ደቂቀ አበው ሰ/ት/ቤት Dekike Abew Sunday School

ደቂቀ አበው ሰ/ት/ቤት                                    Dekike Abew Sunday School Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደቂቀ አበው ሰ/ት/ቤት Dekike Abew Sunday School, Religious organisation, 134 Templeton Pkwy, Watertown, MA.

ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቦስተን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ደቂቀ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።

This the official page of Boston Dagmit Debre Libanos Abune Teklehaimanot Church, Dekike Abew Sunday School

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የደቂቀ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት "STEAM Pathways Symposium" በሚል ርዕስ ለhigh school እና Middle school ተማሪ ልጆቻችን የተዘጋጀ ...
05/21/2026

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የደቂቀ አበው ሰንበት ትምህርት ቤት "STEAM Pathways Symposium" በሚል ርዕስ ለhigh school እና Middle school ተማሪ ልጆቻችን የተዘጋጀ የሙያና የትምህርት ገለጻ ዝግጅት ቅዳሜ June 6, 2026 ከቀኑ 12:30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ፣ በቤተ ክርስቲያናችን አዳራሽ ውስጥ ያካሂዳል።

ስለዚህ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማራችሁ እና በዚያ ቀን volunteer ለማድረግ ፈቃደኛ የሆናችሁ ምእመናን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ቅጽ በመሙላት ስለሙያችሁ ገለጻ ለማድረግ ፈቃደኝነታችሁን እንድታሳውቁን በትሕትና እንጠይቃለን።

https://forms.cloud.microsoft/r/XjPyiLaV8z

Only 2 days left until our Young Adults' Gubae! Open to all 16+ high school students, college students and working profe...
04/16/2026

Only 2 days left until our Young Adults' Gubae! Open to all 16+ high school students, college students and working professionals in the Boston area! Saturday April 18 12-4pm

👇👇👇👇👇

Christ is risen!Join us for a special gubae this *Saturday 12 - 4PM.**RSVP:* https://forms.gle/4pB4HXJmdhm5DNic6*🙏🏾 Spec...
04/15/2026

Christ is risen!

Join us for a special gubae this *Saturday 12 - 4PM.*
*RSVP:* https://forms.gle/4pB4HXJmdhm5DNic6

*🙏🏾 Special Guest:* Fr. Haileyesus Asnake, PhD

*📍Location:* St. Teklehaimanot Church - 134 Templeton Pkwy, Watertown, MA

*🍽️ Lunch will be served*

Tell a friend to tell a friend! We look forward to seeing you 🤍

ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን፣      በዐብይ ኃይል ወስልጣን፣አስሮ ለሰይጣን፣       አግዓዞ ለአዳም፣ሰላም፣     እምኢዜሰ፣ኮነ         ፍሰሃ ወሰላም፣" ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን...
04/13/2026

ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን፣
በዐብይ ኃይል ወስልጣን፣
አስሮ ለሰይጣን፣
አግዓዞ ለአዳም፣
ሰላም፣
እምኢዜሰ፣
ኮነ
ፍሰሃ ወሰላም፣
" ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ እንደተናገረ ተነስቷል እንጅ በዚህ የለም" ሉቃስ 24፥5
መልካም የትንሣኤ በዓል!

በዓለ ትንሳኤ 4/11/2026

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ...
04/06/2026

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

እብኖዲ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

ታኦስ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

ማስያስ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

ትስቡጣ፦
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

Address

134 Templeton Pkwy
Watertown, MA
02472

Opening Hours

5am - 10:30am

Telephone

+18579396963

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደቂቀ አበው ሰ/ት/ቤት Dekike Abew Sunday School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ደቂቀ አበው ሰ/ት/ቤት Dekike Abew Sunday School:

Shortcuts

Share