01/25/2023
የተዋሕዶ ልጆች እግዚአብሔር ቤቱን ሊያጸዳ ሲል ከቅርንጫፉ ሳይሆን ከላይ ከግንዱ ጀመረ ይህ ድንቅ ስራ ነው አትፍሩ አትደንግጡ እውነቱን ልንገራችሁ ጽድቁም ሐጢአቱም ፥ምሁሩም ደንቆሮውም፥ ንጽህናውም ርኩሰቱም፥ ሙስናውም ፥ዘረኝነቱም ------ያለው ከእኛው ቤት ነው ። ያለው ሲጀመር ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃገሩን የማይወድ ሃይማኖት የሌለው የከሰረ ትውልድ አይኖርባትም ።ከነዓንን ለእስራኤል ከማውረሱ በፊት ፌርዛውያንን ኢያቡሳውያንን------ ከምድሪቱ አስወግዶ ነበር ዘፍ15፥16
የተዋሕዶ ልጆች ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሴ ሲመራው የነበረ ህዝብን ይመስላል --- የሚያጉረመርም የግብጽን ሃጢአት የሚያስታውስ ቅድስና የሌለው የ40 ቀን ጉዞ 40 ዓመት የሆነብን ዘጸ21፥1ጀምሮ አንብቡት
ስለዚህ ኢያሱ የሚመራው ህዝብ ለመምጣት የሙሴ ህዝብ መወገድ አለበት ነባራዊው ሁኔታ እየታየ ነው
የኢያሱ ህዝብ ግን ኢያሱ 1፥16 ----ያዘዝከንን ሁሉ እናደርጋለን የሚሉ ነበሩ (ከቁጥር1-ፍጻሜው አንብቡት) በአጠቃላይ እግዚአብሄር የራሱን ህዝብ ይፈልጋል 10ቱ ቃላትን እና 6ቱ ቃላተ ወንጌልን የሚፈጽምለትን ያዘጋጃል