Workageny Page

Workageny Page therefore nothing!!!

እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው ? እግዚ_አብ_ሔር ማለት።
01/02/2026

እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው ?
እግዚ_አብ_ሔር ማለት።

ኦርቶዶክስ ድሮም ልክ ናት!"ኦርቶዶክሳዊያን ዛሬ ላይ የሚሞቱት ትላንት አባቶቻቸው በሰሩት በደል ነው" ያለውን በግዋሻውን እስኪ እንጠይቀው።ለመሆኑ ቅዱሳን ሐዋሪያት፣ ቅዱሳን ጻድቃን እና  ቅ...
05/11/2025

ኦርቶዶክስ ድሮም ልክ ናት!

"ኦርቶዶክሳዊያን ዛሬ ላይ የሚሞቱት ትላንት አባቶቻቸው በሰሩት በደል ነው" ያለውን በግዋሻውን እስኪ እንጠይቀው።

ለመሆኑ ቅዱሳን ሐዋሪያት፣ ቅዱሳን ጻድቃን እና ቅዱሳን ሰማዕታት ስደትን መከራን እና ሞት ሁሉ የተቀበሉት ትላንት ከእነሱ በፊት አባቶቻቸው በሠሩት ጥፋት ወይም በደል ነውን?

ለዚህ ነው ለወንጌል ገና ነህ የተባልከው።

እናንተንም ያወገዘችው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድሮም፣ ዘንድሮም፣ ወደፊትም ልክ ናት

05/11/2025
የአርሲው ጥቃት ሰለባ የሆነው ሕፃን ታምራት አውግቸው የቀኝ እግሩ ተቆረጠ።በወላይታ ሶዶ ከተማ  በሚገኘው ክርስቲያን ሆስፒታል ሲታከም የሰነበተው የአራት ዓመቱ ሕፃን  ታምራት አውግቸው፥ ዛሬ...
05/11/2025

የአርሲው ጥቃት ሰለባ የሆነው ሕፃን ታምራት አውግቸው የቀኝ እግሩ ተቆረጠ።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው ክርስቲያን ሆስፒታል ሲታከም የሰነበተው የአራት ዓመቱ ሕፃን ታምራት አውግቸው፥ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀትር ላይ በጥይት የተደበደበው እና የተመረዘው እግሩ ተቆርጧል።

የሆስፒታሉ ሐኪሞች እግሩ ሳይቆረጥ አሰፊላጊውን ሕክምና አድርገው ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም፥ አልተሳካም። ሕመሙ ለሕይወቱ አስጊ እየሆነ በመምጣቱ የተነሳ እግሩን ለመቁረጥ እንደወሰኑም ለማወቅ ተችሏል።

እግዚአብሔር አምላክ ምሕረቱን ይላክለት።

Via tadesse worku

+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? + (ጊዜ ወስደው ያንብቡት  አያጥር ነገር  ታሪክ ሆኖ ነው)አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለ...
17/06/2025

+ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? +

(ጊዜ ወስደው ያንብቡት አያጥር ነገር ታሪክ ሆኖ ነው)

አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡

በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡

ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦

‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡

ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡

ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡

‘’አባቴ ይባርኩኝ’

‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’

‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ

‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት

‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና

‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡

‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡

‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት

‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡

አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡

ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡

ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦

‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡

ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡

አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡

ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡

በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡

ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው

አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::

አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡

‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’

‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’

መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ውኃው ውስጥ ወረወርሁት፡፡

በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’

‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’

‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’

‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡

‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡

ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 24/ 2012 ዓ ም

/How God Judges People – The patristic heritage book 2 – /Elder Cleopa/ ከሚለው የዜና አበው መጽሐፍ የተተረጎመ/

ማስታወሻ ፦ ይህንን ታሪክ ትንሽ የሚመስለው ታሪክ በ1747 የተጻፈው የቮልቴር ዛዲግ ላይ አንብቤ የታሪኩ ሞራል ደስ ቢለኝም የዞራስትራኒዝም ነበርና ለቤተ ክርስቲያን አይሆንም ብዬ ነበር፡፡ ለካንስ ይህ ታሪክ አስቀድሞ በመነኮሳት ታሪክ የተመዘገበ ነበርና በዚህ መልኩ ከአራተኛውና አምስተኛው ክፍለ ዘመን ወርቃማ የምንኩስና ታሪኮች በአንዱ ተመዝግቦ አገኘሁት፡፡ ባየነውና በምናየው ሁሉ እንዳሻን የእግዚአብሔርን ፍርድ በምንደመድምና በምናብራራበት በዚህ የደፋር ዘመን እንዲህ ያሉ ታሪኮች ልጉዋም ቢሆኑ በሚል ተርጉሜዋለሁ/

ፎቶ :- ብፁዕ አቡነ አብርሃም ለኢየሩሳሌም ተጉዋዦች ጸሎተ ቡራኬ በአውሮፕላን ውስጥ ሲሠጡ ያነሣኹዋቸው::

ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ

12/02/2025
Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
24/01/2025

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

21/11/2023

ሕደረ ቅዱስ ሚካኤል ዋዜማ ከጆሃንስበርግ ጸረ ጽዮን መደኃኒዓላም ካተደራል

25/08/2023
My Fiance!To Be My Wife
26/06/2023

My Fiance!
To Be My Wife

02/04/2023

!!!

#ሰሞኑን በሕገ ወጥ መንገድ የጳጳስ ልብስ ለብሰው ጳጳስ በሉን እያሉ በመንግሥት ወታደሮች ክርስቲያኖችን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ አካላት በቤተ ክህነቱ ግቢ ማንዣበቡን ተያይዘውታል፡፡፡፡
ባለፈው የሐሰት እርቅ ስምምነት ጊዜም ጠቅላዩ ከእነዚህም መካከል የምትሾሙት ይኖራል በማለት ምክር መሰል ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡፡፡፡
ሲመተ ጵጵስና እንዴት?
የጵጵስና መሠረቶቹ ሐዋርያት ናቸው፤ ከሐዋርያት መካከል ክርስቶስን ካገኘ በኋላ ወደ ዓለም የተመለሰ ከይሁዳ በቀር አንድም ሐዋርያ የለም፡፡ መላ ሕይወታቸውን፣ መላ ዘመናቸውን የምሥራቹን ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ ለማዳረስ በመንከራተት፣ በጾም እና በጸሎት፣ በፍጹም ተጋድሎና ትጋት እየኖሩ ምእመናን በበዙባቸው አካባቢዎች ሁሉ ጳጳሳትን እየሾሙ በሰማእትነት አልፈዋል፡፡
የሹመት መሥፈርታቸውም እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥
ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።›› ማቴ፡ 10፥9
‹‹መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።›› ዮሐ፡ 10 11››
‹‹ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛውን ረብ የማይወድ፥ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤ ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።› ቲቶ 1፥7-10
‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።›› የሐ፡ ሥራ፡ 20፥ 28
‹‹‹ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጲስቆጶስ ሁኖ የሚሾመው የምእመናን ጠባቂ ነውር የሌለበት ንጹሕ እና ቸር፤ ለዚህ ዓለም የማይጨነቅ፤ ሃምሳ ዓመት የሞላው የወጣትነት ጊዜው ያለፈ፤ ነገረ ሠሪ ያልሆነ፤ በወንድሞች መካከል ሐሰትን የማይናገር ይሆን ዘንድ እንደሚገባው በጌታችን ዘንድ ሰማን፡፡›› ›› ዲድስቅልያ አንቀጽ 4 ቁ 1
ሕዝቡም የሚሾመውን ሰው በስሙ እና በመልኩ በጠባዩም ሊያውቁት ይገባል፡፡ ፍት ነገ 4፥72
‹‹በሚሾምባቸው ሕዝቦች እና በሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ ይሁን፤… ኤጲስቆጶስ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ በሕዝቡ ምርጫ ይሾም፡፡›› ፍት ነገ 5፥90
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሥርዓተ ሢመትን በዘርፍ በዘርፉ ማቅረብ አይደለም ከላይ ያየናቸው ሐሳቦች ለምናመጣው ሐሳብ መንደርደሪያ ናቸው፡፡
ኤጲስቆጶሳት_እናዳይካሔድብን
ከሕገወጦቹ ጳጳስ ነን ባይ ግለሰቦች እርቅ ጋር በተያያዘ ከመንግሥትም ከአባቶችም የሰማንው በሚመጣው ርክበ ካህናት ሢመት እንደሚካሄድ ነው፡፡
‹‹መንገድ የጠፋበት ሰው የመጀመሪያ እርምጃው ባለበት መቆም እና ስለመንገዱ መጠየቅ ነው›› ከዚያ ጉዞውን ይጀምራል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአጻዌ ኆኅት እስከ ፓትርያርክ ላሉት የክህነት ማዕርጋት የተሰነደ ሥርዓተ ሢመት ቢኖራትም ተግባራዊነቱ ግን እጅግ የወረደ ነው፡፡
1. ዲቁና የራሱ የሆኑ መሠረታዊ መስፈርቶች ቢኖሩትም አሁን ግን በታላላቅ አድባራት እና ገዳማት የንግሥ በዓላት የተገኘ እና ውዳሴ ማርያም አጥንቶ የተገኘ ሁሉ ያለ ምንም ምርመራ በገፍ ይሾማል፡፡ ከዚህ የተነሳ የቤተ ክርስቲያኗ አማኞች ያልሆኑት ጭምር ተሸመው የሚሄዱባቸው አጋጣሚዎች ሰፊ ናቸው፡፡
2. በቅስና በኩል ከሚቀድስበት ደብር ዳብዳቤ ያምጣ የሚል መመሪያ ቢተገበርም የዕውቀት መስፈርቱ ከኪዳን እና ከመስተብቁዕ ያላለፈ፤ ቢቻል ብሉያትን ሐዲሳትን አንብቦ የሚተረጉም፤ ያ ባይሆን እንኳን አራቱን ወንጌላት ንባባቸውን ከነትርጓሜያቸው የማያው ሰው ቅስና እንዳይሾም የሚለው ተግባራዊነቱ ተዘንግቶ ያችን የደብር ደብዳቤ ሰው በሰው አስጽፈው የመጡ ሁሉ ቅስና ተቀብለው ይሄዳሉ፡፡
3. አሁን የተነሳንበት ጉዳይ ሢመተ ኤጲስቆሳት በመሆኑ አንዳንድ ማሳያዎችን እንመለከት፡-
ከላይ በመግቢያ የተቀመጡት የመጽሐፍ ቅዱስ እና የቀኖና መጻሕፍት ጥቅሶች እንደሚነግሩን ኤጲስቆስ መላ ሕይወቱን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሰጠ መናኔ ዓለም ከፍቅረ ሢመት፣ ከፍቅረ ንዋይ፣ ከውዳሴ ከንቱ እና ከተድላ ዓለም፤ የግል ቤት ከመገንባት፣ የግል ገንዘብ ከማካበት የራቁ መሆን አለባቸው ይላል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የመጣው ሥርዓትም ይሄው ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን
1. የምእመናን ድርሻ እና ተሳትፎ የማይታይበት ሹመት መለመዱ
2. እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ጎሳን መሠረት ያደረገ ሹመት ተግባራዊ መሆኑ
3. ከመናንያን መኰሳት መሆኑ ቀርቶ ምናኔን ትተው ከተማ ከገቡ ግለሰቦች መካከል መመረጡ
4. በባለ ሥልጣናት ጣልቃ ገብነት፣ በሴት ወይዘሮ በወንድ መኰንን አማላጅነት፣ ገፋም ሲል በገንዘብ ጭምር የተድበሰበሰ ሹመት መሾም ከተጀመረ ዋል እድር ብሏል፡፡ የሰሞኑ ግርግርም የዚያ ስህተት ውጤት ነው፡፡
ስለዚህ በመጭው ግንቦትም ሢመት ለማካሄድ መታሰቡ ጥፋቱን ከመድገም ያለፈ ሌላ ረብ ጥቅም የለውም ባይ ነኝ፡፡
ምክንያቱም
1. የቀጣዩ ሹመት ፖለቲካዊ ጫና ያለበት እና ብሔር ተኮተር እንደሚሆን ጭምጭምታዎች መሰማታቸው
2. ሰሞኑን በፍቅረ ሢመት ጦር ተወግተው ከወደቁ ሰዎች መካከል ሹመት እንዲካሄድለት መንግሥት መፈለጉ እና በፈጸሙት በደል እንዲሁም የቀኖና ጥሰት ምክንያት ከነዚህ መካከል አንድ እንኳ ለሢመት የሚበቃ ሰው አለመኖሩ፤ (በፍቅረ ሲመት የተወጋ ደማቸው ሳይደርቅ፣ ትዕቢታቸው ሳይርቅ ጥፋታቸውን ሳያምኑ ከቁምስና እስከ ዲቁና የነበረው ክህነታቸው ተሸሮ እንኳን በድፍረት ቤተ መቅደስ የገቡ ሰው ያስጨፈጨፉ በመሆናቸው ምክንያት)
3. በየጓዳው እና በየሰፈሩ የምንሰማቸው የእኔን ሹሙኝ እና የሹሙልኝ ሽኩቻ በእጅግ በመጨመሩ፤
4. የቤተ ክርስቲያኗ መሠረታዊ ችግር የጳጳሳት እጥረት ባለመሆኑ (ብፁዓን አበው በአንደበታቸው ዓመቱን ሙሉ ወደ ሀገረ ሰብከቱ የማይሄድ ጳጳስ እነዳለ ሲናገሩ ሁላችንም ሰምተናል)
5. ከላይ የተጠቀሱት ከዲቁና ጀምሮ እስከ ፕትርክና ያሉት ያልተከበሩ ሥርዓታት እስኪከበሩ እና ለተገቢው ክህነት ተገቢው ሰው የሚሆንበት የአፈጻጸም መመሪያ እስኪሠራ ድረስ፤
6. ሢመቱ ከተካሄደም ለቤተ ክርስቲያን ተጨማሪ ችግር እንደ መጨመር በመሆኑ እና ከመናንያን ገዳማውያን መነኰሳት የመምረጥ ዝንባለው ጨርሶ ስለጠፋ፤ በምንም መሥፈር ሢመት መካሔድ የለብንም፡፡
ችግሩ ጎልቶ የታያችሁ ብፁዓን አባቶች፣ የገዳማት አበ ምኔቶች፣ የአብነት መምሀራን፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ ምእመናን በሙሉ ከዚህ በኋላ ተጨማሪ የምናማው አባት እንዲሾም አንፈልግም በማልት ቤተ ክርስቲያናችን እናስከብር፡፡
#በመምህር አምላክ የቀጣዩ ሢመት ይዘግይልን፡፡
መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ
መጋቢት 21/ 2015 ዓ ም

Address

73 Troye Street
Johannesburg

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Workageny Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Workageny Page:

Share