Meqrez Gospel Light Church, Oakland CA, USA.

Meqrez Gospel Light Church, Oakland CA, USA. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Meqrez Gospel Light Church, Oakland CA, USA., Evangelical church, 3755 13th Avenue, Oakland, CA.

05/19/2026
Happy Mathers  day
05/11/2026

Happy Mathers day

04/12/2026

ነውር የሌለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውር የሌለን አደረገን!!

መቅረዝ የወንጌል ብርሀን ቤተ ክርስትያን
ፓስተር ነህምያ ወልደአማኑኤል
(ከካሊፎኒያ ኦክላንድ)

በእስራኤላውያን ዘንድ ከሚከበሩ አመታዊ በአሎች ውስጥ አንዱ 'የስርየት በአል' ነው። አመት ተጠብቆ የሚመጣ!የማይቀርበት! የሚጓጓለት !የበአሎች ሁሉ ቁንጮ በአል!!

በበአሉ መምጣት የማይደሰት:የማይጨፍር የማይቦርቅ ማን አለና።ለምን ይሆን ግን ይሔ ሁሉ ደስታ?በበአሉ ህዝቡ ከበደል ርሱሰቱ ሁሉ ይነጻበታላ። የከበደውን የሀጥያት ሸክም ሁሉ ያራግፍበታል።ይገላገልበታላ!!

ዘሌዋውያን 6:7 "ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል"ተብሎ እንደተጻፈ አሰስ ገሰሱን ሁሉ ካህኑ በሰዋው በግ ምክንያት ከላዪ ላይ ያራገፈ ህዝብ ይሆንና ከክስ በጸዳ ህሊና አምላኩን እያመለከ በሀሴት ወደ ቤቱ ክትት ነዋ !!!!እፎፎፎይይይይ!!

ታድያ ይሔ ሁሉ የሚገኝበት በአል ምነው አይወደድ! ምነው አይናፈቅ! ምነው በደረሰ አይባል! የበአሉ ማእከል ደግሞ የፋሲካው በግ።ቀድሞ ነገር የበአሉ ሙሽራ ማን ሆነና?በጉ አይደለምን?ደግሞስ የፋሲካ በግ በሌለበት የ'ስርየት በአል 'የሆነው የፋሲካ በአል ራሱ የት አለና!!ምንስ ትርጉም ሊኖረው?

በጉ ግንገና ለገና በግ ስለሆነ ብቻ ለመስዋእት ይቀርባል ብለህ እንዳታስብ።ዘሌዋውያን 6:6 እንዲህ ይላል

"..ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ"

ይኸዋ።በጉ አይነት አለው።የበጉ ምርጫም የዋዛ አይምሰልህ።ምርጫው የበጉን ላት :ፍርምባ: ሽንጥ: ጥርሱን እያዪ ከሌሎች በጎች ሊያወዳድሩት መስሎህ እንዳይሆን?አይደለም!!!

በአምላክ ፊት ለመቅረብ የሚመጥን መስዋእት ይሆን ዘንድ በጉ ማሟሏት የሚገባው ዋና ነገር አለ።እሱ ካልተሟላ በቀር በጉ 'የፋሲካ በግ' ተብሎ በጭራሽ አይጠራም።ይልቁንም ከመታረድ ይቀራል።ድሮ ቅዱሱ አምላክ ፊት ነውር ያለው በግ ምን ሲደረግ ይቀርብና።

አንብበውማ ጥቅሱን።ዘሌዋውያን 22 :20፤" ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ነውር ያለበትን አታቅርቡ"

ታድያስ?እንግዲህ በጉ ማሟላት ካለበት መስፈርት ውስጥ ዋናና ዋናው ከአንዳች የነውር ነቁጥ የጸዳ ሆኖ መገኘቱ ነው። ለዚህም ደግሞ በቅጡ ይመረመራል። ገላው ከአንዳች ቁስል የጸዳ መሆኑ እየተገላበጠ ይታያል።

ምርመራው ደግሞ የሚካሔደው በቀላል ሰዎች እንዳይመስልህ። ከከሙን ሳይቀር አስራት በሚያወጡ :ትንኝ በሚያጠሩ :ጸጉር ሰንጣቂ ፈሪሳውያን ነው የሚካሔደው ።

ጉምቱዎቹ ፈሪሳውያኑ የቀረበላቸውን በግ ተጠግተው ያዪታል።በሰርሳሪ አይኖቻቸው ወደ ውስጥ ሊያዪት ይሞክራሉ። ቀረብ ብለውም ቀንዱን ይይዙታል።አንዴ ከፊት አንዴ ከኃላ አንዴ ከላይ አንዴ ከታች ሌላ ግዜ ደግሞ ከቀኝ ደሞ ከግራ ይፈተሻል። ያውም አስራአራት ቀን ሙሉ።በጽኑ የምርመራ ክፍል ውስጥ በጉ ይቆያል።ወቸው ጉድ!!

በነዚህ ቀኖች አንዳች ነውር ቢገኝበትስ ?አዲዮስ ይባላላ።ይተዋል።ለመታረድ አይበቃም።ይጣላል።ደሞ ነውር ያልተሸከመን ሌላ በግ ፍለጋ ይወጣል።

አሁንም በተባረረው በግ ምትክ የመጣው ሌላው በግ እንዲሁ በቅጡ ይመረመራል። ገላው ከአንዳች ቁስል የጸዳ መሆኑ አሁንም እየተገላበጠ ለአስራአራት ቀን ሙሉ ይታያል።

ከዚህ ሁሉ ምርመሯ በኃላ መቼም አንድ ንጹህ በግ መገኘቱ አይቀር። ያ ምርመራውን ያለፈ በግ ታድያ 'የፋሲካ በግ 'ተብሎ ለመጠራት ይበቃል።እናም የህዝቡን ሐጥያትና ጦስ እምቡሳስ ሁሉ ተሸክሞ ሸክክክ ይደረጋል!ይታረዳል።ይሰዋል።ያኔ የህዝቡም በደል ይሰረያል።ሐጥያት ይወገዳል።ፋሲካ ይበሰራል!

ይህ እንግዲህ በእስራኤላውያን ዘንድ በየአመቱ የሚካሔድ የ'ስርየት በአል' ልምምድ ነበር።የአሮጌው ኪዳን መዝጊያና የአዲሱ ኪዳን መክፈቻ ብስራት ግን ይሔን ተደጋጋሚና አድካሚ በአል እስከወዲያኛው ያስቀረ ሆነ።ጉድ ነው!! ምን ተፈጥሮ?እንዲህ ነው ነገሩ።

ዮሐንስ 1 :29 " በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፡— እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ"

አሁን አዲሱ በግ እስራኤላውያን በበአላቸው እንደሚያቀርቡት አይነት በግ አይደለም።ይሔ በግ ከምድር የሆነ በግ አልነበረም።ይሔ በግ ከበጎች መሀል የተመረጠ በግም አልነበረም። ይሔ በግ ከሰማይ የመጣ በግ ነው።ይሔ በግ በአብ ዘንድ 'የምወደው ልጄ' በሚል ምስክርነት የታጀበ የእግዚአብሔር ልጅ እየሱስ ነው።

ታድያ ይሔ በግ ምንም ያህል በአብ ዘንድ የተመሰከረለት ሆኖ የመጣም ቢሆን በገዛ ፍጥረቶቹም ግን ተመረመረ። በሀይማኖት ሊቃውንት ተመረመረ።በህዝቡ ጭምር ተመረመረ። ማንነቱ ተመረመረ።መውጣት መግባቱ ተመረመረ።

ሺ ግዜ ሺ ይመርምሩት እንጂ ግን እነርሱ 'ስህተት'ከሚሉት ትምህርቱ በቀር በጉ እየሱስ በህይወት በኑሮው :በእለት እለት ምልልሱና በአካሔዱ ሁሉ የሚነቀፍበት የሌለ: ነውር የታጣበት :እጅ በአፍ የሚያስጭን ህይወት ባለቤት መሆኑ በግልጥ ታየ።

1 ጴጥሮስ 2 :22_23 "..እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ"

ይገርማል!!ምርመራው ውስጥ የሮም መንግስትም እጁን አስገባ። ጲላጦስም በመጨረሻ ሀያሉን የሮም መንግስት ወክሎ የምርመራውን ውጤት ለህዝብ አሳወቀ

ማቴዎስ 27 :23_24" ገዢውም፡— ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን፡ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ። ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ፡— እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።"

መልካም ነው!!ነውር የሌለው ለመስዋእት የሚበቃ በግ መሆኑ ከተረጋገጠ ዘንዳ ምን ቀረው ታድያ? መታረድ ነዋ።እንዲታረድ ደግሞ አንድ ድምጽ ከህዝቡ መውጣት ነበረበት። 'ይሰቀል' የሚል።አልቀረም።ወጣ።ህዝቡም አለ

ማቴዎስ 27 :22፤ "ጲላጦስ፡— ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፡— ይሰቀል፡ አሉ"

እንግዲህህዝቡ ሳያውቅም ቢሆን ለመታረድ የሚበቃ ነውር የሌለው የአዲስ ኪዳን በግ እየሱስ መሆኑን 'ይሰቀል' በማለቱ መሰከረ።

ኢየሱስ 'የፋሲካ በግ' መሆኑ እርግጥ ሆነናም ያንን አስጨናቂ የጎልጎታ መንገድ ተያያዘው። የህዝቡን ሐጥያት ተሸክሞ በቀራንዮ አናት ላይ መራራውን ሀሞት ተጋተ። የሞት ጽዋን ጠጣ። 'ላማ ሰበቅታኒ ነፍሴን ተቀበላት' እያለ አንቀላፋ።

ሞቱ የሞት መጋረጃን ቀደደ። የጥሉን ግድግዳ አፈረሰ።ጸሀይ በመጨለም የሞቱ ምስክር ታዳሚ መሆኗን አሳየች። የአዲስኪዳን በግ በሰማይና በምድር ፊት በመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ ታየ። ሐዋርያቶች ስለዚህ የአዲስ ኪዳን በግ እንዲህ አሉ "ነውርና እድፍ በሌለው የክርስቶስ ደም ታጥባችኃል"ወገኔ አሁን ንቃ።በጉ አንዳች ነውር የሌለው መሆኑ ስለአንተ እንጂ ስለራሱ አይደለም። እሱማ የነገስታት ንጉስ :የጌቶች ጌታ :የአለም ሁሉ ፈጣሪ ቃል ነው።:ጨረቃ እንኳን በፊቱ ንጹህ አይደለችም የተባለለት ቅዱስ የሚቀድስ ንጹህ የሚያጸዳ! ሆኖም ግን ስለአንተ ይሔን ሁሉ ሆኗል።እኛም ልጆቹ በሰማያት ያለፈ ሊቀ _ካህን አግኝተናል።ዕብራውያን 4 :14_15 "እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም"አሜን!!

ጥቂት ግዜያት በኖርኩበት ደቡብ አፍሪካ በተባለ አገር አንድ የንግግር ልማድ እንደነበራቸው ትዝ ይለኛል። 'Don't talk to me! talk to my lawyer"የሚል። "ከኔ ጋር አታውራ። እኔን አትነዝንዘኝ። ጠበቃዬን አናግረው" እንደማለት መሆኑ ነው።ወላ በጽሁፍ ታትሞ 'ስቲከር' ሆኖ መኪናቸው ላይ ሁሉ ይለጥፉታል።

ዛሬ ነዝናዥ አለብህ?የክስ ፋይል ከምሮ ገና በማለዳ ቤትህ ደጃፍ ላይ ተደንቅሮ በክስ የሚተከትክህ አለ?በህሊና እዳ የሚያስጨንቅ? ንገረው።'ከኔ ጋር አትጨቃጨቅ።ጠበቃዬን አናግረው' በለው።ጠበቃህ በ'ብሪፍ ኬዝ' ሳይሆን በደም የመጣ ነው።ከደምም ደግሞ ነውር በሌለው ደም ያጠበህ ከዚህ የተነሳም የርሱ ጽድቅ እንዳደረገህ እየነገረልህ ጠላትህን ልክ ያስገባልሀል።አንተ ብቻ በል 'ጠበቃዬን አናግረው'

አድፈሀል ረክሰሀል ?ዛሬ ወደ ጠበቃህ አንዴ ዞር በል።ንጽህና አይሰማህም?ማደፍ መቆሸሽ ይሰማሀል? ህሊናን በሚያጥብ ነውር በሌለው ደም መታጠብህን ቆም በልና አውጅ። ጌታ ሁሉን የሆነው አንተ በጠላት ፊት ቀና ብለህ እንድትሔድ ብቻ እንደሆነ እወቅ።

ዕብራውያን 9 :14 "ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?" አበቃ።ከዚህ በላይ ምን እንዲባል ትፈልጋለህ?

እንግዲህ ወገኖቼ በጉ ይህን ሁሉ የሆነው ላንተና ላንቺ ነው።የሆነውን የሆነው ደግሞ ለአመት አይደለም።ለዘላለም ነው።አሁን አመት እየተጠበቀ የሚነጻ ሀጥያት የለም።መንጻት መቀደስ መታጠብ በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው በየሰከንዱ ሆኗል።ሀሌሉያ!!

ዛሬ ከተከፈልልን ታላቅ ዋጋ ተነስተን በምስክርነታችን ቃል ማንኛውንም በኛ ላይ የተከፈተብንን የክስ ፋይል ወደ መዝገብ ቤት እንዲህ ብለን መለስነው።

"ነውር የሌለው :ኢየሱስ ክርስቶስ ነውር የሌለኝ አድርጎኛል"ብለን እንመስክር

12/16/2025
12/06/2025

ወደ ቃሉ እንመለስ !!

መቅረዝ የወንጌል ብርሀን ቤተ ክርስትያን
በመጋቢ ነህምያ ወ/አማኑኤል
አሜሪካ /ኦክላንድ

🌴"...የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም
ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል
እብ 4:12

¤በአሁን ሰአት ላሉብን ተግዳሮቶች ሁሉ መፍትሔው የእግዚአብሔር ቃል ነው።የሚበጀን ቃሉን መያዝ ነው።

¤ወደ እግዚአብሔር ቃል የሚያይ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚያይ ሰው ነው።

¤የእግዚአብሔርን ቃል የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።ወደ እግዚአብሔር ቃል የሚመለስም ብሩክ ነው።ምክንያቱም

🌴የእግዚአብሔር ቃል ይፈውሳል።
🌴የእግዚአብሔር ቃል ያጽናናል።
🌴የእግዚአብሔር ቃል ስብራትን ይጠግናል።
🌴የእግዚአብሔር ቃል ምሪት ይሆናል።
🌴የእግዚአብሔር ቃል ይመክረናል።
🌴የእግዚአብሔር ቃል ይመልሰናል።

¤የቃሉ ምንጭ መለኮት ስለሆነ በኛ ህይወት ውስጥ የሚሰራውን ሰርቶ ነገራችንን ሁሉ ድንቅ አድርጎ ይለውጣል።

"...በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።(ዮሐ 15:7)

¤የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ፍላጎት ስለሆነ በህይወታችን የሚፈልገውን በመስራት አዲስን ነገር በኛ ያደርጋል።

ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
11፤ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
ኢሳይያስ 55:10-11
¤በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ወደ እግዚአብሔር ቃል ማየት ይሁንልን።

🌲በመጨረሻም የምላችሁ"የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው"።ኤፌ 6:17

💥እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ።

ኑ ና ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበለን ጌታን በክብር እናምልክ
11/11/2025

ኑ ና ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበለን ጌታን በክብር እናምልክ

Address

3755 13th Avenue
Oakland, CA
94610

Telephone

+15106745440

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meqrez Gospel Light Church, Oakland CA, USA. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share