AmlekoTube - አምልኮቲዩብ

AmlekoTube - አምልኮቲዩብ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያደረጉ መንፈሳዊ መዝሙሮች,ስብከቶች እና ዜናዎች የሚቀርብበት ገፅ።
Ethiopian Christian Gospel songs, preaching and News page (Mark 16:15)
(863)

"እንዲህም አላቸው፡- ‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡" (የማርቆስ ወንጌል 16፡15)

"And he said unto them, Go ye into all the world, and preach the gospel to every creature."

➡️ የ 90ዎቹ የርሆቦት አርት ሚንስትሪ ፍሬዎች ታዴ፤ገኒ፤ሚሊዮን፤ ሔኖክና ፌቨንበረከታችን ናችሁ ጌታ ይባርካችሁ በቪሲዲ መቼም የማይረሳ መንፈሳዊ ድራማዎቻቸው ውስጥ በጥቂቱ👇👇የተዋጋ ቅድስና...
09/08/2026

➡️ የ 90ዎቹ የርሆቦት አርት ሚንስትሪ ፍሬዎች ታዴ፤ገኒ፤ሚሊዮን፤ ሔኖክና ፌቨን
በረከታችን ናችሁ ጌታ ይባርካችሁ
በቪሲዲ መቼም የማይረሳ መንፈሳዊ ድራማዎቻቸው ውስጥ በጥቂቱ👇👇

የተዋጋ ቅድስና
ኮብላይ ባለአደራ
የትውልድ ክፍተት ( ይህ ትንቢት የሆነ ፊልም ነዉ)
ተከታይ ጥላ
የጥቀርሻ ድሚፅ
የተጣሰ ድንበር
ነበልባል አሻራ
ተንሸራታች ዘመን
ዝማሬዎቻቸው
ዘመናችሁ ይባረክ ተባረኩ🙌🙏

Secure your glass doors with absolute style. 🚪Artisan says: trust our Glass Patch Fittings! ✨
09/08/2026

Secure your glass doors with absolute style. 🚪
Artisan says: trust our Glass Patch Fittings! ✨

አዲሱን ዓመት በእምነትና በአንድነት እንሻገር  የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አስመልክቶ ዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በ...
09/08/2026

አዲሱን ዓመት በእምነትና በአንድነት እንሻገር የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አስመልክቶ ዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጠ

በመግለጫውን የሰጡት የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት ፓስተር ደሳለኝ አበበ ወደ 2019 ዓ.ም. ስንሻገር ፈተናዎች እና ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሊኖሩ ቢችሉም፣ በእምነት፣ በአንድነትና በትብብር ከተጓዝን ፈተናዎችን ማለፍ ይቻላል ሲሉም ተናግረዋል።

አዲሱን ዓመት በአዲስ ልብ በመጀመር፣ እጃችንን ለመርዳት፣ ልባችንን ለመውደድ፣ አእምሯችንን ለመማር እና እምነታችንን በተግባር ለመግለጽ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ባለፈው 2018 ዓ.ም. ከተገኘው ደስታ ምስጋናን፣ ከመከራ ጽናትን፣ ከስህተት ጥበብን እና ከሐዘን ትምህርትን ይዘን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተለይም ልዩነቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያገናኘንን እምነትና ተልዕኮ ማስቀደም፣ እርስ በርስ መከባበርና መተባበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ቤተ ክርስቲያንም የሰላም መልዕክትን ከመስበክ ባለፈ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ሰላምን በመኖር፣ በማስፋፋትና ለእርቅ በመሥራት የመታረቂያ ድልድይና የተስፋ ምንጭ መሆን እንዳለባት ገልጸዋል።

ወጣቶችም የነገ ተስፋ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬ አጋሮች በመሆናቸው፣ በትምህርት፣ በሥራና በእምነት እንዲጸኑ፣ ድምፃቸውንም ለግንባታ፣ ለማስታረቅና ለፈጠራ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

ፓስተር ደሳለኝ አበበ፣ ለመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የቤተ ክርስቲያኗ ወዳጆች የ2019 ዓ.ም. ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የጸጋና የበረከት እንዲሆን ተመኝተዋል።

“እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይባርክ፤ ቤተሰቦቻችንን ይጠብቅ፤ ለኢትዮጵያችንም ዘላቂ ሰላምን ይስጥ” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዳንኤል አንተነህ

Meserete Kristos Church - Head Office

ግን በጴንጤ ላይ ከበሮ እንዴት ነው የሚያምረው እንዲሁም ከበሮ የኛ ነው ከዚህ በኃላ 🤗🤗
09/08/2026

ግን በጴንጤ ላይ ከበሮ እንዴት ነው የሚያምረው
እንዲሁም ከበሮ የኛ ነው ከዚህ በኃላ 🤗🤗

በመንግስቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን 19 ዙር የውሃ ጥምቀት ተጠማቂዎች እንካን ደስ አላቹህ “የድሮው ሕይወት እዚህ ይቀራል፤ አዲሱ ሕይወት ከክርስቶስ ጋር ይጀምራል!” ✝️💧ዛሬ በእ...
09/07/2026

በመንግስቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን 19 ዙር የውሃ ጥምቀት ተጠማቂዎች እንካን ደስ አላቹህ

“የድሮው ሕይወት እዚህ ይቀራል፤ አዲሱ ሕይወት ከክርስቶስ ጋር ይጀምራል!” ✝️💧

ዛሬ በእምነት ወደ ጥምቀት ውኃ ስትገቡ፣ የድሮውን ሕይወት ትታችሁ ከክርስቶስ ጋር በአዲስ ሕይወት ለመነሳት የምትመሰክሩበት ቀን ነው። በእርሱ ሞት እንደተቀበራችሁ፣ በእርሱ ትንሣኤም እንደተነሳችሁ በሕይወታችሁ መግለጥ የጀመራችሁበት ቀን ነው።

ከዚህ ቀን ጀምሮ ለክርስቶስ ብቻ ኑሩ፤ በቃሉ ጽኑ፤ በፀሎት ጽኑ፤ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመላለሱ፤ በቅድስናም ሕይወታችሁን ግለጡ።

📖 “እንግዲህ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀብረናል፤ ክርስቶስ ከሙታን በአብ ክብር እንደተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።”
— ሮሜ 6፥4

📖 “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ አዲስ ሆኗል።”
— 2 ቆሮንቶስ 5፥17

🔥 የድሮው ሕይወት አልፏል! አዲሱ ሕይወት ተጀምሯል! ከክርስቶስ ጋር ተነሱ፣ ለክርስቶስም ኑሩ!:

ለማንኛውም ቦታ ልዩ ውበትና ጥራት የሚሰጡ የላቀ ደረጃ ያላቸው የመስታወት መገጣጠሚያዎች (Glass Hardware)። ✨ለጥንካሬ፣ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እና ለምርጥ አጨራረስ የተሰሩ ከፍተኛ...
09/07/2026

ለማንኛውም ቦታ ልዩ ውበትና ጥራት የሚሰጡ የላቀ ደረጃ ያላቸው የመስታወት መገጣጠሚያዎች (Glass Hardware)። ✨

ለጥንካሬ፣ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እና ለምርጥ አጨራረስ የተሰሩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመስታወት መገጣጠሚያዎች በመጠቀም የመኖሪያ ወይም የንግድ ስራ ፕሮጀክቶችዎን ያሻሽሉ።

የምንሰጣቸው የተለያዩ ምርቶች፡
✔️ Patch Fittings (የመስታወት መያዣዎች)
✔️ Floor Springs (የወለል ላይ መዝጊያ ዘዴዎች)
✔️ Glass Handles (የመስታወት እጀታዎች)
✔️ Spider Fittings (የስፓይደር አይነት መገጣጠሚያዎች)
✔️ Glass Clamps (የመስታወት መቆንጠጫዎች)
✔️ Connectors (አገናኝ ክፍሎች)

ዘመናዊ ቢሮ፣ ማሳያ ክፍል (showroom)፣ ሆቴል ወይም የቅንጦት መኖሪያ ቤት እየነደፉ ቢሆንም፣ Artisan Trading plc አስተማማኝ እና እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን መገጣጠሚያዎች ያቀርባል።

📍 ለገሀር, መዚድ ፕላዛ 9ኛ ፎቅ
📞 +251900830904
🌍 artisanerp.com

ሊተማመኑበት የሚችሉት ጥራት፤ የሚያደንቁት አጨራረስ።

እየሱስ የነገስታት ንጉስJESUS King of KingsIysuus Mooti Motootti
09/07/2026

እየሱስ የነገስታት ንጉስ
JESUS King of Kings
Iysuus Mooti Motootti

እስኪ እንዳልክ እና ማስተዋልን የምትወዷቸው 👍
09/07/2026

እስኪ እንዳልክ እና ማስተዋልን የምትወዷቸው 👍

Happy birthday Nebiy Zene,እንኳን ተወለድክልን::አንተ የትውልዳችን ስጦታ ነህ::እንወድሀለን::
09/07/2026

Happy birthday Nebiy Zene,እንኳን ተወለድክልን::አንተ የትውልዳችን ስጦታ ነህ::እንወድሀለን::

የጌጃ ቃለሕይወት 70ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የወንጌል ስርጭት እሁድ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ምጌጃ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ፡— እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤን...
09/07/2026

የጌጃ ቃለሕይወት 70ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የወንጌል ስርጭት
እሁድ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
ጌጃ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን
፡— እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።
1ኛ ሳሙኤል 7:12

Address

1701 Liberty Lane, Blacksburg
Virginia Beach, VA
24060

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AmlekoTube - አምልኮቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to AmlekoTube - አምልኮቲዩብ:

Shortcuts

Share