩ::

21/08/2026

ፈልጋችሁት ! አጣሁ ያላችሁት ነገር በፍጥነት ወደ እናንተ መጣ !

 #አንድ ሶቅራጠስ የተባለ ሰዉ ነበር ።አንድ ቀን በጣም የሚቀርባት ልጅ እንዲህ ትለዋለች ጎደኛህ ጥሩ ነገር አላረገም ፤ ከሱ የማይጠበቅ ነገር ነዉ የሰራዉ ትላለች:እሱም ምን አገባኝ ታዲያ ...
21/08/2026

#አንድ ሶቅራጠስ የተባለ ሰዉ ነበር ።አንድ ቀን በጣም የሚቀርባት ልጅ እንዲህ ትለዋለች ጎደኛህ ጥሩ ነገር አላረገም ፤ ከሱ የማይጠበቅ ነገር ነዉ የሰራዉ ትላለች:እሱም ምን አገባኝ ታዲያ ብሎ ሊነሳ ሲል ቆይ አዳምጠኝ ብትሰማዉ ትገርማለህ ትለዋለች።

በዚህ ሰአት እንደማትለቀዉ ሲያዉቅ ሶስት ጥያቄዎችን ብቻ መልሽልኝና ልስማሽ ይላታል
የመጀመሪያዉ፦ስለጎደኛየ የምትነግሪኝ ነገር እዉነትነቱ የተረጋገጠ ነዉ? ምላሽ፦ አይደለም
ሶቅራጠስ ፦የምትነግሪኝ ነገር መልካም ነዉን?
ምላሽ፦አይደለም
ሶቅራጠስ ፦ለኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለዉን ?
ምላሽ፦የለዉም።
ሶቅራጠስ በመጨረሻም እዉነትነቱ ያልተረጋገጠ፤መልካም ያልሆነ፤ለኔ የማይጠቅም ነገር አልሰማም አላት።

ወዳጆቸ እዉነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ መልካም ያልሆነና በሕይወታችን ላይ ጉልህ ሚና የሌለዉ ነገር ላይ ጊዜን ማባከን ትልቅ ብክነት ነዉ።አንዳንዶች በማይመለከታቸዉ ነገር እድሜያቸዉን ይገፍሉ። በዚህም መመለስ የማይችሉትን ዉድ ጊዚያቸዉን ያጣሉ።በጎ አላማ በሌለዉ እዉነቱ ባልተረጋገጠና አንዳች ፍይዳ በሌለዉ እንቶ ፈንቶ ሳንባዝን ለሚጠቅም ነገር፣ ለሠናይና ለእዉነት እንትጋ።ካነበብኩት ላይ የተፃፈ።

እግዚአብሔር ከወሬኛ ሰዎች ይሰዉረን 🤗🤭🙏

ለትውልድ ስለምታደርገው ነገር ከልብ እናመሰግንሃለን። የምንናገረው ቃል የለንም፤ ስለ አንተ እግዚአብሔር ይመስገን! 🙏❤️እስክ አመስግኑ
19/08/2026

ለትውልድ ስለምታደርገው ነገር ከልብ እናመሰግንሃለን።
የምንናገረው ቃል የለንም፤ ስለ አንተ እግዚአብሔር ይመስገን! 🙏❤️

እስክ አመስግኑ

📱ከዲጂታል ጫጫታ ወደ እግዚአብሔር ቃል! 📖✨​በዘመናችን ስማርት ስልኮች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ ጊዜያችንን ይወስዳሉ። እኛ ቴክኖሎጂን ልንጠቀምበት ሲገባ፣ ሳናስበው እሱ ተቆጣጥሮን ይሆን...
19/08/2026

📱ከዲጂታል ጫጫታ ወደ እግዚአብሔር ቃል! 📖✨

​በዘመናችን ስማርት ስልኮች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ ጊዜያችንን ይወስዳሉ። እኛ ቴክኖሎጂን ልንጠቀምበት ሲገባ፣ ሳናስበው እሱ ተቆጣጥሮን ይሆን? 🤔

​የእግዚአብሔር ቃል ግን ውስጣችንን ከተከማቸው አላስፈላጊ የዓለም ጫጫታ የማጽዳት እና አእምሯችንን የማደስ ትልቅ ኃይል አለው!
​እነዚህን 3 የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎች ዛሬ እናስታውስ፦

​ 1. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም (ኤፌሶን 5፡15-16)፦
"ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ጊዜውን በሚገባ ተጠቀሙበት።" ቴክኖሎጂን ለበጎ ዓላማ እንጂ ጊዜያችንን እንዲሰርቀን አንፍቀድ።

2. ልብን መጠበቅ (ምሳሌ 4፡23)፦
"የሕይወት ምንጭ ከእርሱ ነውና አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ።" በየቀኑ የምናየውና የምንሰማው ነገር ማንነታችንን ስለሚቀርጽ፣ አእምሯችንን በበጎ ነገሮች እንሙላ።

3. በአእምሮ መታደስ (ሮሜ 12፡2)፦
ዓለማዊ ጫጫታዎችን (likes, views, shares) ወደ ጎን ትተን ውስጣችንን በቃሉ እናድስ።

​💡 የዛሬው ውሳኔ፦ በቀን ውስጥ ከኢንተርኔት እና ከስልክ ርቀን መጽሐፍ ቅዱስ የምናነብበት እና ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የተወሰነ ሰዓት እንመድብ!

​👇 እናንተስ በቀን ውስጥ ስልክ አጥፍታችሁ የምታሳልፉት የተወሰነ ሰዓት አላችሁ? እስኪ ልምዳችሁን ኮመንት ላይ አካፍሉኝ!

​ሼር

⭐️⭐️⭐️የቀኑ የግጥም ግብዣ⭐️⭐️⭐️*ሳይፀልዩ ማደር*******የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታሚዳቋ ፀለየች...."አውጣኝ አውጣኝ" አለች - ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦወደ አምላኩ ቀርቦሚዳቆ...
15/08/2026

⭐️⭐️⭐️የቀኑ የግጥም ግብዣ⭐️⭐️⭐️
*ሳይፀልዩ ማደር*******
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች - ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደጠጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
የሁለቱን ማብላት - የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታ ጠላት"
ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት
ምግብህ አርገህ ብላት
" ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር
አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ
ሼር

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913454358

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gspel Army Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Gspel Army Media:

Shortcuts

Share