EOTC Maryland Diocese

EOTC Maryland Diocese በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት የሜሪላንድ ግዛት ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት

"በጎነትን መመስከርና ለጽድቅ መቆም የሕሊና ግዴታ ብቻ ሳይሆን፣ የነፍስ ጥሪም ነው!"
05/14/2026

"በጎነትን መመስከርና ለጽድቅ መቆም የሕሊና ግዴታ ብቻ ሳይሆን፣ የነፍስ ጥሪም ነው!"

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ G+2 ሕንጻ  መኖሪያ ቤት  ለመቄዶንያ በስጦታ አበረከቱ።ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ሚያዚያ ፳፫/፳፻፲፰ ዓ/ም ብፁዕ አ...
05/02/2026

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ G+2 ሕንጻ መኖሪያ ቤት ለመቄዶንያ በስጦታ አበረከቱ።

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ሚያዚያ ፳፫/፳፻፲፰ ዓ/ም

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ G+2 ሕንጻ መኖሪያ ቤት ለመቄዶንያ በስጦታ አበረከቱ።

በአሁኑ ሰዓት ብፁዕነታቸው መቄዶንያ ባዘጋጀው የቀጥታ ሥርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተዋል።

ብፁዕነታቸው ቤቱ ከ23 ዓመታት በፊት ለገዳማትና ለወላጆቻቸውን በተለያያዩ ምክንያቶች ላጡ ወገኖች ዕርዳት እንዲሆን በማቀድ የተሠራ መሆኑ ገልጸዋል።

በዚህ ላለፉት በርከታ አመታት በተከራይቶ ከሚገኘው ገንዘብ ለተለያዩ በጎ ዓላማ ሲውል መቆየቱን አስተውሰው በአሁኑ ሰዓት ቀደም ብየ ያሰብኩትንና በውስጥም ስሠራበት የነበረውን በጎ ሥራ በዘለቄታዊነት ሊያስቀጥል የሚችል በጎ አድራጎት ድርጅት ሳስብ የመጣለኝ መቄዶንያ በመሆኑ ለዚሁ እንዲሰጥ ወሰንኩኝ ብለዋል።

ቤቱን የሰጡት የካቲት 1/2018 ዓ/ም ቢሆንም በመቄዶንያ ሥራ አስኪያጅ ክቡር አቶ ቢንያም አማካኝነት ብፁዕነታቸው በሚዲያ ቀርበው እንዲሰጡና ርክክቡም በአካል በቤቱ በመገኘት እንዲሆን እንዲሁም ይህን አርአያነት ያለውን መልካም ሥራ ለሌሎችን ትምህርት እንዲሆን በማሰብ የግድ ወደ ሚዲያ እንደመጡም ተገልጿል።

የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መረጃ ማዕከል በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚረዱበትና በሀገረ ደረጃም በበረካታ ቦታዎች ቅርጫፎችን የከፈተ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው

“ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤”ሐዋ 4:13መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱ የሰው ልጆች የነጻነት አዋጅ እና የ...
04/17/2026

“ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤”ሐዋ 4:13

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱ የሰው ልጆች የነጻነት አዋጅ እና የደስታችን ምንጭ መሆኑን በማስብ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ሊቃነ መናብርት በጋራ በመሆን ለሃገረ ስብከቱ ሊቀ ዻዻስ ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የእንኳን አደረስዎ መርሀግብር ዛሬ በአዳም ሐሙስ በዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በደመቀ ሁኔታ አክብረው ውለዋል።

ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መሪነት በጸሎት የተከፈተ ሲሆን፤ በመቀጠልም የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ አርያም መምህር ብርሀኑ ጎበና የመግቢያ መልዕክት ያስተላለፋ አስተላልፈዋል፤ በመልዕክታቸውም አያይዘው ይህ መሰባሰብ እና አንድነት የብፁዕ አባታችን የትጋት እና የጸሎት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ በውጭ ያለችዋ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ተከፍላ በእንግልት የቆየች በመሆኗ በዚህ ደረጃ አንድነት ተፈጥሮ መታየቱ የእግዚአብሔር ቸርነት እና ረድኤት ከቤተ ክርስቲያን እንዳልተለየ ያሳያል ብለዋል።

በጉባኤው ላይም ሊቀ ጠበብት ጥበብ ይኄይስ ዕለቱን የተመለከተ ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን፤ በመልአከ ሰላም ጥዑመ ልሳን ለብጹነታቸው ቅኔ ቀርቧል። እንዲሁም መርሀግብሩን በማኅበራዊ ሚዲያ በቀጥታ ሲከታተሉ የነበሩ መጋቤ ምስጢር ሰሎሞን ተስፋዬ ከኦስተን ቴክሳስ (Austin,TX) ተጨማሪ ዘአምላክየ እና ጉባኤ ቃና ቅኔ በጽሑፍ ልከው በመጋቤ ወንጌል መምህር ኤልያስ ቀርቧል።

በጉባኤው የፍቅር ማዕድ የተደረገ ሲሆን፤በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀገረ ስብከቱ ያሉ ሁሉንም አድባራትና ገዳማትን አመስግነው፤ ይህንን መርሀግብር በማስተባበር በትጋት የሰሩትን የሦስቱም ስቴት ሊቃነ ካህነትንና ኮሚቴውን አመስግነው፤ ይህ የሚደረገው መርሃግብር የቤተ ክርስቲያን ትውፊትን መሠረታ ያደረገ ሲሆን ይህንኑ ሳይለቅ በባዕድ ምድር መደረጉ የቤተ ክርሰቲያን ክብር ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ብሎም ተተኪው ትውልድ ይህንኑ የአባቶችን ሃይማኖት፤ ሥርዓት እና ትውፊትን ይዞ ለመሄድ ፈርቀዳጅ ዝግጅት መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህ የአብያተ ክርሰቲያናቱ ህብረት እና ፍቅር እንዲቀጥል ሁላችንም አብረን ከሀገረ ስብከቱ ጋር ልንሰራና የቤተ ክርሰቲያናችንንም አገልግሎት ለሁሉ እንዲዳረስ የበኩላችንን መንፈሳዊ ግዴታን እንድንወጣ አባታዊ ምክር እና ቡራኬ ሰጥተው ጉባኤው በጸሎት ተጠናቋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

Address

6509 Riggs Rd
Hyattsville, MD
20782

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EOTC Maryland Diocese posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to EOTC Maryland Diocese:

Shortcuts

Share