Mekane Hiwot St Micheal Ethiopian Orthodox Tewahedo-Boston

Mekane Hiwot St Micheal Ethiopian Orthodox Tewahedo-Boston Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mekane Hiwot St Micheal Ethiopian Orthodox Tewahedo-Boston, Religious organisation, 26 winthrop Street, Roxbury, MA.

12/16/2025
01/09/2025

በስመ አብ ወወለድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ቦስተን የሚገኘው የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ድህረ ገፅ አሰርቶ በስራ ላይ አውሏል።በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የበለፀገውን ይህን ድህረ ገፅ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ይጎብኙ።

ያልዎትን አስተያየት እና ሀሳብ ድህረ ገፁ ላይ ባለው የሀሳብ መስጫ ክፍል ያጋሩን።ስለሚሰጡን ገንቢ አስተያየት በቅድሚያ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን።

https://www.mhstmicheal.org/

መካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

ቦስተን: 2017/2025

11/13/2024

ይህ ፅሁፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጊቢ ጉባኤ ገፅ የተወሰደ ሲሆን የህዳር ሚካኤልን አመታዊ ክብረ በአል አስመልክቶ ቦስተን በሚገኘው የመካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

04/29/2024

ከመካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቦስተን

ሰላም የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች እንኳን ለህማማተ
መስቀል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።

ከነገ ሰኞ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ
ቤተ ክርስትያናችን መካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሳምንቱን
በሙሉ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ክፍት ይሆናል።

ቀጥሎ ያለውን የጊዜ ሰሌዳ በመከተል አገልግሎቱን ማግኘት ትችላላችሁ።

ከሰኞ እስከ ሐሙስ ባሉት ቀናት ቤተ ክርስቲያናችን ከጠዋቱ 7AM/8AM የሚከፈት ሲሆን አገልግሎቱ እስከ 3PM/4PM ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።

አርብ እለት ቤተ ክርስቲያኑ ከጠዋቱ 7AM/8AM ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አገልግሎቱ እስከ ምሽቱ 8PM ድረስ ይከናወናል።

ቅዳሜ እለት ከምሽቱ 5PM የሚከፈት ሲሆን የማህሌት እና የኪዳን አገልግሎቱ ከምሽቱ 7PM/8PM ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:20PM እንዲሁም ቅዳሴው ከምሽቱ 11:30PM ተጀምሮ እስከ 2AM ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት እና በረከት ከእርስዎ እና ከመላው ቤተሰብዎ ጋር ይሁን።

✨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ               አሐዱ አምላክ አሜን ✨✨✨ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር 12 ✨✨  በዓል"በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ ፥እ...
11/07/2023

✨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን ✨

✨✨ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር 12 ✨✨

በዓል
"በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ ፥እንሆ መልአኬን በፊትህ እሰድዳለሁ።በፊቱ ተጠንቀቁ ፥ቃሉንም አድምጡ ፥ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢያት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። "
{ ኦሪት ዘጸአት 23፥20 }

🌿አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር 12 በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝን እና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸዉ ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

🌿እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው። እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በሀገር ዉስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸዉ አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታኦስም ሸጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገዉ ዘንድ የእርሱን ልብስ እና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጦ ሔደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መላእኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻዉን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘዉ አደረገ።
ወደ ቤቱም በተመለሰም ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘ። እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መላአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ። የተራቡ ድኾችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸዉና ወደየ ቤታቸዉ አሰናበታቸው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚካኤልም ለዱራታዎስ እና ለሚስቱ ሁለተኛ ተገለጠላቸው። ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቀዉ አዘዘዉ። በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሣዉ ሆድ ተገኘ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴኦብስታን እንዲ አላቸው ከዚህ ዲናር ወስዳቹ ለባለ በጉ ለባለ ዓሣዉና ለባለ ስንዴው እዳችሁን ክፈሉ የቀረውንም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር ዐስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ዐስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ። በኋለኛዉም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል።
እነርሱም ሲሰሙ ደነገጡ። እርሱም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መስዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸዉ። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ። እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቆጠር ብዙ ነዉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መላአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜንታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤበሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በሙሉቦስተን የሚገኘው መካነ ሕይወት ቅዱስ ሚ...
10/13/2023

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

በሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በሙሉ

ቦስተን የሚገኘው መካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 10 2016 ዓ.ም.
ወይም October 21, 2023 ከ 4PM እስከ 10PM ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ይካሄዳል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ ፣ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እንዲሁም ሊቀ ትጉኃን ደረጄ ነጋሽ ይገኛሉ።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በተለያየ ምክንያት መገኘት የማትችሉ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ለተራዳኢው መልዐክ
ባሉበት ሆነው በ 617 – 276 – 5799 በመጠቀም በዜል ፣ በ ካሽ አፕ አልያም በ ቬንሞ እንዲደግፉ በአምላካችን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

መርሃ ግብሩ በዕለቱ ማለትም October 21, 2023 በቀጥታ በ Youtube እና በ Facebook የሚተላለፍ ሲሆን ቢችሉ የመግቢያ ትኬቱን ይዘው በአካል ካልቻሉ መርሃ ግብሩን እየተከታተሉ በቀጥታ ስልክ ቁጥር 617-276-5799 በመደወል ድጋፍዎን ባመቸዎ መልክ እንዲለግሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹህ ነው።
የሐዋርያት ስራ 20:35

መካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቦስተን

10/13/2023

In the name of the Father, Son, Holy Spirit, One God, Amen

For all followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith in North America.

Mekane Hiwot St. Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, will be hosting a spiritual gathering where donations will be gathered.

For those who are not able to come but wish to donate still, you can use our Church's number, 617-276-5799, to make your donation using Zelle,
Venmo and CashApp.

The event will be held on Saturday, October 21, 2023, from 4 pm to 10 pm and will also be streamed on YouTube and Facebook.

"It is more blessed to give than to receive."
Acts 20:35

Mekane Hiwot St. Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

10/04/2023

በሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በሙሉ

በቦስተን የሚገኘው መካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመጪው ጥቅምት 10,2016 ዓ.ም ወይም October 21, 2023 እለተ ቅዳሜ ከ 4PM እስከ
10PM ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያካሂዳል።

በተለያየ ምክንያት መገኘት የማትችሉ የመልአኩ ወዳጆች ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ባሉበት ሆነው በ 617 – 276 – 5799 በመጠቀም በዜል ፣ በ ካሽ አፕ አልያም በ ቬንሞ እንዲደግፉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

መካነ ህይወት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቦስተን።

Address

26 Winthrop Street
Roxbury, MA
02119

Opening Hours

Saturday 9am - 1pm
Sunday 5:30am - 2pm

Telephone

+16172765799

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekane Hiwot St Micheal Ethiopian Orthodox Tewahedo-Boston posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share