Hamere Birihan Kidist Kidane Mihiret And Kidus Giorgis EOTC

Hamere Birihan Kidist Kidane Mihiret And Kidus Giorgis EOTC Grand Rapids MI Ethiopian Orthodox Church

04/24/2023
04/28/2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን
👉ለሐመረ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምእመናንና ምእመናት በሙሉ👇
እንኳን ለብርሃነ ትንሣዔ አምላክ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ በሚመጠው ቅዳሜ Apr. 30 /2022 ከ 2:00am ጀምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ስለሚከበር የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ እናሳስባለን::ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን👉የደብሩ ሰበካ ጉባዔ‼

እንኳን ለብርሐነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።
04/24/2022

እንኳን ለብርሐነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።

እንኩዋን አደረሳችሁ አደረሰን ዛሬ ድርብ በአል ነው ፆም ይፈታል ጼጥሮስ ወ ጳውሎስ ናቸው እንዲሁም አቡየ ገብረ መንፈስቅድስ ናቸው ።  የቅድሳኑ ፀሎት በሀገራችን እና በህዝባችን ይደር አሜን...
07/12/2020

እንኩዋን አደረሳችሁ አደረሰን ዛሬ ድርብ በአል ነው ፆም ይፈታል ጼጥሮስ ወ ጳውሎስ ናቸው እንዲሁም አቡየ ገብረ መንፈስቅድስ ናቸው ።
የቅድሳኑ ፀሎት በሀገራችን እና በህዝባችን ይደር አሜን።

ሰኔ 12   ዓመታዊ በዓል!እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ ...
06/19/2020

ሰኔ 12 ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

06/08/2020

ፆመ ሐዋርያት

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል
ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን
ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን።

3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14

5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን
ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !

ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!!

06/06/2020

ሃሌ ሉያ እስከነ ቀዳሚ ወእስከ ዮም፡ ከመ ደሙ ለአቤል አዳም።

Address

Wyoming, MI
49519

Opening Hours

6am - 11:30am

Telephone

+16164197795

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hamere Birihan Kidist Kidane Mihiret And Kidus Giorgis EOTC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share