Debre Selam Kidus Mikael EOTC, Indianapolis

Debre Selam Kidus Mikael EOTC, Indianapolis Ethiopian Orthodox Tewahido Church

01/21/2026
የደመራ በዓልን ኑ በእለቱ እናክብር!“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው” 1ኛ ቆሮንቶስ 1:18
09/24/2024

የደመራ በዓልን ኑ በእለቱ እናክብር!

“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው”
1ኛ ቆሮንቶስ 1:18

1 ቆሮንቶስ 1:18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤
09/23/2024

1 ቆሮንቶስ 1:18
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤

የመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም ገ/ሚካኤልአጭር የሕይወት ታሪክ ክቡር አባታችን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም  በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሙ እቲሳ በሚባል ስ...
08/09/2024

የመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም ገ/ሚካኤል
አጭር የሕይወት ታሪክ

ክቡር አባታችን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም በሸዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሙ እቲሳ በሚባል ስፍራ እ. ኢ. አ. በመስከረም 29 ቀን 1934 ዓ.ም ተወለዱ። እድሚያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከትውልድ ስፍራቸው ከሚገኘው እቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም ከተለያዩ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በዲቁና ማዕረግ ተሹመው በዚያው ገዳም አገልግለዋል። ወደ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም በመሄድ በግንቦት 12 ቀን 1956 ዓ.ም አስኬማ መላእክት የሆነውን ምንኩስናን ፈጽመዋል። በተመሳሳይ ዓመት ማዕረገ ቅስናን በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል። በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ በመዝለቅ በመካዬኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ለረጅም ጊዜ በመደበኛ ቀዳሽነት አገልግለዋል።
በ1964 ዓ.ም በአገልግሎት ትጋታቸውንና መንፈሳዊነታቸው ተመርጠው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት እንዲያገለግሉ ተልከዋል። በገዳሙም በትህትና ፣ በቅንነትና በትጋት ይሰጡት የነበረውን አገልግሎት በመቀጠላቸው በ1968 ዓ.ም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የቁምስና ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ባጠቃላይ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ለ26 ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥተው በኮሎምበስ ኦሃዮ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ዓመታት አገልግሎት ሰጥተዋል።
ክቡር አባታችን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም በጥር 13 ቀን 1992 ዓ.ም በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ (የአሁኑ ፓትርያርክ) ፈቃድ የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት ይዘው ወደ ኢንዲያናፖሊስ በመምጣት የደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን አቋቁመው ለ17 ዓመታት በደብር አስተዳዳሪነት በልዩ ትጋትና በትህትና የኢንዲያና እና አካባቢውን ምዕመናን አገልግለዋል።
በእሳቸው ብርታትና በምዕመናኑ ድጋፍ የኢንዲያናፖሊስ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከኪራይ ቤት ወጥቶ የራሱ አነስተኛ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው በኋላም አሁን የምንጠቀምበትን የዚህ ግዙፍ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት እንዲሆን አድርገዋል።
ክቡር አባታችን ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም ቤተ ክርስቲያን የውጭና የውስጥ ሲኖዶስ እንዲሁም ገለልተኛ በሚል በምትታመስበት ወቅት ደብሩ በየዘመኑ ከተሾሙት የሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያለው ግንኙነት ሳይቋረጥ ጸንቶ እንዲቀጥል በማድረግ እንዲሁም በነበረው ፈተና የተነሳ አንድ ካህን በአንድ ደብር ብዙ በማይቆይበት በዚያ ዘመን የኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ17 ዓመታት አለቃው አንድ ደብሩም አንድ ሆኖ ለብዙ አድባራት ምሳሌ እንዲሆን ከፍተኛ ገድል ፈጽመዋል።
አርምሞ ፣ ትጋት ፣ ትህትና እንዲሁም አብርሃማዊ እንግዳ ተቀባይነት መታወቂያቸው የነበረው አባታችን በሚድ ዌስትና አካባቢው አድባራት በሚያገለግሉ አባቶች ካህናትና ምዕመናን ዘንድ እጅግ የሚወደዱና የሚከበሩ ፣ ልዩ ግርማ ሞገስ የተሰጣቸው ፣ ሳይናገሩ የሚያስተምሩ ፣ ቃል ሳያወጡ የሚመሩ አባት ነበሩ።
በ2009 ዓ.ም (2017) እድሚያቸው እየገፋ አቅም እያነሳቸው መሆኑን በመጥቀስ ለ26 ዓመታት ወዳገለገሉበት ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት በመሄድ ቀሪ ሕይወታቸውን በጸሎት ተወስነው ለማሳለፍ በወቅቱ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን ብፁዕ አቡነ ዘካርያስን በማስፈቀድ እንዲሁም የደብሩን ካህናትና ምዕመናን በማሳመን ብፁዕነታቸው በተገኙበት በልዩ ሥነ ሥርዐት በእንባና በለቅሶ ተሸኝተዋል።
በመጨረሻም ያለፉትን 3 ዓመታት በኢየሩሳሌም ገዳም በተመደቡበት ኃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተው በተወለዱ በ78 ዓመታቸው ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። በገዳሙ ሥርዐት መሠረት ነሐሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም የአምስቱም ገዳማት ካህናትና መነኮሳት በተገኙበት የጸሎተ ፍትሃት ከተደረገላቸው በኋላ ሥርዓተ ቀብራቸው በዚያው ገዳም በክብር ተፈጽሟል።
በሃይማኖት በሥነምግባር እንድንጸና በኑሮና በሕይወት በቃልም ያስተማሩንና አብነት የሆኑን ክቡር አባታችን መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም ዛሬ በሥጋ በመለየታቸው ብናዝንም በመንፈስ ግን እንደማይለዩን እናምናለን።
እግዚአብሔር አምላክ የአባታችን ነፍስ ከቅዱሳን ማኅበር ይደምርልን ለእኛም መጽናናቱን ያድለን! አሜን

06/21/2024

Address

1242 W. Ray Street
Indianapolis, IN
46221

Opening Hours

Saturday 2pm - 4pm
Sunday 5am - 12pm

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Selam Kidus Mikael EOTC, Indianapolis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Debre Selam Kidus Mikael EOTC, Indianapolis:

Share