Lij Muluneh Abraham

Lij Muluneh Abraham በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ሰለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።
ኤርም?

20/07/2023
10/10/2021

ዓይኖቹን አንስቶ
አንተን የጠበቀ አሃሃ
አንተን የጠበቀ
መቺ እንዲሁ ይቀራል
ትጎበኘዋለህ አሃሃ
ትጎበኘዋለህ

23/04/2021

እግዚአብሔር ተዋጊ ነው

07/04/2021

የያዘኝ እጁ ነው

07/03/2021

እለሰንቾ አጥሴ

18/12/2020

መዳን በሌላ በማንም የለም
➛በልጁ በኢየሱስ በቀር

''በፍፁም ልብህ በእግዚአብሔር ተመን የልብህን መሻት ይሰጣል''
17/12/2020

''በፍፁም ልብህ በእግዚአብሔር ተመን
የልብህን መሻት ይሰጣል''

11/12/2020


➛❶እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥
➛እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
➛❷የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደሰ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ።
➛❸ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥እንደ በላ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራለሁ።
➛❹ በአንድ አካል ብዙ ብልቶችእንዳሉን፥
➛የብልቶቻቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥
➛❺ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥
➛ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
➛❻ እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤______

25/10/2020

ክርስትያናዊ ጋብቻ
የትዳር ጓደኛ እንዴት እንምረጥ?

የሕይወት ጓደኛ ምርጫ መስፈርቶች
ትዳር ምስረታ ማሰብ ሲጀመር፣ ትዳር እንዲጸና ማድረግ የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሰብዓዊ መስፈርቶች መኖራቸው ቸል ሊባል የሚገባው ነጥብ አይደለም፡፡ ጋብቻ መለኮታዊም ሰብዓዊም ተቋም እንደ መሆኑ መጠን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኆዎችና፣ ሰብዓዊ ተሞክሮዎች፣ ቋሚና ዘላቂ መመሪያዎች እንዲሁም አላፊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተገናዝበው የሚተገበሩበት ሲሆን፣ ምንጊዜም ቢሆን ለመለኮታዊው፣ ዘላቂና ቋሚ ለሆነው መስፈርት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል፡፡

1. ምርጫው በውስጣዊ ማንነት እንጂ ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ እንዳይመሰረት መጠንቀቅ፣
ምንም እንኳ ውጫዊ ውበት ወይም ነገሮች በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ያላቸው መሆኑ ባይካድም፣ ውስጣዊ ውበት፣ የአስተሳሰብ ቁንጅና፣ በእምነት የተሞላ ቅንና ሩህሩህ ልብ፣ እንዲሁም ሙያ የላቀ ትኩረት ሊሰጣቸው ወይም ተመዛዝነው ሊታዩ ይገባል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበታቸውን መንከባከብ ላይ ብቻ ለሚያተኩሩ አማኝ እህቶች ሲመክር “…ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣…” ካላቸው በኋላ የላቀውን ነገር ሲያመለክታቸው “…ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ …” በማለት የትኩረት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ያሳባቸዋል (1ጴጥ.3፡3-4፤ )። ይህ ምክር ለወንዶችም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ለጋብቻ የታሰበው ወንድ ወይም የተመረጠችው ሴት አማኝ መሆኑን/ኗን ማረጋገጥ
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ቃል ኪዳናዊ ግንኙነት እንደ መሆኑ መጠን መከናወን ያለበት አማኝ በሆኑ ተቃራኒ ጾታ ባላቸው ሁለት ግለሰቦች መካከል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ “… ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? …” በማለት የሚያቀርበው ሙግት በተለይ ከጋብቻ አንጻር በጥልቀትና በጥሞና ሊታይ የሚገባው እውነታ ነው (2ቆሮ.6፡14-16) ፡፡

3. የወደፊት ተጣማጆች ልብ ዝንባሌ መሰረቱ እውነተኛ ፍቅር እንጂ የሌሎች ነገሮች ግፊት እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
በተቃራኒ ጾታዎች መካከል መሳሳብ፣ መፈላለግ መኖሩ ተፈጥሯዊ ጉዳይ በመሆኑ አንዱ ሰው ሌላውን ማፍቀር ኃጢአት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለጋብቻ ሲታሰብ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ በእርግጥ ይህን/ይህቺን ሰው እወደዋሁ/እወዳታለሁ? የሚለው እንጂ፣ ምን አለው? ከማን ወገን ነው? …ወዘተ ሊሆን አይገባም፡፡

ይህን ጉዳይ አውጥቶ አውርዶ የመወሰን ግላዊ ነጻነትን የሚጋፉ አያሌ ልምዶች ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መኖራቸው እሙን ሲሆን፣ ውጤታቸውም አስከፊ ነው፡፡ ከነዚህም ምክንያቶች መካከል የፍቅር ግንኙነቱን ከሚፈልጉት አንዱ “እግዚአብሔር አንቺን/አንተን ሰጥቶኛል” ብሎ ጥያቄ ማቅረብ፣ አንዳንድ ነቢያት ነን ባዮች “አከሌን/እከሊትን እንድታገቢ/እንድታገባ እግዚአብሔር ተናግሮኛል” ሲሉ የሚያመጡት አሳሪ መልዕክት፣ እንዲሁም
ማንም ሰው የፍቅር ስሜት የሌለውን ሌላ ሰው አግብቶ ሰላም ያለበት፣ የተረጋጋና የእግዚአብሔር በረከቶች የሚከተሉት ኑሮ መሥርቶ መኖር ስለሚቸገር ራስን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሥራ መጥመድ ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት ውስጥ ዘሎ ከተገባ በኋላ ችግሮች ውሎ አድሮ መከሰት ሲጀምሩ “እግዚአብሔር እንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ስገባ ለምን ዝም አለኝ?” ብሎ ለማማረር መሞከር ስሜት ሊሰጥ የማይችል ቂልነት መሆኑን መገንዘብና ኃላፊነቱን መውሰድ ግድ ይላል፡፡

4. ብስለትና ዝግጁነትን መመዘን
ጋብቻ ቤተሰባዊ ኑሮን ለመመሥረት ሕጋዊ የመግቢያ በር ስለሆነ ቀጣዩን ኃላፊነት ወስዶ ለመኖር ከሚያስችለን ሁለንተናዊ ብስለት ደረጃ ላይ እንገኛለን? ብሎ ራስን መጠየቅና ሁኔታዎችን መመዘን ብልህነት ነው፡፡ ብስለት አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ገጽታዎችን ሊያጠቃልል የሚችል ሲሆን፣ ሁለት ከተለያዩ ጾታዎች፣ ጀርባ ታሪኮች፣ አመለካከቶች፣ እውቀት ደረጃ፣ የአስተዳደግ ባሕል የመጡ ሰዎች የጋራ ጎጆ ቀልሰው አንድ ሥጋ ሆነው አብረው ለመኖር ሲጣመሩ ያስተሳሰራቸውን ጽኑ ፍቅርና እነዚህን ልዩነቶች አጣጥመው ወደፊት ለመራመድ ብስለት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እርስ በእርስ እየተናበቡ ፍቅርን ለመለዋወጥ፣ የአንዱ ብርታት የሌላውን ድካም እየሸፈነ የሚመች ረዳት የመሆን ሚናውን ለመወጣት ዝግጁ መሆን ከእያንዳንዱ የትዳር አጋር ይጠበቃል፡፡ እንዲህ ሲባል ግን ፍጹምነትን መጠበቅ ይኖርብናል ማለት አይደለም።

✍ እግዚአብሔር ያንተ ያንቺ ከሆነው ጋር ያገናኛቹ 🙏

18/10/2020

ኪዳኑን አስብ 🙏🙏🙏🙏🙏

Address

Ulundi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lij Muluneh Abraham posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share