Debre Selam St.Michael EOTC

Debre Selam St.Michael EOTC በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ሳክራሚንቶ , አሜሪካ
3909 36th St, Sacramento, CA 95820

https://gofund.me/d0f334052

(ንግስ)እሁድ የቅ/ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሳክራሚንቶ ደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ወቅ/ማርያም ሰኔ 21 እሁድ ሁላችሁም ተጋብዛችሗል
06/24/2026

(ንግስ)እሁድ የቅ/ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሳክራሚንቶ ደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ወቅ/ማርያም
ሰኔ 21 እሁድ ሁላችሁም ተጋብዛችሗል

06/23/2026

“አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።”
ሐዋ16፥5

06/23/2026

st m

� New to streaming or looking to level up? Check out StreamYard and get $10 discount! �

06/23/2026
06/23/2026
የሳክራሚንቶ ደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ወቅ/ድንግል ማርያም የኢ.ኦ.ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊውን የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል በዓል በደመቀ አከበርን
06/22/2026

የሳክራሚንቶ ደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ወቅ/ድንግል ማርያም የኢ.ኦ.ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊውን የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል በዓል በደመቀ አከበርን

06/18/2026

ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ
{ ት ዳን 10÷13 }
መላእክት ማለት ምን ማለት ነው??
ሚካኤል ማለትስ ምን ማለት ነው???
መላእክት የሚለው "ቃል"መልእክተኞች' ተላላኪዎች'የእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ' የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡

✔ሚካኤል ማለት"‹‹መኑ ከመ እግዚአብሔር' እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?›› ማለት ነው፡፡ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.10፥13'2፥1/ ውስጥ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡

✔ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› /ዳን.12፥1/ በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› /ዳን. 10፥13/ በማለት ያስረዳል፡፡

✔በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይ ከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

✔ቅዱስ ሚካኤል አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድ መልአክ ነው፡፡ ‹‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም›› ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ኃይል ዲያብሎስን ድል የነሣ መልአክ ነው፡፡ ‹‹በሰማይ ጦርነት ተነሣ ሚካኤልና እርሱ መላእክት ከዘንዶው ከመላእክቱም ጋር ተዋጉ›› /ራእ. 12፥7/ ይላል፡፡

✔የሚካኤል በዓል ሰኔ 12 የሚከበርበት ምክንያት ዲያብሎስን በፈቃደ እግዚአብሔር ተዋግቶ ያሸነፈበት አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ክብር ይግባውና እግዚአብሔር በዚህች ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ከወገኞቹ ከመላእክት ሁሉ በላይ አክብሮ ሹሞታል›› ይላል ድርሳነ ሚካኤል

✔ከዚህ በተጨማሪ ይህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በአንዲት አገር ሃይማኖቱ የቀና ታላቅ መኮንን ከሙ አስተራኒቆስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ ሚስቱም አፎምያ ትባላለች፡፡ አፎምያ ባልዋ አስተራኒቆስ ታሞ እያለ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ እንዲሰጣት ለመነችው፤ እንዳለችው አደረገላትና ባልዋ ሞተ፡፡

✔ከዚህ በኋላ አፎምያ ባልዋ ያሠራላትን ሥዕል ይዛ በሃይማኖት ጻንታ ስትኖር ዲያብሎስ በተለያየ መልኩ ይፈትናት ጀመር፡፡ አንድ ጊዜ ባልቴት እየመሰለ ሌላ ጊዜ ሌላ እየሆነ ባል ማግባት እንዳለባት መከራት፡፡ መጽሐፍም ጠቀሰላት፡፡ ከንጉሡ ጋር ማጋባት እንዳሰበ ነገራት እርሷ ግን ማግባት እንደማትሻ እግዚአብሔርን እያገለገለች ኖራ ማለፍ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ ዲያብሎስ ግን ፈተናውን እያባሰ እያባሰ መጣ፡፡ በመጨረሻ ግን በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል አሳፍራ አዋረደችው፡፡

✔የሰኔ ሚካኤል ዕለት ዲያብሎስ ዳግመኛ ሊፈትናት መጣ፡፡ ሚካኤል ነኝ አላት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል››/2ቆሮ.11፥13/ እንዳለ በዚህን ዕለት የቀረባት ራሱን ለውጦ የብርሃን መልአክ መስሎ ነበር፡፡ አፎምያ ግን አስተዋይ ስለነበረች ‹‹የብርሃን መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ያለበት በትርህ ወዴት አለ?›› አለችው፡፡

✔በኛ በመላእክት ዘንድ የመስቀል ምልክት አይደረግም አላት፡፡ እርሷም ስለ ተጠራጠረችው የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ልታመጣ ወደ ሥዕል ቤቷ ስትገባ ዘለለና አነቃት፡፡ አፎምያ ጮኸች፤ ቅዱስ ሚካኤልም ፈጥኖ ደርሶ አዳናት ዲያብሎስንም አዋረደላት፡፡

✔ዲያብሎስ አፎምያ ያሰበችውን ጸጋ ሆኖ የተሰጣትን ኑሮ ትታ በተለየ ዓለም እንድትኖር እንደ መከራት በእኛም ሕይወት እንዲህ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በጋብቻ ወቅት ምንኵስናን እንድናስብ' በዕርቅ ሰዓት ጥላቻ እንዲሰማን' በሰላም ጊዜ ጦርነትን' በጾም ጊዜ ምግብን' በትዕግሥት ጊዜ ቁጣን በመረጋጋት ጊዜ አድመኝነትን በውስጣችን ሊያኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ እንደ አፎምያ በእምነትና በምግባር ጸንተን በማስተዋል ልንኖር ይገባል፡፡

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

የሰኔ ሚካኤል የሚከበርበት 6 ምክንያት1. ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት2.ግብፅ ውስጥ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት3. አፎሚያን የረዳበት4.ባህራንን የሞት ደብዳቤ የቀየረበት5.ቅዱስ ላሊበላን ወደሰማይ...
06/17/2026

የሰኔ ሚካኤል የሚከበርበት 6 ምክንያት

1. ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት
2.ግብፅ ውስጥ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት
3. አፎሚያን የረዳበት
4.ባህራንን የሞት ደብዳቤ የቀየረበት
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደሰማይ ያሳረገበት
6.ለፍጥረታት ምህረትን የሚጠይቅበት
የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን!

Address

Sacramento, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Selam St.Michael EOTC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share