Debre Kerbe Kidist Mariam WeAbune Habtemariam Church pages

Debre Kerbe Kidist Mariam WeAbune Habtemariam Church pages Debre Kerbe Kidist Mariam WeAbune Habtemariam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.
13505 Dulles Technology Dr, Herndon VA 20171

በደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል አቡነ ሃብተማርያም ቤተክርስቲያን የዳግም ትንሳኤ አገልግሎት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተገኙበት
04/19/2026

በደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል አቡነ ሃብተማርያም ቤተክርስቲያን የዳግም ትንሳኤ አገልግሎት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተገኙበት

04/17/2026
04/12/2026

“አሁን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኲር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል ሞት በሰው በኩል ስለመጣ ትንሣኤ ሙታን በክርስቶስ ሆነ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ ሁሉ ደግሞ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ" (፩ቆሮ.፲፭÷፳)

የትንሣኤ በዓል ከዘመነ ሐዋርያት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይከበር ነበር። በኢየሩሳሌም የበዓሉንም አከባበር ልዩና አስደሳች የሚያደርገው ጌታ በብርሃን ተገልጾ በተአምራዊ ክስተት መነሣቱን ለተሰበሰበው ሕዝብ ሲያረጋግጥና እግዚአብሔርንቱን ሲገልጽና በተአምራዊ ክስተት ሲታጀበ መሆኑ ነበር።

የበዓሉ ታሪካዊና ተአምራዊ መነሻውም ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ መቃብር በሄደ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ለወዳጆቹ ትንሣኤውን አረጋግጧል። ክርስቲያኖችም ይህንን ታሪክ መሠረት አድርገው ጧፍ በመስቀልኛ ገምደው በጎልጎታ ከክርስቶስ መቃብር ላይ ተሰብስበው "ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ፣ ትንሣኤህን ለምናምን ብርሃንህን ላክልን" እያሉ ለትንሣኤው ምልክትነት ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን እንዲልክላቸውና በቅዱስ ጴጥሮስ አንጻር ትንሣኤው በተአምራዊ ብርሃን መገለጥ እንዲረጋገጥላቸው ይማጸኑ ነበር። እውነትም ብርሃን ከሰማይ ወርዶ በምእመናን ላይ ሲረብ የትንሣኤው ክብረ በዓል ይጠናቀቅ ነበር።

በዚህ መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን "ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ፣ ትንሣኤህን ለምናምን ብርሃንህን ላክልን" እያለች ዕለቱንም ብርሃን የሚል ተጨማሪ ስያሜ ሰጥታ ከዐርብ ማታ ጀምራ እሑድ ሌሊት ትንሣኤውን በተማኅጽኖ ዝማሬ "አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ገባሬ ሕይወት ክርስቶስ፣ ሕይወትን የሠራ ክርስቶስ ሥልጣኑን በሞት ላይ ገለጠ" በማለት ታከብራለች።

እኛም ትንሣኤንውን የምናከብረው ከዓርብ ምሽት ጀምሮ እስከ እሑድ ሌሊት ድረስ ከቤተክርስቲያን ገብቶ ሳይወጡ ቀዳሚትን ሳይቀር በመጾም ነው። በዚህ ታሪካዊና ተአምራዊ መነሻነት ቤተክርስቲያናችንና ሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናትም ቀዳሚት ስዑር በሌላም ስያሜዋ የትንሣኤ ዋዜማ ወይም ርደተ ብርሃንም ተብላ መጠራቷ ምክንያቱ ይህ ነው።

ከዓርብ ምሽት ጀምሮ እስከ እሑድ ሌሊት እነዚህን ፫ ቀናት በዚሁ ዓይነት አቆጣጠር ስናከብርም ክርሰቶስ በምድር ልብ በመቃብር ከተቀበረበት ዓርብ የቀዳሚት ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ በእሑድ ሌሊት ከሙታን መካከል ተለይቶ እስከ ተነሣበት ሰዓት ድረስ ፫ መዓልትና ፫ ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ በሥጋው ማረፉን ወይም መቆየቱንና በነፍሱ ደግሞ ሲዖልን መመዝበሩን ለማስተማር "ንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተንሥአ እሙታን፣ እኛ ግን የተሰቀለውን ከሙታንም ተለይቶ የተንሣውን ክርስቶስን እንሰብካለን" (፩ቆሮ.፩÷፳፫) ነው።

"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አግአዞ ለአዳም አሰሮ ለሰይጣን ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የእኛም የኀጢአት ውሃ ይወገድ"

የትንሣኤ በዓል መለያየትንና ጥላቻን ያስወገደ በሞቱ ሞታችን የተደመሰሰበት ፣ ትንሣኤያችን የታወጀበት፣ በተከፈለልን ዋጋ ለሰው ልጆች ሁሉ አዲስ የድኅነት ምዕራፍን የከፈተ ታላቅ በዐል ነው።

በድጋሜ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ። በዓሉ የፍቅርና የበረከት የሰላምና የአንድነት ያድርግልን።
በትንሣኤው ሰላም ለናፈቃት ዓለምና ለሕዝቧቿ የትንሣኤውን ብርሐን ያብራላት። የልዑል እግዚአብሔር ሰላም ምድራችንን ይግዛ። ለሕዝባችን አንድነትን፣ ለመሪዎች ጥበብንና የሀገር ፍቅርን ለትውልድ ራዕይን ያድልልን።

የትንሣኤውን በዓል በፍቅርና በደስታ እንዲያሳልፉ ከልቤ ምኞቴን እገልጻለሁ። መልካም በዓል።

መ/ር ዮሐንስ ለማ (ቀሲስ)
እሁድ ሚያዝያ ፬ቀን ፳፻፲፰ (2026) ዓ.ም

የ ጌታችን የመደሃኒታች የ ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ  በዓል  በደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ሀብተማርያም።
04/12/2026

የ ጌታችን የመደሃኒታች የ ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ሀብተማርያም።

04/11/2026

Address

2472 Centerville Road
Herndon, VA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Kerbe Kidist Mariam WeAbune Habtemariam Church pages posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share