Amen Media

Amen Media " This is the solemn pronouncement of the Amen, the faithful and true witness, the originator of God's creation" ( Revelation 3;14)

በእግዚአብሔር አምላክ ጸጋና እርዳታ "THIS IS THE DAY" ለህትመትና ስርጭት በቅቷል። ይህ መጽሐፍ በጸሎትና በምስጋና እናንተ ውድ ወገኖቼ በምትገኙበት ይመረቃል:: FOUR CORNERS...
08/03/2024

በእግዚአብሔር አምላክ ጸጋና እርዳታ "THIS IS THE DAY" ለህትመትና ስርጭት በቅቷል። ይህ መጽሐፍ በጸሎትና በምስጋና እናንተ ውድ ወገኖቼ በምትገኙበት ይመረቃል::
FOUR CORNERS ETHIOPIAN EVANGELICAL CHURCH
33 UNIVERSITY BLVD E
SILVER SPRING MD 20903
SATURDAY, AUGUST 24/2024; 2:00PM - 6:00PM
አብራችሁኝ እግዚአብሔርን እንድናመሰግንና እርስ በእርስ ለፍቅርና ለምልካም ስራ እንድንነቃቃ በአክብሮት ጠርቼአችኋለሁ።

ደስ ብሎኛል ! እግዚአብሔር ይመስገን !!!“THIS IS THE DAY" A fool-proof remedy for unmet resolutions and goals.የተሰኘው መጽሐፌ በታወቁ ሁለት አስታ...
06/29/2024

ደስ ብሎኛል ! እግዚአብሔር ይመስገን !!!
“THIS IS THE DAY"
A fool-proof remedy for unmet resolutions and goals.
የተሰኘው መጽሐፌ በታወቁ ሁለት አስታሚዎች ተቀባይነት አግኝቷል። ታትሞ ሲወጣ በስድስትና በሰባት ወራት ውስጥ “Best Seller List” እንደሚገባም አምነውበታል። በቅርቡ የሚሰጡኝን ቅድመ ክፍያ ተደራድረን ስንጨርስ ከአስራ አምስት በላይ Platforms እንዲሁም ከሶስት ሺህ በላይ በሆኑ የአሚሪካ የመጽሐፍ መሸጫ መደብሮች ይከፋፈላል።
እኔ እስከማውቀው ድረስ እነዚህ አሳታሚዎች የትውልደ ኢትዮጵያዊን መጽሐፍ በራሳቸው ወጭ አርመውና አስተካክለው፡ የመጽሐፉን ሽፋን ሰርተው፡ አሳትመውና አከፋፍለው ደጎስ ያለ ገንዘብ በቅድሚያ ለመክፈል ተስማምተው አያውቁም።
ይህ እኔ በእግዚአብሔር አምላክ ጸጋ፤ ሞገስና እርዳታ ያገኘሁት እድል ለሌሎች ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጸሐፊዎች ትልቅ በር ይከፍታል ብዬ አምናለሁ።
ይህ የሁላችንም ለሁላችንም ትልቅ ስኬት ነው።
ከአሳታሚዎቼ ጋር ባደርኩት ስምምነት መሰረት ይህ መጽሐፍ በቅርቡ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ብቻ ተመርቆ ይለቀቅል።
ባከታታይ ስለ መጽሐፉ ይዘትና ስለምረቃው መረጃዎችን አጋራችኋለሁ።
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር አምላክ ብቻ ይሁን !!!

አዲስ ማንነት እንጂ አዲስ ዓመት ምንም አያመጣም።የዲስኒ ታዋቂው ካርቶኒስት ስለ ለነገ-ይደራውያን የሳለው አስቂኝ ካርቶን አይረሳኝም። እንዲህ ይላል።“ዛሬ ሊደረግ ታቅዶ የነበርው የነገ-ይደራ...
12/13/2023

አዲስ ማንነት እንጂ አዲስ ዓመት ምንም አያመጣም።
የዲስኒ ታዋቂው ካርቶኒስት ስለ ለነገ-ይደራውያን የሳለው አስቂኝ ካርቶን አይረሳኝም።
እንዲህ ይላል።
“ዛሬ ሊደረግ ታቅዶ የነበርው የነገ-ይደራውያን አባልት ስብሰባ ለነገ ተላልፏል።”
ባለቅኔዋ ግሎሪያ ፋይዘር ለነገ-ይደራዊነትና የይቆይ-ይደርሳላዊነትን አስከፊነቱን ለመግለጽ እንዲህ ዘረፈች።
“ዛሬ መፈጸም የሚገባኝን ለነገ ማሳደር የኔ ታላቁ ሐጢአት ነው።
ከነገ ጀምሮ ግን ይህንን አላደርግም።”
እግዚአብሔር በሰራት ቀን የሚገባንን አድርገን ፍሬ እንዳናፈራ ከሚያደርጉ አንኳር ተግዳሮቶች መሀከል ለነገ-ይደራዊነት”ን የሚስተካከል አስከፊ ተግዳሮት አለ ብዬ አላምንም። በእንግሊዝኛ ቋንቋ (Procrastination) የሚባለውን ይህንን ጸረ-ስኬት እኩያ አንድ የአማርኛ ቃል ፈልጌ ባለማግኘቴ “ለነገ-ይደራዊነት” እና “ቆይ-ይደርሳላዊነት” ብዬዋለሁ።
እኔ በግል ሕይወቴ እጅግ ጎትቶኝ የነበረው አሁንም በጥብቅ የምታገለው ይህ አስከፊ ባሕርይ ነው።
ነገ እሰራዋለሁ፡ ነገ እጽፈዋለሁ፤ ነገ እሰጣለሁ፤ ነገ እጸልያለሁ፤. . .
ወገኖች፤ ዛሬ መስራትና መጨርስ የሚገባንን ነገር ለነገ ማሳደርና ማስተላለፍ እንዳልተጠቀምንበትና አስቀድመን እንደበላንው እቁብ እቆጥረዋለሁ።
እቁብ አስቀድሞ መብላት የሚጠቅምበት ጊዜ አለ። ያልታሰበ አደጋ ሲደርስ፤ ብዙ ወለድ ያለው እዳ ለመክፈል፡ ቋሚ ንብረት ለመገንባት፤ አትራፊ ንግድ ለመጀመርና ለመሳሰለው አስቀድሞ እቁብ መውሰድ ይጠቅም ይሆናል።፡ ዘላቂ ጥቅም ለሌለው አልባሌ ነገር የሚባክን እቁብ አስቀድሞ መብላት ግን ህመሙ የሚጀምረው የበላንውን እቁብ መክፈል ስንጀምር ነው። ለነገ-ይደራላዊነትን በአግባቡ ከማንጠቀምበት ከተበላ እቁብ ጋር ያመሳሰልኩት ለዚህ ነው። ሰርተን ሲደክመን ማረፍ ሲገባን ሳይደክመን አርፈን በድካምና በውጥረት መስራት።
አንዳንድ መሰረታዊ አስተምህሮዋቸው አጠያያቂ ቢሆንም ማይልስ ሞንሮ ይህንን በተመለከተ ያሉትን እጅግ እጋራዋለሁ። እንዲህ አሉ።
“በአለም ላይ እጅግ ብዙ ጥበብ የሞላቸው መጽሐፍት፤ አስደናቂ ስእሎች፤ ማራኪ ዝማሬዎች፤ አዳዲስ ጠቃሚ ግኝቶችና የመሳሰሉት የት እንደሚገኙ ታውቃላችሁ?” ጥያቄውን እራሳቸው መለሱት። “እነዚህን ድንቅ ስራዎች የምታገኙት፤ በታዋቂ ሙዚየሞች ወይም ቤተ-መጻሕፍት ሳይሆን በመቃብር ቦታ ነው። ነገ እሰራዋለሁ፤ እጽፈዋለሁ፤ አንቆረቁረዋለሁ.... ሲሉ ከነበሩ ሰዎች ጋር የቀን ብርሀን ሳያዩ አብሯቸው ተቀበሩ።”
ለነገ-ይደራላዊነትና ቆይ-ይደርሳላዊነት በተሰጠን የተቆጠረ ቀንና ጊዜ ፍሬ እንዳናፈራ የሚያደርግን ትልቅ ሰርና ተግዳሮት ነው።
በርግጥ ለነገ የምናሳድራቸውና በመቆየት የምንጠቀምባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ አስተውላለሁ። በጸሎት በመጠበቅና በመጽናት ምላሽ ይገኛል።
“ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።” (መዝሙረ ዳዊት 40፥1)
እግዚአብሔር አምላክን ታምኖ በመጠበቅ ሐይል ይታደሳል።
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
(ትንቢተ ኢሳይያስ 40፥31)
እንደዚህ አይነቶቹ ጠቃሚና አስፈላጊ ባሕርያት “ነገ-ይደራላዊነት” ወይም “ቆይ-ይደርሳላዊነት” አስከፊ ባሕርያት አይደሉም።
ዛሬ ማድረግ የሚገባንን እያደረግን የእግዚአብሔር አምላክን ጊዜ መጠበቅ ከኛ የሚጠበቅ ውጤቱም መልካም የሆነ አስፈላጊ ባሕርይ ነው።
እንዲሁም እጅግ ፈተና በዝቶብን ልናደርገው እጅግ የተገፋፋንበትን ስጋዊ ሐጢአት እስከጭራሹ ወዲያውኑ ማስወገድ ካልሆነም ለነገ ማስተላለፍ ይጥቅማል እንጅ አይጎዳም። በቁጣ በከረረ ምሬት ጊዜ ልናደርግ ያሰብንውን ነገር ወደ ነገ ብናስተላልፈው እናተርፋለን፤ እንተርፋለንም።
ሁልጊዜ ወደ መጀመሪያው ግሩምና ድንቅ አፈጣጠራችን መመለስ እጅግ ይጠቅማል። እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ የፈጠረን በአምሳሉ በመሆኑ፤ እንዲሁም ባሁኑ የሕይወታችን ዘመን እግዚአብሔርን እንድንመስል በመጠራታችን፤ ይህንን በተመለከተ የእግዚአብሔር አምላክን ባህርይ ልንመስልና ልንወርስ ይገባናል። እግዚአብሔር አምላክ አጽናፈ አለሙን በስድስት ቀን ሲፈጥር ሁሉንም በቀኑ ሳያስተላልፍ መፍጠሩን ብቻ መመልከት ይበቃል።
ይህንን እግዚአብሔር በሰራት ቀን የሚጠበቅብንን አድርገን ለአምላክችን ክብርና ምስጋና፤ ለሰው ልጆች ጥቅም ለእኛም ስኬትና እርካታ እንዳንሆን የሚያደርገንንን ክፉ ባሕርይ ማስወገድ የሚገባን ከዛሬና ከዛሬ ጀምሮ ብቻ ነው። ይህንን የስኬት ጠር ከነገ ጀምሮ ለማስወገድ ማሰብ በራሱ የዚህንን መርዘኛ ጠንቅ ማንነት አለመረዳት ነው። ዛሬ በድጋሚ ይህንን እላለሁ። ዛሬ ማድረግና መከወን የሚገባንን ይህ ለነገ ይደር የምለውን አጉል ባህርይ ከነገ ጀምሮ አስተካክለዋለሁ ብሎ ማሰብም በራሱ የዚህ አደገኛ የስኬትን ጠር ባህርይ አለመረዳት ነው። መውገድ ያለበት እግዛብሔር በፈቃዲኡና በችሎታው በሰጠን በዛሬዋ ቀን ነው። ዛሬ።
(በቅርቡ ታትሞ በነጻ ከሚታደለው “እግዚአብሔር የሠራት ቀን” መጽሐፍ የተቀነጨበ)

http://amenmedia.org/
12/18/2016

http://amenmedia.org/

This is my first book. God willing it will be printed very soon. After that, I will set up a system so that you may directly order the book from here. I will also upload the whole content so that you...

Address

55o5 1st Street NW
Washington D.C., DC
20011

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Amen Media:

Share