Shiloh Ethiopian Eritrean Church New Orleans

Shiloh Ethiopian Eritrean Church New Orleans Fellowship of believers in the Lord Jesus Christ in New Orleans and area. Sunday service
9:45 AM
2001 Airline Dr
Metairie, LA 70001

02/28/2026

Come along and worship the Lord with us this Sunday! Service starts at 10 am! You’ll always leave with something from the house of the Lord! He will speak to you and guide you, if you let him!

Address is 1915 airline Dr. Metairie,LA.
Inside of Celebration!

ባየው ባየው አይለወጥም ፍቅሩ::
ባየው ባየው አይቀዘቅዝም መውደዱ::
ባየው ባየው አይለወጥም እንክብካቤው::
እንደ ትናንቱ እንደ ልጅነቴ መውደዱ ያው ነው::

02/23/2026

Sunday Feb 22,2026

በዘመኔ ሁሉ
የማልመልሰው ውለታ አለብኝ
የእግዚአብሔር ልጅ
ጌታ ኢየሱስ ለኔ ያደረገልኝ
ብዘረዝረው ደግሞም ባወራው ከቁጥር ሁሉ በዛ
እኔም በአለኝ ሀይሌ
ምስጋና ለእሱ ላብዛ

02/23/2026

እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው።
በዛሬው እለት የነበረን አምልኮ::
Sunday Feb 22, 2026

~ 2025ም እንደ ሌሎቹ ዘመናት ከነክፋቱ ማለፉ ነው። በጣም ክፉና ተለዋዋጭ ቀናትን ይዞ መጥቶ ነበር ብዬ ብደመድም ከእኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። ደግነቱ ቶሎ ማለፉ። ክፋቱ ግን ከሱ በ...
01/01/2026

~ 2025ም እንደ ሌሎቹ ዘመናት ከነክፋቱ ማለፉ ነው። በጣም ክፉና ተለዋዋጭ ቀናትን ይዞ መጥቶ ነበር ብዬ ብደመድም ከእኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። ደግነቱ ቶሎ ማለፉ። ክፋቱ ግን ከሱ በሚከፋ ሌላ ዓመት መተካቱ።~

>>>የሚመጣውም የሚገፉ፤ ቢችሉ ሊጥሉ እና ሊነጥሉ የሚሞክሩ ሞገደኛ ነጣቂ ጊዜያትን ያቀፈ እንደሚሆን ማጤን አለብን። >>>በዓለም ሳለን ይህ ይሆን ዘንድ የግድ ነው ተብሎ ተጽፏል።

>>>ደግነቱ የእኛ ተስፋ መለዋወጥም ሆነ እርጅና የማይሞክረው እግዚአብሔር መሆኑ በጀን። “ይብላኝለት ጌታ ለሌለው” እንዳለችው ነው።

~~ነገሩ ሰቆቃወ ኤርምያስ ምዕራፍ 3:21-25
እንደሚመክረን ነው~~~~~~

"21 ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ
በተስፋ እሞላለሁ።
22 ይኸውም ሳንጠፋ የቀረነው
የእግዚአብሔር ምሕረት ከቶ
የማያቋርጥና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ
ሆነ ነው። 23 እነርሱ በየማለዳው
ይታደሳሉ፤ ስለዚህ የአንተ ታማኝነት
ታላቅ ነው። 24 የእኔ አለኝታ
እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርሱን ብቻ
ተስፋ አደርጋለሁ። 25 እግዚአብሔር
በተስፋ ለሚጠባበቁትና
እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው።”

ስለዚህ እግዚአብሔርን ብቻ ተስፋ የምታደርጉ ቅዱሳን በዚህ የምስጋና ጸሎት
ተባበሩኝ።

እግዚአብሔር የሰማይ አባት አንተ ብቻ
ታማኝ ነህ። አትለወጥም፤ ዓመታትህም አያረጁም። ታድናለህ፤ ትታደጋለህ፤ ታሻግራለህ። በዚህ ባለፈው ዓመት በምህረትህ ብዛት በቤትህ እንዳኖርከን በመጭዎቹ ዘመናትም አንተኑ ብቻ ተስፋ እናደርጋለን። ራራልን፤ በፊትህ ደስታ አጥግበን- በህይወት እንኖራልን።
የልጅህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለቤተሰቦቻችን፣ ለጎረቤቶቻችን፡ ለህብረተሰባችንና ለምድራችን ህይትን እንዲሰጥ እንለምንሃለን።
በጭንቀትና በደዌ ለተያዙ ሁሉ፣ በእስራት ላሉ ሁሉ፤ በስደት እና በመከራ ለሚያልፉት ሁሉ እንድትራራ እንለምንሃለን።
ሁሉ ለስምህ ክብር ይሁን።
ጌታም ክርስቶስም በሆነው በውድ ልጅህ በኢየሱስ ስም።

አሜን

አቤት ጌታ ባለመላ Telegram - https://t.me/AbetgetaBalemelaAlbumBotApple Music - https://music.apple.com/us/album/abet-geta-balemela/1629903357Spotify - https://ope...

09/25/2025

የኒው ኦርሊንስ ነዋሪ በነበረው በሳሙኤል ሽፈራው ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ህልፈቱን አስመልክቶ ከኮሚኒቲው የተላለፈ መልእክት ተመልክታችሁ ምላሽ እንድትሰጡ እናበረታታችኃለን!

"የተከበራችሁ የኒው ኦርሊዬንስና አካባቢው ምእመናን ምእመናት እንዲሁም ነዎሪዎች በሙሉ

ውንድማችን ሳሙኤል ሽፈራው (ሳሚ) በደረሰብት ድንገተኛ ህማም ምክንያት በዛሬው እለት 09/24/2025 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል
ሳሚ ከአስራ አራት አመት በፊት ከአትላንታ ወደ ኒው ኦርሌንስ ሲመጣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ባለቤትና Chef በመሆን እንዲሁም በtransportation industry በመሰማራት ከተማችንን በፍቅር ያገለገለ ወንድማችን ነበር

ምንም እንኳን የሳሚ የመጨረሻ ማረፊያው አትላንታ ቢሆንም እዚህ ኒው ኦርሌንስ ውስጥ በእጅ የበላን እና ብዙ ወዳጅ ስላው ቅዳሜ September 27 በ 10:00 am St Mark Coptic Orthodox Church ሙሉ የፍትሃተ service ስለሚደረግለት በሰአቱ ተገኝታቹህ እንድትሸኙት በትህትና እንጠይቃለን
መቼም እዳው ለነዋሪው ስለሆነ እ ኛ የኒው ኦርሌንስ ወዲጆቹ እንደ ባህላችን የተቻለንን ያህል ለልጁ ሄኖክ(Henock) በቀጥታ በ Zelle
470-535-1008
እንድትልኩ በትህትና እንጠይቃለን

በወድማችን ማለፍ ሁላችንም የተሰማን ሀዘን በጣም መራራ ነው የወድማችንን ነፍስ በአፅደ ገነት ያስፍርልን

በቅድሚያ በጣም እናመሰግናቹሀለን ቸሩ አምላክ መላውን ቤተ ሰባቹህን ከክፉ ይጠብቅ ::

አሜን 🙏🏽"

05/04/2025

Come to church today!
At 09:45 AM
At 2001 Airline Dr inside Celebration Church
And hear the message of Jesus!
We will be waiting for you! God bless you!

03/02/2025

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ዛሬ March 2 ከ9:45 pm ጀምሮ በሚኖረን የፀሎት የዝማሬና የቃል ጊዜ
በአንድነት እንድንገለገል ተጋብዛችሃል::
ኑ::
ለንጉሱ እንዘምር እናመስግን
በቅዱስ ቃሉም እንታነፅ::
ተባረኩ::

2001 Airline drive. Inside Celebration Church

02/08/2025

“ እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።” ቆላስይስ 3:13፤

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
የፊታችን እሁድ Feb 2nd ከ9:45 pm ጀምሮ በሚኖረን የፀሎት: የዝማሬና የቃል ጊዜ በአንድነት እንድንገለገል ተጋብዛችሃ:: ኑ ለንጉሱ እንዘምር እናመስግን በቅዱስ ቃሉም እንታነፅ::
ተባረኩ::

09/13/2024

ሻሎም ቅዱሳን
እግዚአብሔር በምህረቱ ከፍራንሲን አደጋ ስላተረፈን ስሙ ይባረክ:: እርሱ ታዳጊ አምላክ ነውና::
የምናመልክበት የሰለብሬሽን ቤተክርስትያን ግን ጎርፍ ገብቶታል::
መሪዎቿም ክፍሎቹን ለማጽዳት ትብብር ጠይቀዋል::
ምእምናን ነገ ከጥዋቱ 8 ሰአት ጀምሮ የጽዳት ዘመቻ ያደርጋሉ::
አቅምና ፈቃዱ ያለን እንድንተባበር አደራ ይሁን!

ተባረኩ

08/24/2024

“ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።”
‭‭2 ሳሙኤል‬ ‭22‬:‭4‬ ‭

08/20/2024

-ሴይጣን ሰውን አታለለ
ሰው በሐጢያት ወደቀ

-እዚአብሔር በ ሰው እና በ ሴይጣን መሀል ጠላትነትን ለዘለአለም አስቀመጠ

-እግዚአብሔር አዳኝ እንደሚመጣ ተስፋን ሰጠ

-ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር ይመጣል ያለው ተስፋ አዳኝ የሆነው እየሱስ ከድንግል ማሪያም በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ተወለደ

-እየሱስ ስለ አለም ሁሉ ሀጢያት እራሱን አሳልፎ ሰጠ:: ስለ ሀጥያታችን ሞተ::
ሴይጣን የሰራውን ስራ አፈረሰ::ያበላሸውን አስተካከለ::

-በማመን ብቻ ያውም እየሱስ በእኔ ፈንታ ስለ ሀጥያቴ እንደሞተ ይህን ቃል ወደልብ በመቀበል እና በማመን ተስፋንም በእየሱስ ላይ በመጣል ሰው ከሀጥያቱ ነፃ ይሆናል::

-ስለዚ ሴይጣን ሊከስ ሲመጣ የሚከስብት ሀጥያት የለም:: ምክንያቱም ሀጥያቴን ተሸክሞ አየሱስ የሀጥያቴን ደሞዝ በኔ ፈንታ ተቀብሎልኛል::

ጠበቃ አግኝቻለው::

መፅሐፍ ቅዱስም እንደሚለው በ 1ኛ ዮሃንስ መልእክት ምእራፍ 3 ቁጥር 9
“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።" ይላል ::

እንዲሁም ቁ16 "እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል"

ቁ23 "ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ "

የጌታ መልአክም ለዮሴፍ እንዳለው በማትዮስ ወንጌል እንደተጻፈ

"እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፡— የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።"

እየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሀጥያት ይድናል:: አሜን::

Address

2001 Airline Drive
Metairie, LA
70001

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shiloh Ethiopian Eritrean Church New Orleans posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category