Ethiopia Orthodox church.

Ethiopia Orthodox church. Mostly it used to religion

ዕርገተ ክርስቶስ      “አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ” /መዝ ፵፮ ፥ ፭/።                   እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ !!! መ/ር ጌታቸው በ...
05/21/2026

ዕርገተ ክርስቶስ
“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ” /መዝ ፵፮ ፥ ፭/።
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ !!!

መ/ር ጌታቸው በቀለ

የጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓል “ዕርገት” ይባላል፡፡ ዕርገት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡
ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት ለአርባ ቀናት እየተገለጸ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡

ዘመነ ዕርገት

በዓለ ዕርገት በየዓመቱ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡ በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም “ዘመነ ዕርገት” ተብሎ ይጠራል፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(1948)፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ ገጽ ፯፻፷/፡፡

ዐርገ በስብሐት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ ዕለቱን ወደ ሰማይ አላረገም፡፡ ዐርባ ቀን ለሐዋርያት በሥጋ እየተገለጠና እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት እያስተማራቸው ቆየ፡፡ በዐርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን እስከ ቢታንያ አወጣቸው፡፡ እጆቹን አንሥቶ ባረካቸው፡፡ በአርባኛው ቀን ሐዋርያትን ሰብስቦ ዓለምን ዞረው እንዲያስተምሩ መመሪያ ሰጥቶ ለዚህም ኃይል የሚሆናቸው መንፈስ ቅዱስን እስከሚልክላቸው ድረስ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዝዞ ዐረገ፡፡ “እነርሱ በተሰበሰቡ ጊዜ ጌታ ሆይ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ ይኸውም “አቤቱ በዘሩባቤል የሄደችውን መንግሥት ለእስራኤል ልጆች የምትመልሰው መቼ ነው?” ሲሉት ነው፡፡ እርሱም “አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውንና ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልሰጣችሁም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፣ በኢየሩሳሌም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” አላቸው፡፡ “…ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው” እንዲል /ሐዋ.፩፥፩-፱/፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፤እነሆ ነጫጭ(ብሩህ) ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በሰው አምሳል ተገልጠው በአጠገባቸው ቆሙ፡፡ “የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን፣ በሥልጣን በቅዳሴ ሲያርግ እንዳያችሁት ዳግመኛ በብርሃን በሥልጣን በቅዳሴ ሲመጣ ታዩታላችሁ” አሏቸው፡፡

የጌታችን ዕርገት በነቢያት ትንቢት

የጌታችን ዕርገቱ በነቢያት አስቀድሞ የተነገረ ነው፡፡ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ ስለገለጠላቸው ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ (በይባቤ መላእክት፣ በቅዳሴ) ዐረገ” ብሏል /መዝ. ፵፮፥፭/፡፡ ዳግመኛም “ወደ ላይ ዐረግህ ምርኮን ማረክህ” ብሏል /መዝ.፷፯፥፲፰/፡፡ ሦስተኛም “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ላረገ ለእግዚአብሔር ዘምሩ” በማለት የዕርገቱን ነገር አስቀድሞ ተናግሯል /መዝ.፷፯፥፴፫/፡፡ ከዚህም የምንረዳው “እግዚአብሔር ዐረገ” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት መስክሯል፡፡

የጌታችን ዕርገት በኃይሉና በሥልጣኑ

አዳም በተፈጠረ በዐርባ ቀኑ አግኝቶ ኋላ በምክረ ከይሲ ያጣውን የጸጋ ልጅነትን እንደመለሰለት ለማጠየቅ፤ ለዐርባ ቀናት ለሐዋርያት እየተገለጸ መነሣቱን ሲያስተምራቸው ከቆየ በኋላ፤ በዐርባኛው ቀን ሁሉንም ወደ ቢታንያ አውጥቶ በአንብሮተ እድ ባርኮ፣ የሥልጣነ ክህነትን ጸጋ ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ዐርጓል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማረጉ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት ለመላክ፣ የባሕርይ አምላክነቱን ለመግለጽ በተዋሐደው ሥጋ በክብር እንዳረገ ዳግመኛ በታላቅ ግርማ ዓለምን ለማሳለፍ ተመልሶ እንደሚመጣ ለማጠየቅ ነው፡፡
ጌታችን ያረገው ከደብረ ዘይት ተራራ ነው /ሉቃ.፳፬፥፶-፶፫/፡፡ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ሲያስተምር “እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?” በማለት እንደገለጸው፤ ዕርገቱ ክብሩ በሚገለጽበት በየማነ አብ፣ በዘባነ ኪሩብ ለመቀመጥ ነው /ዮሐ.፮፥፷፪/፡፡ ይህንንም ቅዱስ እስጢፋኖስ “እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” በማለት ገልጾታል/ሐዋ. ፯፥፶፯/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም “…በሥጋ የተገለጠ፣ በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ” ሲል ገልጾታል/፩ኛ ጢሞ.፫፥፲፮/፡፡ /አባ ጎርጎርዮስ (1974)፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፡፡ አዲስ አበባ፤ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታተመ፤ ገጽ 131/፡፡

የጌታችን ዕርገት ልዩ የሆነበት ምሥጢር

የጌታችን ዕርገት አስቀድመው ካረጉ ከእነ ኤልያስ፣ ከእነ ዕዝራ ሱቱኤል፣ ከእነ ሄኖክ ይለያል፡፡ እነርሱ ዐረጉ ቢባሉ በራሳቸው ሥልጣን አይደለም፡፡ ሄኖክን እግዚአብሔር እንዳሳረገው በኦሪት ዘፍጥረት ተገልጾ ይገኛል፡፡ “ሄኖክ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና” ይላል /ዘፍ.፭፥፳፬/፡፡ ዕዝራ ሱቱኤልንም መላእክት ወደ ብሔረ ሕያዋን እንዳስገቡት ተገልጿል፡፡ “ይህን ሁሉ ጽፎ ያን ጊዜ መላእክት ዕዝራን ይዘው እንደሱ ያሉ ደጋግ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ብሔረ ሕያዋን ወሰዱት” ይላል /ዕዝራ ሱቱኤል ፲፫፥፵፱/፡፡
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላካዊ ኃይሉና በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ ወደ ሰማይ የወጣው በኃይሉና በሥልጣኑ ነው፡፡ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ ሄኖክ ያረገው በራሱ ኃይል ሳይኾን እግዚአብሔር ወስዶት ነው/ዘፍ.፭፥፳፬/፡፡ ነቢዩ ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ያረገው በራሱ ኃይል ሳይሆን እግዚአብሔር ወስዶት ነው/፪ኛ ነገ.፪ ፥፲፩/፡፡ እኛንም በትንሣኤ ዘጉባኤ ነፍሳችንን ከሥጋችን አዋሕዶ ትንሣኤ ዘለክብር አስነሥቶ ወደ ሰማይ እንደሚያሳርገን እናምናለን፡፡ ይህንንም ራሱ ባለቤቱ “እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትኾኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኀዋለሁ በማለት እውነተኛ ተስፋ ሰጥቶናል” /ዮሐ.፲፬፥፫/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና” ያለው ለዚህ ነው /ፊል.፫፥፪/፡፡
ቅዱሳን አባቶች ሃይማኖታቸው የጸና ምግባራቸው የቀና የክርስቶስን አምላክነትና የማዳኑን ምስጢር ቅዱሳት መጻሕፍትን መረጃ በማድረግ በጸሎተ ሃይማኖት ድንጋጌያቸው ገልጸውልናል፡፡ የ318 አባቶች የሃይማኖት ውሳኔ በመጨረሻው አንቀጽ “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ፤ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኮንን ሕያዋነ ወሙታን ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ” (በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ዳግመኛም በክብር ይመጣል በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ፤ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም፡፡) ብለው ወስነዋል፡፡ ወልድ ሰው የኾነበትን ቅዱስ ዓላማ ፈጽሞ ወደላከው ወደ አባቱ በክብር ዐረገ፤ በክብር ዙፋኑም ተቀመጠ፤ የወረደው ሌላ የዐረገው ሌላ አይደለም ለማለት ዐርገ በስብሐት ሲሉ አባቶች ተናገሩ፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስም “ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ ነው” ሲል የሰው ልጅ ክርስቶስ በባሕርይ ክብሩ በመለኮታዊ ሥልጣኑ ሁሉን ለማድረግ የሚችል ሁኖ በሰማይ እንደሚኖር ገልጦ ተናገረ /ዮሐ.3፣13/፡፡

በዓለ ዕርገት በቤተክርስቲያን

ዕርገት በምእመናኑ ዘንድ እንደ ትንሣኤና ልደት ዝግጅት ባይደረግበትም በቤተክርስቲያን ግን የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥበት ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ይባቤው የሚደረግበት ዕለት ነው፡፡ /ብርሃኑ አድማስ (2002)፡፡ በዓላት፡፡ አዲስ አበባ፤ ሜጋ ማተሚያ ቤት፤ ገጽ 88/፡፡ ዕለቱ በቤተክርስቲያን ትውፊቷ መሠረት ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ክህነትን የሰጠበት በመሆኑ ልዩ መታሰቢያነትና ምስጢር ያለው ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጌትነቱን ሥርዐት የፈጸመበት፣ ከሊቀ ጳጳስነት ጀምሮ እስከ ዓፃዌ ኆኅትነት ያለውን መዓርግ የሰጠበት፣ ወደ ላከው ወደ ባሕርይ አባቱ ወደ አብ ያረገበት በአብ ዕሪና የተቀመጠበትን በዓለ ዕርገትን ማክበር እንዲገባ ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት አዘዋል፡፡ “ሥርዐቱንና መዓርጋቱን ሁሉ የፈጸመበትንና ወደላከው ወደ እግዚአብሔር አብ ያረገበትን በአብ ቀኝ የተቀመጠበትን የጌታችንና የመድኃኒታችንን በዓለ ዕርገት አክብሩ” /ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፤ አንቀጽ 19፤ ቁጥር 736 እና 740/፡፡

እንደ ማጠቃለያ

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት “እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡” ብሏል /ዮሐ. ፲፮፡፯/፡፡ እርሱ በአካል ስለሚለያቸው የሐዘን ሰሜት እንዳይሰማቸው የሚያጽናና መንፈስ እንደሚልክላቸው “አብ በስሜ የሚልከው መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል” ብሎ ነግሯቸዋል /ዮሐ. ፲፬፥፮/። ይህንን ተስፋ በማመን ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለዉ ይመለከቱ የነበሩት ደቀ መዛሙርት በሃምሳኛዉ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል። እኛም ዕርገቱን እያሰብን ዓይናችንን ወደ ሰማይ እናነሳለን።
ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ያዘዛቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ በመታመን አደራቸውን እንደተገበሩ ሁሉ በሐዲስ ኪዳን ያለን ምእመናንም ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠብ የሰጠንን የትሕትናን አደራ፤ በመስቀል በመቸንከር ያሳየንን መከራን የመቀበል አደራ፤ በገዛ ሥልጣኑ ከሙታን በመነሣት የነገረንን ትንሣኤ ዘጉባኤን ተስፋ በማድረግ በምክረ ካህን በፈቃደ እግዚአብሔር እየኖርን ክርስቲያናዊ ምግባራትን ከሃይማኖት ጋር አስተባብረን ልንይዝ ይገባል።
በዓለ ዕርገትን ስናከብርም በጸሎት፣ በምስጋናና በቅዳሴ ሊሆን ይገባል፡፡ ዕርገት የድልና የክብር በዓል ነው። በቤተክርስቲያን ተገኝቶ በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ፣ በምስጋና፣ ጸሎትና የቅዱስ ቊርባን በመቀበል ከጌታችን ጋር ያለንን ኅብረት ማጽናት ይገባል። ዘለዓለማዊ ሕይወትን እያሰብን በሃይማኖት ጸንተን፣ ሕጉን ትእዛዙን ጠብቀን እንድንኖር እግዚአብሔር ማስተዋሉንና ጥበቡን ያድለን፡፡ አሜን፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ሃይማኖተ አበው
✍️ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜ
✍️ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ
✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ በዓላት

*
05/19/2026

*

"ፈሪ አትሁኑ! የጠንቋዮችንና የሃሰተኞችን ወሬ አትስሙ። የእግዚአብሔር ስም የጸና ግንብ ነውና በእርሱ ላይ እንታመን።"ዓለም ላይ አለ የተባለ ጀግና ጠንቋይ ይድገምብኝ | እኔ በጌታችን እና ...
05/16/2026

"ፈሪ አትሁኑ! የጠንቋዮችንና የሃሰተኞችን ወሬ አትስሙ። የእግዚአብሔር ስም የጸና ግንብ ነውና በእርሱ ላይ እንታመን።"

ዓለም ላይ አለ የተባለ ጀግና ጠንቋይ ይድገምብኝ | እኔ በጌታችን እና በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናለሁ
በህይወታችን ውስጥ የተለያዩ ፈተናዎች፣ የሰዎች ማስፈራሪያዎች ወይም የክፉ መንፈስ ውጊያዎች ሊገጥሙን ይችላሉ። ነገር ግን እኛ የምንታመነው በሰው ኃይል ወይም በጠንቋዮች ተንኮል ሳይሆን በኃያሉና በድል አድራጊው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው!
"ፈሪ አትሁኑ! የጠንቋዮችንና የሃሰተኞችን ወሬ አትስሙ። የእግዚአብሔር ስም የጸና ግንብ ነውና በእርሱ ላይ እንታመን።"
​ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #እምነት #ክርስቶስ #ድንግልማርያም #መዝሙረዳዊት #የመንፈስጥንካሬ

አንድ መነኩሴ በዝሙት ኃጢአት ተሸንፎ ይወድቃል። ሲወድቅ ወዲያው ተነስቶ በንስሐ ያለቅሳል። ነገር ግን አሁንም ይወድቃል። እንዲህ እያለ ሰባት  ጊዜ ወደቀ! ነገር ግን በወደቀ ቁጥር ወደ ጌታ...
05/15/2026

አንድ መነኩሴ በዝሙት ኃጢአት ተሸንፎ ይወድቃል። ሲወድቅ ወዲያው ተነስቶ በንስሐ ያለቅሳል። ነገር ግን አሁንም ይወድቃል። እንዲህ እያለ ሰባት ጊዜ ወደቀ! ነገር ግን በወደቀ ቁጥር ወደ ጌታ ፊት እየቀረበ "ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!" እያለ ያለቅስ ነበር ንስኃም ይገባ ነበር።

በመጨረሻም ዲያብሎስ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ "ይህ ሰው ርኩስ ሆኖ ሳለ፣ እንዴት ትቀበለዋለህ? አንተ አድልዎ ታደርጋለህ!" እግዚአብሔርም ለዲያብሎስ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ አንተ ክፉ የሆንክ ጠላት፣ እርሱ ወደ ኃጢአት ሲመጣ አንተ ሰባት ጊዜ ከተቀበልከው፤ እኔ መሐሪና ይቅር ባይ የሆንኩ አምላክ፣ ወደ እኔ በንስሐ ሲመጣ እንዴት አልቀበለውም?"

***
ዛሬ አንተ ብትወድቅም፣ ብትረክስም፣ በኃጢአት ብትቆሽሽም... በወደቅህበት አትቅር! ወዲያውኑ ተነሳ። ራስህን ይዘህ ወደ ንስሐ አባትህ ሂድ። "አልችልም" አትበል። መቶ ጊዜ ብትወድቅ፣ መቶ አንድ ጊዜ ተነሳ። እግዚአብሔር አንተን ለማዳን የፈሰሰው ደም፣ ካንተ የኃጢአት ክምር እጅግ ይበልጣልና።
****
ትምህርቶችን በዩቱብ:በቴሌግራም፣በቲክቶክ እንዲሁም በዚህ በfacbook ማግኘት ይችላሉ
****

Follow, share, comment..

ኢየሱስ የተነበበባት ፊደላችን ተወለደች።የትኛውም ከአንደበታችን የሚወጣ ቃል ረቂቅ ነው። አይታይም አይጨበጥም።"ኢየሱስ" ብለን በቃላችን ብቻ ብንናገር ስሙ አይዳሰሰም አይታይም። ይህን ስም ማ...
05/09/2026

ኢየሱስ የተነበበባት ፊደላችን ተወለደች።
የትኛውም ከአንደበታችን የሚወጣ ቃል ረቂቅ ነው። አይታይም አይጨበጥም።
"ኢየሱስ" ብለን በቃላችን ብቻ ብንናገር ስሙ አይዳሰሰም አይታይም። ይህን ስም ማየትና መንካት ከፈለግን የግዱን ኢየሱስ ብለን በፊደል መጻፍ ያስፈልገናል።

በወንጌል
"እግዚአብሔር መንፈስ ነው" ተብሎ ተጽፏል።መንፈስ ማለት ረቂቅ ማለት ነው።
ረቂቁ አምላክ እንዴት ገዘፈ? እንዴት ታየ?
በፊደል ስለተገለጠ ነዋ። ፊደል ያልናት ድንግል ማርያምን ነው። ረቂቁ አምላክ ሰው ስለሆነባት ስለታየባት ቤዛ ሊሆነን ግዙፍ ሥጋን ስለነሳባት።
እሷ ፊደል ከሆነች ልጇ ወንጌል ነው።
ወንጌልን ያለ ፊደል ምን ብለህ ታነበዋለህ? እንዴትስ ታየዋለህ?
ወንጌላችን የሚጻፍባት ፊደል ዛሬ ከሐና ማሕፀን ከኢያቄም አብራክ ተገኘች።
ሰአሊ ለነ ቅደስት!

Share, follow..

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሦስት የእምነት መመሪያዎች አሏት፡፡ እነርሱም፦፩ኛ፡- ዶግማ፪ኛ፡- ቀኖና ፫ኛ፦ትውፊትዶግማ ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም ዕምነት ማለት ነው፡፡ቀኖና፡- ደግሞ ቃ...
05/08/2026

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሦስት የእምነት መመሪያዎች አሏት፡፡ እነርሱም፦

፩ኛ፡- ዶግማ
፪ኛ፡- ቀኖና
፫ኛ፦ትውፊት

ዶግማ ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም ዕምነት ማለት ነው፡፡

ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡

ትውፊት ፦ አወፈየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ውርስ ቅብብል ማለት ነው።

፩. #ዶግማ

ወይም ዕምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል፦
ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡ በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱ አንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡

በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ዶግማ ወይም እምነት ይባላል፡፡

፪. #ቀኖና

ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖት አባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበትና የሚቀነስለት ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል፦
እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴት በሰማንያ ወንድ በአርባ ቀናችን ነው፡፡ የተወለዱ ሕጻናት ሴቷ ሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው ቢታመሙና በሽታው አስጊ ከሆነ በ፲(10)፣ በ፳(20)፣ በ(፴)30…....ቀናቸው መጠመቅ ይችላሉ ቀኖና ነውና፡፡

በቤተ-ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝ ከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ ቀኖና ነውና፡፡

በቤተ-ክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ ነው ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል። ቀኖና ነውና።
ስለቀኖና (ስለ-ሥርዓት) ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።

፩ ‹‹ነገር ግን ሁሉን በአግባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡››
፩ኛ ቆሮ ፲፬፥፵
14፥40!
፪ ‹‹ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው ሥርዐት ሳይሆን
በተንኮል ከሚሄዱት ወንድሞች ሁሉ ትለዩ ዘንድ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን::
እኛን ልትመስሉ እንደሚገባችሁ እኛም በእናንተ
መካከል ያለ ሥራ እንዳልኖርን ራሳችሁ ታውቃላችሁ››
፪ኛ ተሰ ፫፥፮-፯
3፥6-7!

ቀኖና (ሥርዓት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነና ወንጌልን የሚያስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ማስተማርና መሰጠት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡
በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን /የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ ዕለት ዕለትም ቁጥራቸው ይበዛ ነበር፡፡›› ይላል የሐዋ ሥራ ፲፮፥፬-፭(16፥4-5)፡፡ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ደርቤንና ልስጥራን በተባሉ ቦታዎች ለነበሩ ክርስቲያኖች ወንጌልን ከሰበከ በኋላ ሐዋርያት የወሰኑትን ቀኖና (ሥርዓት) እነደሰጣቸው እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ቀኖና ወይም ሥርዓት ቤተ-ክርስቲያንን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡

በመሆኑም ዶግማንና ቀኖናን ወይም ዕምነትንና ሥርዓትን ጎን ለጎን ይዞ መጓዝ ሐዋርያትን መከተል ነው፡፡ እንግዲህ ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያንን የሚቃወሙ ሰዎች ሁሉ፤ የሚቃወሙት በቀኖና (በሥርዓት) የሚመሩትን ክርስቲያኖች ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስን በመሆኑ እንዳይሳሳቱ አደራ እንላለን፡፡

፫. #ትውፊት

ትውፊት ማለት ውርስ፤ ቅብብል ማለት ሲሆን ክርስቲያናዊ ትውፊት አበው ጠብቀው ለእኛ ያቆዩን በቤተ-ክርስቲያን ሕይወት የምናገኘው የክርስቲያኖች ኑሮ፤ ውርስ ትምህርትና ሥርዓት ነው።

አንድን ትውፊት ክርስቲያናዊ ነው ይምንለው፦
፩) ቅዱሳን አበው በኑሮአቸው የገለጡት ማለትም የተናገሩት፤ የሰሩትና ያስተማሩት
፪) በቤተ-ክርስቲያን ተጠብቆ የሚሰራበት፤
፫) እኛን ከቀደሙ አበው ጋር አንድ የሚያደገን፤ አሰረ ፍኖታቸውን እንድንከተል የሚያበቃን ሲሆን ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

ሼር ና ፎሎው አያርጋችሁ 🙏🙏
ከ አንገታም አቦ የተወሰደ

''ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው''📌መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ  | በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን!ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅ...
05/06/2026

''ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው''

📌መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

| በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን!
ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤
ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፤
ብፁዕ ኣቡነ ሕርያቆስ
የኣዲስ ኣበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣
በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)።
የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤
ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎኣል፤
ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሓፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!

ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው፤
ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ ኣከናውኖታል፤
በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ኣስታረቀ፤
ለዚህም ነው ተበዳይ እሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እሱ፣ ኣስታራቂ እሱ፣ ታራቂ እሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለኛ ግር የሚል ቢመስልም ለሱ ቀላል ነበረ።
በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በኣንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ሽፍታ “ዛሬውኑ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “ኣባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ ኣደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ ኣማሕፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው።

ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው፤
እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ ኣድኖናል” ብለን በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፣ እሱም “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” ብሎ የሚያረጋጋን በመሰቀሉ ይህንን ውጤት ስላስገኘልን ነው።

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረ ሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር ኣንድ ተልእኮ ነው፤
ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በኣስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የኣንድነት ምስጢር ነው፤
እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ ኣሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት ኣይኖርም ነበር፤
ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮኣችንን በኣግባቡ ኣለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሳሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል።

ይሁንና ኣሁንም ሕዝቡን ወደ ኣንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤
ሃገርን በኃላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም ኣማራጭ ሓሳብ ኣለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልኂቃነ ሃገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም ኣትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ ኣይደለምና፣
የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ ኣዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በኣንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሃብትን ማግኘት፣ የእምነት ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው።

ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም፤
ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው ኣማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን ኣይበጅም እንላለን።

በመጨረሻም፦
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ ኣምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን!!!
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሓት ለእግዚአብሔር፤
አሜን!!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤
ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
ኣዲስ ኣበባ - ኢትዮጵያ

EOTC TV

ቸሩ መድኃኒዓለም ለንስሃና ቅዱስ ቁርባን ያብቃን🙏⓶⓻🙏በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች ዝርዝር ትርጉም ከነማስረጃው እንደሚከተለው ቀ...
05/05/2026

ቸሩ መድኃኒዓለም ለንስሃና ቅዱስ ቁርባን ያብቃን🙏⓶⓻🙏
በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች ዝርዝር ትርጉም ከነማስረጃው እንደሚከተለው ቀርቧል፦
🌿፩. ኢየሱስ (ኢያሱ/Yeshua)

* ትርጉሙ፦ "እግዚአብሔር ያድናል" ወይም "መድኃኒት" ማለት ነው። ይህ ስም ለክርስቶስ በሰውነቱ የተሰጠው የግል ስሙ ነው።
* ማስረጃ፦ "ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።" (ማቴዎስ ፩፡፳፩)

🌿 ፪. ክርስቶስ (Christos)

* ትርጉሙ፦ "የተቀባ" ማለት ነው። በጥንት ዘመን ነገሥታት፣ ካህናትና ነቢያት ለሥራ ሲመረጡ በቅዱስ ዘይት ይቀቡ ነበር። ኢየሱስ ደግሞ የባሕርይ ንጉሥ፣ የባሕርይ ካህንና ነቢይ ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ መሆኑን ያሳያል።
* ማስረጃ፦ "እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ... ዞረ።" (የሐዋርያት ሥራ ፲፡፴፰)

🌿 ፫. መድኃኒዓለም (Medhanealem)

* ትርጉሙ፦ "የዓለም መድኃኒት" ማለት ነው። "መድኃኒት" እና "ዓለም" ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ሲሆን፣ ክርስቶስ ለአንድ ወገን ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ መሆኑን ያመለክታል።
* ማስረጃ፦ "እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።" (፩ኛ ዮሐንስ ፬፡፲፬)

🌿፬. አማኑኤል (Emmanuel)

* ትርጉሙ፦ "እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ" ማለት ነው። ይህ ስም አምላክ ሰው ሆኖ ከሰዎች ጋር መኖሩን የሚገልጽ የምሥጢረ ሥጋዌ ስም ነው።
* ማስረጃ፦ "እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" (ማቴዎስ ፩፡፳፫)

🌿 ፭. ወልደ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ልጅ)

* ትርጉሙ፦ ክርስቶስ ከአብ ጋር ያለው የባሕርይ አንድነት የሚገልጽ ነው። "ልጅ" ሲባል እንደ ሰው ልጅ በዘር የሚገኝ ሳይሆን፣ ከአብ ጋር በህልውና (በመገኘት) አንድ መሆኑን ያሳያል።
* ማስረጃ፦ "ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የኃይል ቀኝ ተቀምጦ የሰማይንም ደመና ሲመጣ ታዩታለህ አለው። ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና... የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አለው።" (ማርቆስ ፲፬፡፷፩-፷፪)

🌿 ፮. ቃል (Logos)

* ትርጉሙ፦ ክርስቶስ የአብ "ጥበብና ቃል" መሆኑን ይገልጻል። ቃል ከአእምሮ እንደሚወጣ፣ ወልድም ከአብ ያለ መለየት መገኘቱን ያሳያል።
* ማስረጃ፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።" (ዮሐንስ ፩፡፩)

🌿ስለ መድኃኒዓለም (ኢየሱስ ክርስቶስ) ማንነትና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታጀበ ዝርዝር ማብራሪያ፦
◈ መለኮታዊ ማንነቱ (ፍጹም አምላክነቱ)
ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል።

ጥቅስ፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።" (ዮሐንስ 1:1)

ትርጉም፦ እርሱ ዓለም ሳይፈጠር የነበረና ራሱም አምላክ እንደሆነ ይገልጻል።

◈ ሰብአዊ ማንነቱ (ሰው መሆኑ)
አምላክነቱን ሳይተው፣ እኛን ለማዳን ሲል የእኛን ሥጋ ለበሰ።

ጥቅስ፦ "ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ..." (ዮሐንስ 1:14)

ትርጉም፦ የማይታየው አምላክ በድንግል ማርያም በኩል ተወልዶ በምድር ላይ ሰው ሆኖ ተገልጧል።

◈ የመምጣቱ ዋና ዓላማ (ቤዛነት)
"መድኃኒዓለም" የሚለው ስያሜ የሥራው ውጤት ነው።

ጥቅስ፦ "የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና።" (ሉቃስ 19:10)

ትርጉም፦ የመጣው በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር የተለየውን የሰውን ልጅ ፍለጋና ወደ ቀድሞ ክብሩ ለመመለስ ነው።

◈ አንድያ መንገድና መካከለኛነቱ
ወደ ዘላለም ሕይወት ለመድረስ ብቸኛው በር እርሱ እንደሆነ አስተምሯል።

ጥቅስ፦ "ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" (ዮሐንስ 14:6)

ትርጉም፦ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ በመስቀሉ ሞት አፍርሶ እርቅን ፈጥሯል።

◈ ሞቱና ትንሣኤው
የክርስትና እምነት ማዕከል ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱ ነው።

ጥቅስ፦ "ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል።" (ዮሐንስ 11:25)

ትርጉም፦ ሞቱ ለእኛ ቤዛ ሊሆን ሲሆን፣ ትንሣኤው ደግሞ ለእኛ የዘላለም ሕይወት ዋስትና ነው።

◈ ዳግም ምጽአቱና ንግሥናው
በመጨረሻው ዘመን ዓለምን ለመፍረድ በክብር ይመጣል።

ጥቅስ፦ "እነሆ፥ በደመና ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ... ያዩታል።" (ራእይ 1:7)

ትርጉም፦ እርሱ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ሆኖ ለዘላለም ይነግሣል።

Orthodoxawian follow ብቻ አድርጉ...
05/03/2026

Orthodoxawian follow ብቻ አድርጉ...

Address

Chicago, IL

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Orthodox church. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopia Orthodox church.:

Share