Kidus Raguel S.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት

Kidus Raguel S.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidus Raguel S.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት, Religious organisation, 1001 Ruritan Cir, Sterling, VA.

Debre haile Kidus Raguel Cathedral's Tsion Mariam Sunday School preserves the rules, order and faith of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and committed to the future by doing as our fathers did for us with full responsibility.

11/05/2025

Save the Date Nov 16

"ብርሃናዊ ነህ ብራሃናዊ"
09/28/2025

"ብርሃናዊ ነህ ብራሃናዊ"

በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራል ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት መዘምራን Debre Haile Kidus Raguael CathedralSterling, VA, 20164አገልግሎታችን በፍጥነት እንዲደርስዎ የዩቱብ እና የፌስቡክ ቻናሎቻችንን ሰብስ...

Save the Date “Friday May 9”
05/06/2025

Save the Date “Friday May 9”

ቅድስት፤ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የ...
03/02/2025

ቅድስት፤ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡

‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡

ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡

፨ የዕለተ ሰንበት ክብር፤
በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8
በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡
ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡

ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡

ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና››
ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

• Facebook 👉 Kidus RaguelS.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጵዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት

01/26/2025

የጥር 21 የእመቤታችን የቅድሶት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍቷ ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀጥታ ስርጭት

12/20/2024
የደበረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት13ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ዝግጅት ቀጥታ ስርጭትኅዳር 8: 2017/ Nov 17, 2024
11/17/2024

የደበረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራ
ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት
13ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ዝግጅት
ቀጥታ ስርጭት

ኅዳር 8: 2017/ Nov 17, 2024

Debre Haile Kidus Raguael CathedralSterling, VA

6ኛው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ማስታወሻ ፎቶበደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራልስተርሊንግ ቨርጂኒያኅዳር 1: 2017 ዓ.ም/ Nov 10, 2024
11/13/2024

6ኛው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ማስታወሻ ፎቶ
በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራል
ስተርሊንግ ቨርጂኒያ

ኅዳር 1: 2017 ዓ.ም/ Nov 10, 2024

Save the Date
11/13/2024

Save the Date

Address

1001 Ruritan Cir
Sterling, VA
20164

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidus Raguel S.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Kidus Raguel S.S የደ/ኃ/ቅ/ራ ጽዮን ማርያም ሰ/ት/ቤት:

Share