Holy Trinity EOTC Nashville, TN.

Holy Trinity EOTC Nashville, TN. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Holy Trinity EOTC Nashville, TN., Church, 2558 Couchville Pike, Nashville, TN.

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”ኢሳይያስ 53:5
04/11/2026

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”

ኢሳይያስ 53:5

04/06/2026
በዓለ ሆሣዕና 2026/2018 አ.ም. አከባበር በቅድስት ሥላሴ ናሽቬል ቴነሲ።
04/05/2026

በዓለ ሆሣዕና 2026/2018 አ.ም. አከባበር በቅድስት ሥላሴ ናሽቬል ቴነሲ።

02/17/2026

ዐቢይ ጾም (ጾመ ፵ ዘጾመ ክርስቶስ)
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
ይህ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ፵ መዓልትና ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳይጥፍ በትኅርምት የጾመው ጾም በመሆኑ “ዐቢይ ጾም” ተብሏል /ማቴ. ፬፥፬/፡፡ እኛም ጌታ የጾመውን ለማስታወስ፣ በረከቱን ለማግኘት፣ በግብር እርሱን ለመምሰል፣ የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን፡፡ ጌታችን የጾመው እቀደስ፣ እከብር ወይም እነጻ ብሎ ሳይሆን ለእኛ አርአያ ለመሆን ነው፡፡ ዐቢይ ጾም ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡
የዐቢይ ጾም ስምንት ሣምንታት
ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዐቢይ ጾም ለሚገኙት ሰንበታት ሁሉ የተለየ መዝሙር ሠርቶላቸዋል፡፡ ሰንበታቱም በመዝሙሩ ስም፡-
፩- ዘወረደ
፪- ቅድስት
፫- ምኩራብ
፬- መጻጉዕ
፭- ደብረ ዘይት
፮- ገብርኄር
፯- ኒቆዲሞስ
፰- ሆሣዕና ተብለው ይጠራሉ፡፡ /መጽሐፈ ድጓ/፡፡

የበረከትና የዕረፍት ዕለታት በመሆናቸው ከሥጋ ሐሳብና ሥራ ተለይተን በእግዚአብሔር ቃል በጸሎትና በዝማሬ ተግተን ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብባቸው ናቸው፡፡ ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡
በስምንቱ ሣምንታት ውስጥ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጾሙ የጾሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡
የዐቢይ ጾም ሥያሜዎች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዐዋጅ ከሚጾሙት ሰባቱ አጽዋማት አንዱና ትልቁ ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም በተለያዩ ሥያሜዎች ይታወቃል፡፡ የይኸውም፡- ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ኢየሱስ፣ ጾመ ሁዳዴ፣ ዐርባ ጾም በመባል ይታወቃል ፡፡ እነዚህንም እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን፡-

ዐቢይ ጾም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው ጾም ስለሆነ “ዐቢይ ጾም” ይባላል፡፡
ጾመ ሁዳዴ
በጥንት ዘመን ገባሮች ለባለርስቱ የሚያርሱት መሬት “ሁዳድ” ይባል እንደነበር ዐቢይ ጾምም ሠራኤ ሕግ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመውና ምእመናን ይህን እያሰቡ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ የሚጾሙት ስለሆነ “ጾመ ሁዳዴ” ይባላል፡፡
የካሣ ጾም
የቀድሞዎቹ ሰዎች አትብሉ የተባሉትን በመብላታቸው ከገነት ለመባረር ለውርደትና ለሞት ለሲዖል ባርነት ተዳርገዋል፡፡ ዳግማዊ አዳም የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በሆድ ምክንያት ድቀት አግኝቶት ረኃበ ጸጋ ደርሶበት የነበረውን ቀዳማዊ አዳምንና ልጆቹን በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠን፡፡ ስለዚህ ዐቢይ ጾም “የካሣ ጾም” ይባላል፡፡
የድል ጾም
አዳምና ሔዋን በገነት ሳሉ በምክረ ከይሲ ተታለሉና ድል ሆኑ፤ ተስፋ አበውን ሊፈጽም የመጣ ክርስቶስም ዲያብሎስን ድል ያደርግልን ዘንድ ተጠምቆ ሳይውል፣ ሳያድር ከዚህ ዓለም ርቆ ወደ ገዳም በመሄድና ከሰው ተለይቶ ፵ መዓልትና ሌሊት በመጾም ዲያብሎስን፣ ፈቃደ ሥጋችንን ድል የምናደርግበትን ኃይል አጎናጸፈን፤ ስለዚህ ዐቢይ ጾም ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ ድል የተነሡበት ዲያብሎስ ያፈረበት ስለሆነ “የድል ጾም” ይባላል፡፡
የመሸጋገሪያ ጾም
ነቢዩ ሙሴ ፵ ቀንና ሌሊት በሲና ተራራ ጾሞ እሥራኤል ዘሥጋን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት ያሸጋገረ ሲሆን፤ ክርስቶስም እሥራኤል ዘነፍስ የተባልነውን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ፵ መዓልትና ሌሊት በመጾም ያሸጋገረን በመሆኑም “የመሸጋገሪያ ጾም” ተብሎ ይጠራል፡፡
ጾም አስተምህሮ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ድካም ሁሉን ማድረግ ሲቻለው መምህረ ትሕትና ነውና አርአያውን ሊተውልን ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ እኛን ወደ እርሱ በፍቅረ ይስበን ዘንድ አስቀድሞ ወደ እኛ መጣ፡፡ መጥቶም ረኃባችንን ተራበ፣ ድካማችንን ደከመ፣ ፈተናችንን ተፈተነ፡፡ ስለዚህ በጾሙ ትሕትናን ትዕግሥትንና ድል ማድረግን ስላስተማረበት ጾሙ “ጾመ አስተምህሮ” ይባላል፡፡
ቀድሶተ ገዳም
እነ ዮሐንስ፣ እነ ኤልያስ የኖሩትን የብትሕውና ኑሮ ለባሕታውያን፣ ለመነኮሳት ባርኮ ስለ ሰጠ፤ ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ በገዳም ከአራዊት ጋር ኖሮ በዲያብሎስ ተፈትኖ ድል አድርጓልና ጾሙ “የቀድሶተ ገዳም ጾም” ይባላል፡፡
የሥራ መጀመሪያ ጾም
ጌታችን የማስተማር ሥራውን ከመጀመሩ፣ አንቀጸ መንግሥተ ሰማያትን ከማስተማሩ አስቀድሞ የጾመው በመሆኑም “የሥራ መጀመሪያ ጾም” ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለሆነም ሐዋርያት እርሱን አብነት አድርገው ሠራቸውን በጾም ጀመሩ፡፡
እንደ ማጠቃለያ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጾም የጾመው ለአብነት፣ ለማስተማር፣ ለአርዓያ ነው። በዚህ ታላቅ ጾም ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ፣ ከሰው የሥጋ ጠባይ የሚመጣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ድል የተነሱበት ነው። እኛም ይህን እያሰብን በተለያየ መንገድ የሚመጣብንን ፈተና ለማራቅ ከዚህ ታላቅ ጾም በረከት እንድናገኝ እንጾማለን። ጸልዮ ጸልዩ፣ ጾሞ ጹሙ ብሎናል። /ማቴ.፮፥፲፮/። ጾም ለክርስቲያኖች ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ነው። ስለዚህ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረን ይህን ጾም ከምግብ ለመከልከል ጋር ጸሎትን፥ ስግደትን፣ ምጽዋትንና የንስሐ ዕንባን ጨምረን እንጹመው።

ጌታችንና ነቢያት፣ ሐዋርያት የተውልን መንፈሳዊ መሣሪያ ነውና፡፡ እንግዲህ ዐብይ ጾም ማለት ጌታ ስለኛ ባየው መከራ የምናዝንበት፣ በሰጠን ኃይል ከሰይጣንና ከፈቃደ ስጋ የምንዋጋበት፣ በበደልነው ገብቶ የካሠልንን እያሰብን ዳግም ወደ ኃጢአት ላንመለስ ቃል የምንገባበት፤ አርአያ ሆኖ ከሠራልን ሥርዐት፤ ከኖረልን ሕይወት የምንማርበት፤ ራሳችንን ለፋሲካው በግ ለሥጋ ወደሙ የምናዘጋጅበት ሰሞን ነው፡፡ በመሆኑም በሰላም፣ በፍቅር፣ በትሕትና ጾመን ለበዓለ ትንሣኤው በሰላም እንዲያደርሰን፣ ጾመን ለማክበር እንዲያበቃን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ፍትሐ ነገሥት
✍️ መጽሐፈ ድጓ
✍️ ሃይማኖት አበው
✍️ ስንክሳር
✍️ የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ
✍️ በዓላት
✍️ ጾም፣ ጸሎት ምጽዋት
✍️ Enclopedia of Aethiopica

የ2018 ዓ.ም የጾመ ነነዌ ከጥር 25 - 27 ይቆያል። ይህ ወቅት የንስሐ፣ የጸሎትና የእግዚአብሔር ምሕረት የሚገለጥበት ቅዱስ ሳምንት ነው። የነነዌ ሰዎች በጾም ከጥፋት እንደዳኑ ሁሉ፣ እኛ...
02/01/2026

የ2018 ዓ.ም የጾመ ነነዌ ከጥር 25 - 27 ይቆያል። ይህ ወቅት የንስሐ፣ የጸሎትና የእግዚአብሔር ምሕረት የሚገለጥበት ቅዱስ ሳምንት ነው። የነነዌ ሰዎች በጾም ከጥፋት እንደዳኑ ሁሉ፣ እኛም ወደ ታላቁ ጾም ከመግባታችን በፊት በንስሐ ታጥበን የእግዚአብሔርን ምሕረት እንድንቀበል ታዝዞልናል።

01/24/2026

Girls day out at In-N-Out 🤍🍔!!!
So grateful for these amazing young women, their hard work, dedication, and commitment to serving the church never goes unnoticed. A small thank-you for hearts that serve so faithfully. We appreciate you more than you know 🙏🏽💛

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።Happy Feast of Theophany!
01/20/2026

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

Happy Feast of Theophany!

01/11/2026
01/09/2026

የጥምቀት በዓል በናሽቬል ቴነሲ
ከተራ፤ ጥር ፲ ፤ ፳፻፲፰ ዓ.ም.
January 18, 2026 4PM - 7PM

በዓለ ጥምቀት፤ ጥር ፲፩ ፤ ፳፻፲፰ ዓ.ም.
January 19, 2026 1AM - 12PM

Nashville Debre Keranio Medhanialem EOTC
4506 Nolensville Pk, Nashville, TN 37211

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። Happy & Blessed Feast of Nativity!
01/07/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። Happy & Blessed Feast of Nativity!

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ጥሪ!
01/03/2026

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ጥሪ!

Address

2558 Couchville Pike
Nashville, TN
37217

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Holy Trinity EOTC Nashville, TN. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Holy Trinity EOTC Nashville, TN.:

Share

Category