13/07/2026
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልግስና ከተረዳን ማንንም የመለወጥ ሃይል አለው። ይህ ወጣት መጋቢ (Pastor) ስለ ልግስና ከዚህ በፍት የነበረውን መረዳት አሁን እየወሰደ ካለው (Theology of generosity) ፈጽሞ እነደቀየረውና እውነተኛ መረዳት መድረሱ ከአንደበቱ ሰምተናል። ከህግ ፣ ከግዴታ፣ እና ብሰጥ መልሼ አገኛለሁ ከምል አስተሳሰብ የጸዳ እና የእግዚአብሔርን ባህሪይ በማንጸባረቅ እለት ተእለት ከሕይወታችን የሚመነጭ የፍቅርና የርህራሄ አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር ራሱ የለጋሰልን:-
1) አምሳሉን
2) እስትንፋሱን
3) የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ
4) ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። በመሆኑም ልግስና የእግዚአብሔር ባህሪይ መሆኑን በመረዳት አሁን ያለውን የአለምን እጦት እና የሰው ልጆችን የእጦት መከራ ማሸነፍ የምንችለው በምንም የማይገደበውን የእግዚአብሔርን ባህርይ በመጋራት ለሌሎች በረከት እንድንሆን የክርስቶስ ፍቅር ግዴታ አለብን።
ተባረኩ።