09/05/2026
+++ ለእመ ኮነ እሑድ በጳጉሜን +++
❖ የዕለቱ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል [የዓመቱ መጨረሻ ግጻዌ]
==
** መዝሙር ዘወርኃ ጳጉሜን= ከመ እንተ መብረቅ
+++++
(በ፪) ከመ እንተ መብረቅ ዘይወጽእ እምጽባሕ ወያስተርኢ እስከ ዓረብ ከማሁ ምጽአቱ ለወልደ እግዚአብሔር ምስለ ኃይለ ሰማያት በንጥረ መባርቅት (ከ) ምስለ አእላፍ መላእክት ወኵሎሙ ሊቃነ መላእክት (ከ) አክሊለ አክሊላት ዲበ ርእሶሙ ለካህናት።
ትርጕም፦
++++++
መብረቅ (ፀሐይ) ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንዲታይ የሰው ልጅም አመጣጡ እንዲሁ ነው። ከሰማይ ኃይላት ጋር በመባርቅት ብልጭታ። ከአእላፍ መላእክትና ከሊቃነ መላእክት ሁሉ ጋር። የአክሊላት አክሊል በካህናት ራስ ላይ አለ።
መልእክታት:-
========
➊. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፩ : ፩ - ፲ (1:1-10)
➋. ፪ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፲ - ፍጻሜ (3:10-ፍጻሜ)
➌. የሐዋ/ሥራ ፱ : ፩ - ፲ (9:1-10)
+ ምስባክ
======
እግዚአብሔርሰ ገሐደ ይመጽእ።
ወአምላክነሂ ኢያረምም።
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ።
ትርጉም:-
=====
እግዚአብሔር ግልጽ ሆኖ ይመጣል።
ዝምም አይልም።
እሳት በፊቱ ይነድዳል።
(መዝ ፵፱ : ፪ /49 : 2)
====
Our God shall come,
and shall not keep silent; A fire shall devour before Him,
(Psalm 50:2)
+ ወንጌል
=======
የሉቃስ ወንጌል ፲፯ : ፲፩ - ፍጻሜ /17:11-ፍጻሜ
====
+ ቅዳሴ ~
** ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ) - በግዕዝ ዜማ