Elias Girma Pastor

Elias Girma Pastor Pastor

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ....መንፈስ ቅዱስ 🔥🔥🔥🙏ትላንት ከእርሻ መጥቶ ያለ ውጊያ ልምድ በሬዎችን ቆራርጦ ለጦርነት ነጋሪት ጎስሞ ጠላትን ድባቅ መትቶ ከተማይቱን ያዳነው ብንያማዊው ሳኦል  ዛሬ ...
10/06/2026

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ....መንፈስ ቅዱስ 🔥🔥🔥🙏

ትላንት ከእርሻ መጥቶ ያለ ውጊያ ልምድ በሬዎችን ቆራርጦ ለጦርነት ነጋሪት ጎስሞ ጠላትን ድባቅ መትቶ ከተማይቱን ያዳነው ብንያማዊው ሳኦል ዛሬ ከቤተመንግስት ወጥቶ፣ ተደራጅቶ፣ ልምድ ዝና እያለው በፍርሃት የራደው አልፎም ጠላትን የሚጥልለትን ማፈላለግ የተያያዘው ለምንድነው?

ካልን መልሱ ቀላል ነው ያኔ ያጀገነው የወረደበት መንፈስ ዛሬ ስለራቀው እንደሆነ በእነዚህ ክፍሎች መረዳት እንችላለን። (1ሳሙ 11:6፣ 16:14 ምዕ 17)
የትላንቱን ድል ዛሬም ለመድገም በመንፈስ ከመሞላት ውጪ ምን አማራጭ አለን? እንደ ሳኦል የሚጥልላችሁን በማፈላለግ እደጅ እደጁን የምታዩ ወዳጆቼ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ነውና በእኛ ለእኛ እኛን እንዲሠራ ዕድል እንስጠው።

ሌላኛው ብንያማዊው ሳውል ሐዋርያዊ ተልዕኮውን "ሀ"ብሎ ከአንጾኪያ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አብያተ ክርስቲያናትን ከተከለ፣ "አማልክት ሰዎችን መስለው ወርደዋል" እስኪባሉ ምልክትና ድንቅ በእጆቹ ከተደረገ በኋላ

እንደ ቀድሞው የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ ለመስማት፣ ለመመራት የተዘጋጀ ልብ ነበረው።
በሁለተኛውም ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ ወደ እስያና ወደ ቢታንያ መንፈስ ቅዱስ እንዳይሄዱ ሲከለክላቸው ወደ ሜቅዶንያ እንዲሄዱ ሲልካቸው ለእርሱ ለመታዘዝ አልተቸገሩም።(ሐዋ 13 እና ሐዋ 16)። ከብዙ ስኬትና ድል በኋላም ያኔ ውጤታማ ባደረጋቸው በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንጂ በልምምዳቸው አይታመኑም ነበር።

አደጉለት እንጂ አላደጉበትም። ልጅ ሲጎረምስ ለያዥ ለገራዥ የሚያስቸግርበት ጊዜ ይኖራል ልክ ከአባቱ ባገኘው ነገር ያለአባቱ መኖር እንደሚችል አስቦ ከስሮ እንደመጣው የጠፋው ልጅ (ጎረምሳው)
አለችኝ በምንላት ነገር ማካበዱን ትተን ለመንፈስ ቅዱስ ቀለል ብለን ለመላክ እንደግለት እንጂ አንጎርምስ ለማለት ነው።

ከትዝታ ማሕደርየዛሬ 16 ዓመት የወጣው በሰማያት የሚለው መጽሐፍ ከያዛቸው ርዕሶች መካከል ጸሎት... በአባትና በልጅ መካከል ያለ ግንኙነትጸሎት... የሰላም ዋስትናጸሎት... ከእግዚአብሔር ጋ...
16/05/2026

ከትዝታ ማሕደር

የዛሬ 16 ዓመት የወጣው በሰማያት የሚለው መጽሐፍ ከያዛቸው ርዕሶች መካከል

ጸሎት... በአባትና በልጅ መካከል ያለ ግንኙነት
ጸሎት... የሰላም ዋስትና
ጸሎት... ከእግዚአብሔር ጋር የመሥራት ዕድል
ጸሎት... የኃይል መንገድ

👉...የተሳሳቱ የጸሎት ልምምዶች

💢..እግዚአብሔርን በጸሎት የማስገደድ ሁኔታ
💢...በሰዎች ላይ የሚደረግ ጸሎት
💢...የአህዛብ አይነት የጸሎት ልምምድ
💢..የሐይማኖተኞች የጸሎት ልምምድ
👉..እንጸልይ ዘንድ አስተምረን እና ሌሎችም

የዛሬ 12 ዓመት ደግሞ የቤቱ መልክ የሚለው መጽሐፍ ከያዛቸው ጥቂቶቹ

🤔...ታላቅ ሚስጥር
🤔...ጸጋ
🤔...መስቀል
🤔..ከኃጢያት አርነት
🤔...ከሕግ አርነት
🤔...አዕምሮ

✍️..የዚህ ዓለም መልክ
✍️...የሐይማኖት መልክ
✍️...የሰይጣን መልክ
✍️...አዳማዊ መልክ
✍️...የልጁ መልክ
✍️...ልደትና እድገት
✍️...የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ዓላማ
✍️...ተስሎ ነበር…እስኪሳል ድረስ
✍️...በመንፈስ ተመላለሱ

11/04/2026

እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።
"... ስለ ኃጢአታችን

ሞተ፥ ተቀበረም ... ተነሣ"(1ቆሮ 15:3-4)

መስቀሉ በደሙ ቀለም ፍቅር የተፃፈበት ሰሌዳ ነው

መስቀሉ የእግዚአብሔር ፍቅር የተብራራበት ህያው መፅሐፍ

በመንፈሳችን ላይ የተነቀስነው፣ በዓይነ ህሊናችን

ተሰቅሎ የተሳለው፣ ለዚህ ዓለም የመነንበት፣

ወደ ፍቅሩ ገዳም የፈለስንበት የእግዚአብሔር የማዳን

ጥበብ፣… ያለነገረ መስቀሉ ነገረ ክብሩ የለም 👑

ደግሞም.. "መስቀሉን ሳስብ መስቀሌን እረሳለሁ! "

ባለፉት ሦስት ቀናት በLebowakgomo በእግዚአብሔር ምሕረት መልካም ጊዜ አሳልፈናል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።
29/03/2026

ባለፉት ሦስት ቀናት በLebowakgomo በእግዚአብሔር ምሕረት መልካም ጊዜ አሳልፈናል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

25/03/2026

"... ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። (1ሳሙ17:36)

ይህንን ዘመቻ ተቀላቀሉ !!! ! የዚህን እንቅስቃሴ መነሻ ሃሳብ አካፍሎን በማስተባበር ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ገርጂ አማኑኤል መጋቢ  የሆነው ዘርዬ ነው። የምር ለሚጋደሉ የክርስቶስ ኢየሱ...
16/03/2026

ይህንን ዘመቻ ተቀላቀሉ !!!

!



የዚህን እንቅስቃሴ መነሻ ሃሳብ አካፍሎን በማስተባበር ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ገርጂ አማኑኤል መጋቢ የሆነው ዘርዬ ነው።

የምር ለሚጋደሉ የክርስቶስ ኢየሱስ ወታደሮች ትጥቅ በማቀበል ውስጥ የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ የቀረበ ጥሪ ነው።

ለዚህ በጎ ሥራ እኔ አለሁ የሚል ከታች ባለው አድራሻ ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላል።
እግረ መንገዳችንን ግን በየቦታው በእውነት የሚያገለግሉትን በገጠር ከተማ ያሉትን ቤታቸውንም እንድናይና ፍቅራችንን እንድንገልጥላቸው ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ስንቅም እንድናቀብላቸው ቢሆን ጥሩ አይመስላችሁም?

ይህንን ዘመቻ ተቀላቀሉ። ፓስተር ዘርዬና ገርጂ አማኑኤል እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

ለበለጠ መረጃ:
📞 0924894242
📞 0965659465
📧 [email protected]

 ! መጻሕቱን በማድረስ ከአገልጋዮቻችን ጋር እንቁም።
13/03/2026

!

መጻሕቱን በማድረስ ከአገልጋዮቻችን ጋር እንቁም።

ያለፉት ሦስት ቀናት በእግዚአብሔር ምሕረት መልካም ጊዜ አሳልፈናል።
09/03/2026

ያለፉት ሦስት ቀናት በእግዚአብሔር ምሕረት መልካም ጊዜ አሳልፈናል።

ዘወትር ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ አድራሻ፡173 Queen.StKensington Johannesburg 2094,New Life Church
04/03/2026

ዘወትር ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ
አድራሻ፡173 Queen.St
Kensington Johannesburg 2094,New Life Church

07/02/2026

ዛሬ ማለዳችንን ያሳመረ፣ ከባለቤቴ ጋር ያመለክንበት ድንቅ የአምልኮ ዝማሬ። ተባረኩበት። ዘማሪዎቹ ደግሞ የኔ ቤተሰቦች ናቸው። (ቲሽዬ ይህን መዝሙር ስለላክሽልን ተባረኪ።)

Address

Webber Road
Johannesburg

Telephone

+27843684968

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Elias Girma Pastor posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Elias Girma Pastor:

Share