Being an Orthodox Christian.

  • Home
  • Being an Orthodox Christian.
Directions Website

Being an Orthodox Christian. The word Orthodox Christian was given to the early followers of Jesus, and the name has been 'stuck' to this day.

Being a Christian is not only about keeping rules and regulations, performing rituals, or even going to church. It's about a friendship - a friendship with Jesus Christ or an imitation of Christ's way of life. Jesus said that knowing him is the doorway to a special relationship with God. Jesus says that we can begin such a special relationship with God by committing ourselves to follow him.

In Christianity, the term Orthodox means "conforming to the Christian faith as represented in the creeds of the early Church.”

The word Orthodox Christian was given to the early followers of Jesus, and the name has 'stuck' to this day.

26/07/2025
02/02/2023

ምዕመናኑን ስለ ክፉ መናፍስት ውጊያ ያሳወቁ፣ ከ 30 ዓመታት በላይ በፈተና በታጀበ አገልግሎት የዘለቁ፣ ስድብን እንደምርቃት እየቆጠሩ፣ ትውልድን የአምልኮት ሕይወት ያስተማሩ፣ አገልግሎትን ካለመታከት፣ ተግባራዊ ክርስትናን ከጸሎት ጋር አስተባብረው የያዙት ክቡር አባታችን መላከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ! የማገለግላት ወለላይቱ እመቤት ዕድሜ ከጤና ጋር ትስጣቸው።

"ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት" የማቴዎስ ወንጌል 2: "1-2፤ ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው...
09/01/2023

"ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት"
የማቴዎስ ወንጌል 2:
"1-2፤ ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና፡ እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።"........

"11፤ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።"

“ወበዓለም ሰሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ -በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፡33)ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ትምህርት ለቅዱሳን ሐዋርያት ስለሚጠብቃቸው...
21/09/2021

“ወበዓለም ሰሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ -በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፡33)
ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ትምህርት ለቅዱሳን ሐዋርያት ስለሚጠብቃቸው መከራ አስቀድሞ የነገራቸው እውነት ነው፡፡ ጌታችን ተከታዮቹን ወደ ዓለም ሲያሰማራ ትሾማላችሁ፣ ትከበራላችሁ፣ ትደሰታላችሁ፣ ዓለምም ይመቻችኋል ብሎ አልነበረም፡፡ ይልቁኑም እናንተን የገደለ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀረበ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል ብሎ ፊት ለፊታቸው የተጋረጠውን መከራ በማስረዳት በእምነትና በጽናት እንዲያልፉት ነግሮአቸዋል፡፡ ያም አምላካዊ ቃል እውን ሆኖ ሁሉም ሐዋርያት ከዚህ ዓለም በመከራ መስቀል አልፈዋል፤ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ተከታዮቻቸው ሁሉ በተመሳሳይ መከራ መስቀል አልፈዋል፤ አሁንም እያለፉ ይገኛሉ፡፡"

ብጹእ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

"The   means turning away from  , thinking that God knows, sees, and judges us in all the thought and desire we imagine,...
26/08/2021

"The means turning away from , thinking that God knows, sees, and judges us in all the thought and desire we imagine, in the words we say, and by the work we do."
HH Abune Mathias, Patriarich of EOTC

በትህትና...+ ዲያብሎስን ድል ማድረግያ ዋናው መንገድ፣ ትህትና መሆኑን የቀደሙ አባቶችም አስተምረውናል ምክኒያቱም ሰይጣን የወደቀው በትእቢት ሃጢያት ነው። በዚህ ምክኒያት ትህትና ድል ያደር...
17/10/2020

በትህትና...
+ ዲያብሎስን ድል ማድረግያ ዋናው መንገድ፣ ትህትና መሆኑን የቀደሙ አባቶችም አስተምረውናል ምክኒያቱም ሰይጣን የወደቀው በትእቢት ሃጢያት ነው። በዚህ ምክኒያት ትህትና ድል ያደርገዋል፣ ያዋረደውንና ወደ መርገም ያመጣውን፣ ከገነት መውጣቱን፣ ከሊቀመለአክትነት መዋረዱን ያስታውሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል: "፤እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።" (ወደ ቆላስይስ 3:12) ብሎ ከዚህም በመቀጠል "14፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።" ይለናል። ይህንን መንፈሳዊ ኃይል ግን እንዳንረዳ ዲያብሎስ በውስጥ ባህሪያቶቻችንን ተመሳስሎ በስውር በሚገባ ማስተዋላችንን አድቅቆታል።

ህዝቡ በቃሉ ሳይሆን በተቃራኒው በተንኮልና በክፋት ተወጥሯል። የአብዛኛዎቻችን ትኩረት አምልኮት ላይ ሳይሆን የሃይማኖትና የሰው ቲፎዞ በመሆን ተቧድነን በመሰዳደብ ቃለህይወት ያሰማልን በመባባል ለተንኮል እንደጋገፋለን። ዲያብሎስ የቱን ያህል እንደረቀቀብን ለመረዳት አቅማችን ደቋል፣ አቅም አንሶናል። ነገር ግን ትህትና ማለት እራስን ዝቅ ማድረግ ነው ከፍ የሚያረግህ አማላክ አለህና፣ ትህትና ማለት የሰውን ሳይሆን የእግዚአብሄርን ክብር ከፍ ማድረግ ነው፣ ትህትና ማለት ከኔ በላይ አባቶች አሉ ብሎ ማሰብ ነው፣ ትህትና ማለት በትእቢት ከመወጠርና አባቶችን ከመሳደብ መቆጠብ ነው፣ ትህትና ማለት ለአምላክህ መንበርከክ መስገድን ማወቅ ነው፣ በመንበርከክህ ወይም በመስገድህ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ያስብሃል፣ ባለመንበርከክህ ግን ከዲያብሎስ ጋር በፍቃድህ ተወዳጅተሃል ማለት ነው። ምክኒያቱም 'ክፉ ኃይላት ከሰማይ የተባረሩት አንገዛም ብለው ነው፡፡ አንሰግድም ብለው ነው፡፡ በፍቅሩ አንወድቅም ብለው ነው፡፡

'ታዲያ የሰው ልጅ በወደቀው የጨለማው ሠራዊት ምትክ ክብሩን ለመውረስና ምስጋናውን ለማድረስ ሲፈጠር ይህንን ተከትሎ ነው፡፡ አንወድቅም አንገዛም አንሰግድም ባሉት እብሪተኞች ምትክ በትህትና በፍቅር የተሞሉ በአምልኮት የሚሰግዱ የሰው ልጆችን እግዚአብሔር አምላክ አባት ሊሆናቸው ፈጠረ፡፡ ጽልመተ መልአክ ወደ ዓለም እስከሠራዊቱ የወደቀበት ምክንያት ግን ለፈጣሪ አልገዛም ብሎ ነው፡፡ ለአምልኮት ስግደት አልወድቅም ብሎ ነው፡፡ እኔ ራሴ አምላክ ነኝ ብሎ ነው፡፡ እንዲሰገድለት እንጂ ወደ እግዚአብሔር እንዲሰገድ በፍጹም አይፈልግም፡፡ ስለዚህ አምላክ ከክፉው ሊለየን 'እንደ እግዚአብሔር ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ' አለን። ይህ መንፈሳዊ ኃይል በአምላክ ፊት ዝቅ ማለትን መንበርከክን ያስተምረናል፥ ለአምልኮት ስግደት ይመራናል ስንሰግድ ደግሞ በሕይወታችን ውስጥ ስፍራ ካለው ዲያቢሎስ ከኛ ጋር በአንድነት ለመገኘት ይቸገራል፡፡ ይህንንም ሲያጠናክርልን "ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።" (የማቴዎስ ወንጌል 4፥10)'

በእመቤታችን ምልጃ መድኃኒዓለም ፀጋውና ክብሩን ያድለን አሜን!
https://youtube.com/channel/UCnKuEi4RpKqsbcS2u5AtkVg

"ከፈተናና ከመከራ ለማምለጥ እንዳትሞክሩ፤ከመከራ የሚሸሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር ይርቃል፤መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ 'በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸን...
20/06/2020

"ከፈተናና ከመከራ ለማምለጥ እንዳትሞክሩ፤
ከመከራ የሚሸሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር ይርቃል፤
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ 'በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ'።"- ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ (በግብጽ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው መናኝ, St Paul the first Hermit)

>እግዚአብሔር አሁንም በቃችሁ ይበለን! መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ከአሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ የካቲት  7 2012 ዓ.ምእኝህን አባት እንዴት እንደምወዳቸው ግን: እውነተኛ አባት እ...
15/02/2020

>

እግዚአብሔር አሁንም በቃችሁ ይበለን!

መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ
ከአሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ
የካቲት 7 2012 ዓ.ም

እኝህን አባት እንዴት እንደምወዳቸው ግን: እውነተኛ አባት እውነት የገባው ብቻ ይረዳቸዋል::

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Being an Orthodox Christian. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your place of worship to be the top-listed place of worship?

Share