06/09/2025
ጳጉሜ 1/2017
👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን ብለን በማመን በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከነሐሴ ወር መጨረሻ በኋላ ጳጉሜ የምትባል አምስት ወይም ስድስት ቀን አለች እንኳን አደረሰን
👉ጳጉሜን ወር እንዳንላት 25 ቀን ይጎላታል ሳምንትም እንዳንላት 2 ቀን ያንሳታል ለወርም ለሳምንትም አቅም የሚያንሳት #ጳጉሜ በአመቱ መጨረሿ ላይ ትገኛለች
👉ጳጉሜ የሚለው ስያሜ #ኤፓጉሜኒ 'ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜው "ተጨማሪ" ማለት ነው በመሆኑም ጳጉሜ የአመቱ ምራቂ ቀናት እንጂ ወር ወይም ሳምንት አትባልም
👉አውሮፓውያን በአመቱ ወራት ውስጥ በታትነዋታል ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ በማድረግ የአመቱን ቀን 365 ወይም 366 ቀን ብለው ደምረውታል
👉ጳጉሜ በየአመቱ አምስት ወይም ስድስት ቀን ሆና የምትመጣ ናት አንዴ ጳጉሜ ስድስት ሆና ትመጣለች በዚህም የአመቱ በዓላት ቀናትን ትቀይረዋለች ለምሳሌ የገና በዓል በአራት አመት አንዴ ታህሳስ 28 ቀን ሲውል ሌላውን ግን 29ኝ አይለቅም
👉በዚህም ኢትዮጵያ የ13 ወር ፀጋ ባለቤት እና ከአፍሪካም ከአለም ብቸኛ የሯሷ አቆጣጠር ያላት ሀገር ያደርጋታል እስካሁን ሳይንስ ያልደረሰበት ነገር ግን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በሚገባ የሚያውቁት ጳጉሜ ትሆናለች ለዚህም ብቸኛዋ ማስረጃ ተዋህዶ ሐይማኖትና ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት
👉የጳጉሜ ፆም ይህች ፆም ከሁለቱ የፈቃድ ፆም አንዷ ናት አንዱ ፆመ ፅጌ ሲሆን ሁለተኛዋ ይህች የጳጉሜ ፆም ናት በብዙሀን ዘንድ ባትታወቅም ታላቅ የበረከት እና እራስን የም
ናድስባት ጾም ነች
👉የጳጉሜ ፆም ፆመ ዮዲት በመባልም ትታወቃለች ይህም
ዮዲት እራሷ #ስለፆመችው ነው ዮዲት ስላችሁ የቤተክርስቲያን አጥፊ የሆነችው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነ አስምሩልኝ
👉ዮዲት ጠላቷን ማጥፋት የቻለችው በፆም እና በፀሎት #ከእግዚአብሔር አምላክ ሀይልን አግኝታ ነው ሙሉ ታሪኩን መፅሐፍ ቅዱስ ላይ መፅሐፈ ዮዲት ላይ ይመልከቱ
👉ሌላው ይቺ ጳጉሜ መታሰቢያ ቀን ነች
እርሱም በደብረ ዘይት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድ ነው አሉት ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ብዙዎችንም ያስታሉ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ
👉አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው ሕዝብ በሕዝብ ላይ ላይ ይነሣልና ራብሞ ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል እነዚህም ሁሉ መጀመሪያ ናቸው ማቴ.24 ሙሉዉ ይነበብ
👉ጳጉሜ የአመቱ መገባደጃና መሸጋገሪያ እንደመሆኗ መጠን እጅግ ድንቅ ቀን ናት ይህች ወር መታሰቢያ ናት የዘመነ ፍዳ መገባደጃ ከቁር ብርዱ መላቀቂያ በመሆኗ ብዙ እና አያሌ ጥቅም አላት
👉ስለዚህ ምዕመናን በየአመቱ #ጳጉሜን የቻለ በመፆም በመፀለይ መጪውን አመት የተሻለ እንዲሆን እራስን በማዘጋጀት ፀበል በመጠመቅ በልዩ ዝግጅት ያሳልፋሉ
👉እኛም ይቺን በዓመት አንዴ የምትገኝ ዕለት ስለ #ሐገራችንና ሠላም ስለ #ህዝባችን ፍቅርና አንድነት እየፀለይን ለመሪዎቻችንንም ህዝቡን የሚመሩበትን ጥበብ እንዲሠጥልን የቻልን እየፆምን ስለ እራሳችን ሀጢአት እያለቀስን ንስሀ ገብተን ከሀጢአት የፀዳ አዲስ አመት ለመቀበል ፈጣሪ ይፈቀድልን ዘንድ እየተማፀንን መጪዉ አዲስ አመትም ሆና የምታርፍበት አዲስ አመት እንዲሆንልን የቅዱሣኑ ሁሉ ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉 ጳጉሜ 1/2017 ዓ/ም
ከሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ