Apostolic Church of Rustenburg South Africa

Apostolic Church of Rustenburg South Africa we only baptize in the name of jesus.

21/06/2026
21/06/2026

ተዘጋጅቶ ያለመጠበቅ ጉዳቶች



👉🏾መዘጋጀት ስንል በራሱ ከሆነ አደጋ ከሚመጣው አስከፊ ከሚሆን ነገር ለመትረፍ የሚያስፈለገው መስፈርት በመሙላት ዝግጅት ማደረግን ይመለከታል ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ተዘጋጅቶ ያለመጠበቅ ስለሚያስከትለው አደጋ በግልጽ ያስጠነቅቃል ብዙ ምሳሌዎች ለእግዚአብሔር መንግስት አለመዘጋጀት የሚያከተለውን መዘዝ ያሳያሉ ።

በእግዚአብሔር ቃል ማቴዎስ 25:1_4 “በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።

በዚህ ቦታ የተጠቀሱ አሥሩም ለመዳን ከተጠሩት ናቸው ከእነዚህ አምስቱ ተዘጋጅቶ የሚጠብቁ እና አምስቱ ደግሞ ያልተዘጋጁ ናቸው ።

👉🏾ያልተዘጋጁ ሰዎች መጨረሻ ከዚህ በመቀጠል እናያለን

👉 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። “ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ’ አሉአቸው። ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ። “በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ‘ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን፡’ አሉ። እርሱ ግን መልሶ፦ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም፡’ አለ። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ማቴዎስ 25:5_13

👉🏾ወገኖች የመዘጋጀት ግዜ አሁን ነው ኢየሱስ ከመጣ በኃላ

👉 መዘጋጀት የለም

👉ፀሐይ ☀️ እና ጨረቃ ከጨለመ በኃላ

👉የ ምህረት በር ከተዘጋ በኃላ

👉 ሰማይ በኃይለኛ ትኩሳት ስቃጠል

👉 ይህ ምድር እንደ እርሾ ስቦካ መዘጋጀት የለም ።

ማንም ማዳን የማችል ቀን ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።

✍️ እናንተ እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፥ ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ትኵሳት ሳይመጣባችሁ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፥ ተከማቹም። እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፤ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።

ሶፎንያስ 2:1_3

እግዚአብሔርን ፈልጉ ምናልባት በቁጣ ቀን ትሰውሩ ይሆናል ይላል አሁን ተዘጋጁ እግዚአብሔርን ፈልጉ።

08/02/2026

ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ አትውሰድበኝ።

ይህ አነጋገር ዳዊት በፀሎት መንፈስ ከአምላኩ ጋር የተነጋገረበት ቃላት በመሆኑ ይታወቃል እኛም ዛሬ እንዲህ እንላለን:- ከፊትህ አትጣለኝ፥ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
መዝሙር 51:11

የሃማኖት ዋናው ክፍፍል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ አካል ናቸው የሚል እና አንድ ነው የሚል ስሆን የተለያዩ ናቸው የሚሉት መንፈስ ቅዱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው የራሱ አካል አለ የሚል አቋም ያላቸው ናቸው።

በዚህ ክፍል ዳዊት :-ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። ስል
1ኛ ማነው የመንፈሱ ባለቤት የምወስደው ?
2ኛ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ይወስዳል ?

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተለየ አካል የያዘ አምላክ አይደለም።

ከሁሉ በላይ የሆነው የመንፈሱም የልጁም ባለቤት የሆነው አንድ አምላክ አብ አለን ፤የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔር ልጅ በመባል መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ምክንያት #የ የሚል ቅጥያ ባለቤትነት ገላጭ ሆኖ ይገኛል።

ለእግዚአብሔር መንፈስ ያለው አመለካከት በትክክል በመረዳት እስከ ኢየሩሳሌም እንደ ዳዊት ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ እያለን እንኑር።

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው በ ቅንነት ቃሉን በመማር እና በማወቅ እንድንኖር ያ የእሥራኤል አምላኩ አንዱ ይርዳን።
አሜን
ወንድማችሁ ነኝ

08/02/2026

/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ባለቤታቸው የመከላኪያ ከፍተኛ አመራር ጀነራል ሀብታሙ ጥላሁን በሆሳዕና ቸገኝተዋል ክብር ለኢየሱስ ይሁን

08/02/2026

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሰበካ ኮንፈረንስ በሆሳዕና እናት አጥቢያ እየተካሄደ ያለውን ኮንፈረንስ በቴሌግራም ቻናላችን በድምፅ መከታተል ትችላላችሁ::
ሊንክ ኮሜንት ስር ታገኛላችሁ::

Address

River Street 34
Bothaville
9660

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+27610101041

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic Church of Rustenburg South Africa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share