Durban apostolic Church

Durban apostolic Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Durban apostolic Church, Religious organisation, Durban.

18/04/2026

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፡— ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፡— እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥

ማር 12:29

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት በቴክርስቲያን በጋሞ ዞን በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች አርባ ምንጭ ሚያዝያ  8/2018 ዓ.ም. (ጋሞ ቴሌቪዥን)የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት...
18/04/2026

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት በቴክርስቲያን በጋሞ ዞን በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች

አርባ ምንጭ ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ም. (ጋሞ ቴሌቪዥን)

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ለጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ተጎጁዎች ሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።

ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት በቤቴክርስቲያኗ ሀገረ ስብከት ምክትል አስተዳዳሪ ቢሾኘ ጌታሁን ላምቤቦ የተመራ ልዑክ ነው።

ምክትል አስተዳዳሪው በተከሰተዉ አደጋ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ቤቴክርስቲያኗ የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በፀሎቷ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗንም አስረድተዋል።

የቤተክርስቲያኗ ወንጌላዊ ደረጀ ከበደ በበኩላቸው አደጋው አሳዛኝ መሆኑን ገልፀው ለተጎዱ ወገኖች መፅናናትን ተመኝተዋል።

እርስ በርሳችን መረዳዳት የክርስትና ተግባር መሆን አለበት ሲሉ አስረድተዋል።

የቤቴክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ቢሾፕ ብርሃኑ ጅጅጎ የጋሞ ማህበረሰብ አስታራቂና ሰላም ፈላጊ መሆኑን ገልፀው በተፈጠረው አደጋ እጅጉ ማዘናቸውና ለዘላቂ መፍትሄ እንደሚተባበሩ ጠቁመዋል።

የአርባ ምንጭ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ቢሾኘ ከበደ ጋሻዉ በበኩላቸዉ የጋሞ የሰላም የፍቅርና የጥበብ ሕዝብ መሆኑን ገልጸዉ ይህ አደጋ ተፈጥሮአዊ ሆኖ የመጣ እንጂ የሚገባዉ አልነበረም። በተከሰተዉ አደጋ እጅግ ማዘኑን ገልጸዉ ቤተክርስቲያኗ ሁሌም በአስፈላጊዉ ጊዜ ከመንግስት ጎን እንደሚትሆን ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ተስፋፅዮን ዘነበ በበኩላቸው አደጋው ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ድጋፍ ላደረጉና ላፅናኑ ምስጋና አቅርበቀዋል።

ለአደጋው ተጎጂዎች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የሁሉም ተሳትፎ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

24/01/2025
ዕዳ ይዞ መኝታ፥       የዋጋው ክፍያ እጅግ ይከብዳል!!!የተሰጠንን ይህን ወርቃማ ጊዜ እንጠቀምበት    ቀን ሳለ በብርኃኑ መመላለስ ይሻላል!!!ራስን ማየት መፈተሽ፦ከምንም ምንም በፊት!!...
12/12/2020

ዕዳ ይዞ መኝታ፥
የዋጋው ክፍያ እጅግ ይከብዳል!!!

የተሰጠንን ይህን ወርቃማ ጊዜ እንጠቀምበት
ቀን ሳለ በብርኃኑ መመላለስ ይሻላል!!!

ራስን ማየት መፈተሽ፦
ከምንም ምንም በፊት!!!

♠ኃጢያቱን የሚሸፍን!!አይለማም♠፤
የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል።

፨ሁልጊዜ የሚፈራ ሰው ምሥጉን።ነው፤
፨ልቡን የሚያጸና ግን በክፉ ላይ ይወድቃል
ምሳ 28÷13-14፥

፨መባህን ከመሰውያ ላይ ከማስቀመጥህ በፊት ከወንድም ጋር ፨አንዳች፨ቢኖርብህ
አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ!!!።
ማቴ 5÷23

ለጸሎት በቆማችሁ ጊዜ በሰማያት ያለው
አባታችሁ ♥ይቅር እንዲላችሁ♥፤
፨♥በማንም ላይ አንዳች♥፨
ቢኖርባችሁ ፨ይቅር፨በሉ።
እናንተ ግን
ይቅር ባትሉ!! በሰማያት ያለው አባታችሁ
♠ኃጢያታችሁን♠
ይቅር አይደላችሁም።
ማር11÷25-26

የልብ መዙጋጀት ከሰው ነው፤
የምላስ መልስ ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ምሳ16÷1 አሜን
MB.

Address

Durban

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Durban apostolic Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share