Arcbishop Abune Selama foundation the Bale Goba

Arcbishop Abune Selama foundation the Bale Goba Mission: In raising funds for the finish up of the Sunday school building in Blae Goba.

የጎባ ልጅ
09/06/2026

የጎባ ልጅ

አዲስ ዓመት አዲስ መዝሙር

09/03/2026
08/29/2026

ነገረ ጉባኤ
በቤተክርስቲያን የሚደረግ ጉባኤ ግብ ይዞ መነሳት አለበት። የሚጋበዙ መምህራን ለአካባቢው ምዕመናን ጥያቄ መልስ የሚሆኑ ርዕሶች ሊሰጣቸው በተመጠነ ሰዓት የተዘጋጁትን ትምህርት ሊያቀርቡ ይገባል። ከ40 ደቂቃ ያልበለጠ ሰዓት ለሰሚዎቹ ምቹ ትምህርት ማቅረቢያ ጥሩ ጊዜ ነው።የጉባኤው ባራኪና አልባሽ አባቶች በአጭር ንግግር መጠቅለል አለባችሁ። ያረዝማሉ እየተባሉ የሚታሙ እንዳንሆን ሰሚዉም መልእክታችንን እንዲወድ። ዘማሪያን ትምህርቱን የሚደግፍ መዝሙር በተመጠነ ጊዜ ማቅረብ አገልግሎቱን ግልጽ ያደርገዋል። ጉባኤው ከፖስተር ያለፈ ጠንካራ ቅስቀሳ ይፈልጋል። ሰውን ከዓለም እጅ ፈልቅቆ የሚያወጣ ጥሪ ያስፈልጋል። የአውደ ምህረት ዝግጅት የእግዚአብሔርን ክብር በሚመጥን መንገድ ተለፍቶ ተደክሞ ሊዘጋጅ ይገባል። ንጹህ የተዋበና የተረጋጋ አውደ ምህረት ሰሚዎቹን ይጠራቸዋል። የድምጽ መሳሪያ ባለሞያዎች የአገልጋዮቹን ድምጽ እየሰሙ ከፍ ያለውን ድምጽ መመጠን ያነሰውን መጨመር አለባቸው። አገልጋዮች የምናወጣው ድምጽ ለሰሚዎች ተመጣጣኝ መሆኑን ማየት አለብን። ትልልቅ ሰዎች እና ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ ስለሚረበሹ ለሰሚዎቸ ማዘን አለብን። ማይኩና እና ተናጋሪው መሃል የትንፋሽ ጋፕ ያስፈልጋል። ማይክ ጎርሶ መናገር የተናጋሪውን ድምጽ ሰሚውንና መሳሪያውን በጣም ያበላሻል። የመዝሙር መሳሪያ ከሆኑት አንዱ ና ለዘማሪያን ዋና የሪትም መሪ ከበሮ ነው። ከበሮ መቺ ባለሞያዎች እንደ ክራርና መሰንቆ ተለይተው መዘጋጀት አለባቸው። ከበሮው ረግቦ ካርቶን እንዳይሆን የእግዚአብሔር ክብር መገልገያ ነውና አስወጥሮ ጥራቱን መቆጣጠር ይገባል። ያለ ልብሰ ስብሐት ዘለው ከበሮ የሚይዙትን መቆጣጠር የመድረግ አጋፋሪዎች ስራ መሆን አለበት። መርሐ ግብር መሪ ብቻ ሳይሆን የመድረክ አጋፋሪ ወጣቶች መመደብ አለበት። መርሐ ግብር መሪ አሸጋጋሪ እንጂ ሰባኪና ትምህርት አልባሽ አይደለም። በየመሃሉ በስመ አብ ማለት የለበትም። ጠቀለል አድርጎ መመረቅ አለበት። ቲክቶክ ላይ መቀመጥ የለመደ ህዝብ ስለምናገለግል ምጥን ያለ ቁጥብ መሆን አለበት። ጉባኤ የስብከተ ወንጌል የሰንበት ትምህርት ቤትና የሰበካ ጉባኤ የጋራ ሥራ ነው። አይመለከተኝም የሚል የእግዜር ሰራተኛ አይኑር። ባራኪው ጌታ የልባችንን ዝንባሌ እያየ ነው እጁን የሚዘረጋልን። ይመርበት ይክበርበት እያልን ከተጋን እግዚአብሔር ከፊታችን መሰላል ይዘረጋልናል። እንዳይታጎል ስናገለግል ግን ባዶ ድካም ብቻ ነው የሚተርፈን። የአገልግሎት ልብስ ተጎናጽፈን እንውጣ። እግዚአብሔርን እንደምንወድና እንደምናከብር ማሳያ ነውና።
ህዝቡ ቆሞ ሲዘምር የመድረክ ላይ ካህናትና ሹማምንት ቆመን መዘመር አለብን። ዘማሪ ሲዘምር ሰባኪ ሲሰብክ ሌላው እያወራ የእግዚአብሔርን ዓውደ ምህረት ተመልካች አልባ ማስመሰል ልክ አይደለም። አክሊላችንን አውርደን የምንሰግድለት ክርስቶስ መድረክ ነው። ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ጌታ ዓውደ ምህረት ስለሆነ በብርሃን መድመቅ አለበት። የሚዲያ ባለሞያዎች ነጠላ ለብሰው ካሜራችሁ ና ሰራተኞቻችሁ ህዝብን እንዳይሸፍኑ ጀርባ ሳይሰጡ ተጠንቅቀው መስራት አለባቸው። ምዕመናን በሰዓት መገኘት፣ ድምጽ አውጥቶ መሳተፍ፣ በገንዘብ ማገዝ የሚጎድለውን እያዩ መሸፈን አለባቸው። የተጣሉ ሰዎች በጉባኤ አብረው ከሰሩ ጉባኤው ድንዝ ይላል። ታርቀው ጸልየው ይውጡ። ሁሉ አገልጋይ ከማገልገል በፊት ሰወር ብሎ መጸለይ ሲያልቅም ሰወር ብሎ ማመስገን እግዚአብሔር አብሮ እንዲሰራ ይጋብዘዋል።
ስሙን የምታገለግሉ ሁሉ ሰላምና በረከት ይብዛላችሁ።
አካፍሉት

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7:00 በአጋፔ ዘኦርቶዶክስ ዩቱብ ይጠብቁን
05/05/2026

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7:00 በአጋፔ ዘኦርቶዶክስ ዩቱብ ይጠብቁን

ነገ በዕለተ መድኃኒዓለም 7:00 ይወጣልየተወደዳችሁ ለሌሎች አካፍሉት
05/04/2026

ነገ በዕለተ መድኃኒዓለም 7:00 ይወጣል
የተወደዳችሁ ለሌሎች አካፍሉት

Address

Stockwell Drive
Murfreesboro, TN
37128

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arcbishop Abune Selama foundation the Bale Goba posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Arcbishop Abune Selama foundation the Bale Goba:

Shortcuts

Share