Debre Berhan Holy Trinity EOTC

Debre Berhan Holy Trinity EOTC Debre Berhan Holy Trinity is an Ethiopian Orthodox Tewahedo Church that Serves Orthodox Christians.

10/29/2024
09/11/2024

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ::

በኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

ዘመን መለወጫ
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ እንዲል፡፡
በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 7፥1/ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡

ዕንቁጣጣሽ
ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም ወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ
ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡

በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ክፍል።

05/05/2024

“ወኀቤየ ሀሎ መራኁተ ሞት ወሲኦል - የሞትና የሲዖል መክፈቻ አለኝ” ራዕ 1፥18
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ከ መጋቤ ሐዲስ ምስጢረሥላሴ ማናዬ

ቅዱስ ያሬድ

ውድ ኦርቶዶክሳውያን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በቅድሚያ ለ2016 ዓ.ም. ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ !!

ጌታች አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን ተወልዶ ሠላሣ ሦስት ዓመት ኖሮ ሰውን በደሙ ሊቀድሰው በምድር መካከል በቀራንዮ ተሰቀለ ለሰው ነፍሱን ሰጠ። እስከሞት እስከ መቃብር ደረሰ።ሰውን ለማዳን በመቃብር ሦስት ቀንና ሌሊት አድሮ ተነሣ ።
እሱ እራሱ እንደተናገረ
“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።”
ማቴ 12፥40
ውድ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች !
ትንሣኤ ከጌታችን በዓላት እጅግ ትልቁ በዓል ነው። ሞት ድል የተነሣበት በሞት ጥላ ስር የነበረ የሰው ልጅ ከሞት ተገዥነት የተገላገለበት በዓል ነው። ትንሣኤ ማለት መነሣት ማለት ነው አምላካችን ክርስቶስ ከተቀበረበት ሲነሣ የእኛም ሕይወት ከውድቀት ተነስቷል። ትንሣኤ በዓልነቱ የክርስቶስ ብቻ አይደለም። የሰው ልጆች ሁሉ ነው። ሞት የሰው ሁሉ እንደነበረ ትንሣኤም የሰው ሁሉ ነው። በተለይ ትንሣኤ ልቡና፣ ክርስትና ላለን ደግሞ ልዩ ነው። ትንሣኤ የተስፋ ፍጻሜ ነው። ሰው መኖር ይፈልጋል ግን የመኖር ፍላጎቱ በሞት ይገታል። ሕያው ሆኖ የመኖር ፍላጎታችን ያለ ምንም ገደብ የምንናገኘው በትንሣኤ ነው።
ሰው ሦስት ጊዜ ይወለዳል
1 ሥጋዊ ልደት ከእናትና ከአባት
2 መንፈሳዊ ልደት በጥምቀት ከክርስቶስ
3 በትንሣኤ ከመቃብር እንወለዳለን
የመጀመሪያው ልደት ከሥጋና ከደም ያገኘነው በመሆኑ ሞትን ያስከትላል። ይህን ሞት ማሸነፍ የምንችልበት መንፈሳዊ ልደት በጥምቀት በጥልቅ ምስጢር በማይመረመር ግብር እናገኛለን።ጥምቀት ሦስተኛውን ልደት ትንሣኤ ሙታን ይጠቁመናል። ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብለን ስንጠመቅ አምላካችን ሦስት መዓልትና ሌሊት በከርሠ መቃብር ማደሩን እና ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን እየመሰከርን ነው ። የምንጠመቅበት መጠመቂያ የመቃብር ምሳሌ ነው ገዳው ላይ ጠልቀን አንቀርም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብለን እንወጣለን እንዲሁም በሞት አመካኝነት ወደመቃብር ብንወርድም መቃብር ይዞ ሊያስቀረን አይችልም።የሞትና የሲዖል መክፈቻ አለኝ ያለን አባታች አምላካችን ክርስቶስ የትንሣኤያችን በኩር ነውና። ሞታችንን ድል ነስቶ መቃብራችንን ከፍቶ ያስነሣናል። ይህ ሦስተኛ ልደታች ትንሣኤ የአዳም እናት ከሆነችው ከመሬት የምንወለድበት ነው።ለዚህ ልደት በኩራችን ክርስቶስ ነው።
“እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።”
ቆላ 1፥18
በሥጋ አዳምን መስለን እንወለዳለን በጥምቀት ክርስቶስን እንመስላለን።በትንሣኤ ክርስቶስን መምሰላችን ይረጋገጣል።አዳምን በመምሰላችን ሞትን ማሸነፍ አንችልም ክርስቶስን በመምሰላችን ግን ሞትንም መቃብርንም እናሸንፋለን።በዚህ ከሞት በኋላ ሞት የለሌበት ሕይወት በትንሣኤ ይቀጥላል።ዘለዓለማዊ የመኖር ሕልማችን እውን ይሆናል።
ይህ ትንሣኤ ባይኖር ሁሉም ነገር ከንቱ ነበር ማመናችን መጠመቃችን ስብከታችን ሁሉ ነገራችን ከንቱ ይሆን ነበር ሁሉ ነገር ማሰሪያ ትንሣኤ ነው።
ይህን የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ከልብ ስሙት

1ኛ ቆሮ 15፥12-22
የክርስቶስ ትንሣኤ ከልደቱ የበለጠ አምላክነቱን ያረጋገጠ የአይሁድን ገድለነው እንገላገል የሚል ከንቱ ተስፋ እንደ ሰም ያቀለጠ ነው ። የሞት እና የሲዖል መክፈቻ አለኝ ያለው አምላካችን።ሲዖል ከተሰኘ መቃብር መቃብር ክፍቱ መግነዝ ፍቱ ደንጋይ አንሱ አፍር ቀንሱ ሳይል አጋዥ ሳይፈልግ ከሞት ተነስቷል ሞት ይዞ መግነዝ ገንዞ ሊያስቀረው አልቻለም። መጽሐፍ እንዲህ ብሎ እንደመሰከረ
>
ሐዋር 2፥23
በዚህ መልኩ ሞት ተሸነፈ ሕይወት ተሰጠ የሞት መሸነፍ መኖርን ተስፋ ለሚያደርግ የሰው ልጅ ትልቅ የምሥራች ነው። ያሸነፈው የገዛው ጠላቱ ሞት ሲሸነፍ ከመስማት በላይ ለሰው ምንደስታ ሊኖረው ይችላል ?

የሰሙነ ሕማማት እና ትንሣኤ መርሐ ግብር (የተስተካከለ)
04/29/2024

የሰሙነ ሕማማት እና ትንሣኤ መርሐ ግብር (የተስተካከለ)

የፊታች ዓርብ እና ቅዳሜ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ጋርላንድ፡ ቴክሳስ እንገናኝ።
04/18/2024

የፊታች ዓርብ እና ቅዳሜ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ጋርላንድ፡ ቴክሳስ እንገናኝ።

Address

4406 Broadway Boulevard
Garland, TX
75043

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Berhan Holy Trinity EOTC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share