Zemzem - Ethiopian Muslims Islamic Knowledge Center in Diaspora

Zemzem - Ethiopian Muslims Islamic Knowledge Center in Diaspora This page is for islamic knowledge teaching and knowledge sharing

ታላቁ ዓሊምና ሙሐዲስ የ  #ኢማም አንነወዊ'ይ ሸይኽ   ስለ ሰይዳችን ﷺ ሙዕጂዛዎች ሲናገሩ እንዲህ ይሉናል : «ﻓﺈﻧﻬﺎ ﻟﻴﺴﺖ ﻣﺤﺼﻮﺭﺓ ﻋﻠﻰ ﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﻣﻨﻬﺎ ﻓﻲ ﻋﺼﺮﻩ ﺻﻠﻰ اﻟ...
02/03/2023

ታላቁ ዓሊምና ሙሐዲስ የ #ኢማም አንነወዊ'ይ ሸይኽ ስለ ሰይዳችን ﷺ ሙዕጂዛዎች ሲናገሩ እንዲህ ይሉናል :

«ﻓﺈﻧﻬﺎ ﻟﻴﺴﺖ ﻣﺤﺼﻮﺭﺓ ﻋﻠﻰ ﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﻣﻨﻬﺎ ﻓﻲ ﻋﺼﺮﻩ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ، ﺑﻞ ﻟﻢ ﺗﺰﻝ ﺗﺘﺠﺪﺩ ﺑﻌﺪﻩ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋﻠﻰ ﺗﻌﺎﻗﺐ اﻟﻌﺼﻮﺭ، ﻭﺫﻟﻚ ﺃﻥ ﻛﺮاﻣﺎﺕ اﻷﻭﻟﻴﺎء ﻣﻦ ﺃﻣﺘﻪ ﻭﺇﺟﺎﺑﺎﺕ اﻟﻤﺘﻮﺳﻠﻴﻦ ﺑﻪ ﻓﻲ ﺣﻮاﺋﺠﻬﻢ ﻭﻣﻐﻮﺛﺎﺗﻬﻢ ﻋﻘﻴﺐ ﺗﻮﺳﻠﻬﻢ ﺑﻪ ﻓﻲ ﺷﺪاﺋﺪﻫﻢ ﺑﺮاﻫﻴﻦ ﻟﻪ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﻮاﻃﻊ، ﻭﻣﻌﺠﺰاﺕ ﻟﻪ ﺳﻮاﻃﻊ، ﻭﻻ ﻳﻌﺪﻫﺎ ﻋﺪ ﻭﻻ ﻳﺤﺼﺮﻫﺎ ﺣﺪ، ﺃﻋﺎﺫﻧﺎ اﻟﻠﻪ ﻣﻦ اﻟﺰﻳﻎ ﻋﻦ ﻣﻠﺘﻪ ﻭﺟﻌﻠﻨﺎ ﻣﻦ اﻟﻤﻬﺘﺪﻳﻦ اﻟﻬﺎﺩﻳﻦ ﺑﻬﺪﻳﻪ ﻭﺳﻨﺘﻪ..»

«.. የሰይዳችን ﷺ ሙዕጂዛ (ተአምራት) በእሳቸው ዘመን በተገኘ ነገር ብቻ የተገደበ አይደለም.. ነገር ግን ከሳቸውም ﷺ በኋላ በየዘመናቱ ሁልግዜም እየታደሰ ይኖራል ። ምክንያቱም ኡመታቸው ውስጥ ያሉት የአላህ ወዳጆች ከራማና በችግራቸው ግዜ በእሳቸው ﷺ ተመጅነው ፍላጎታቸውን እና እፎይታን የሚሹ ሰዎች ያገኙት የዱዐቸው ተቀባይነት ለእሳቸው ﷺ ትክክለኛ ማረጋገጫዎችና ከሳቸው ተአምራት ውስጥ ስለሚቆጠሩ ተአምራታቸውን ቆጥሮና ገድቦ የሚጨርሰው የለም ። አላህ ከዲኑ ከማፈንገጥ ይጠብቀን በሱናቸውና በመመሪያቸው ከተመሩት ያድርገን..»

📗 ፈታዋ ኢብኑ ሶላሕ : (1/210)
https://t.me/mededulhabib

ጁምዐቱን ሙባረካ'ህ
በሰይዳችን ﷺ ይሁንበት የዱንያም የአኼራችንንም እጣ ፈንታ ሰዓዳ አላህ ያድርግልን

You can view and join right away.

09/20/2022

የፍትሀዊው መሪ የዑመር ቢን ዐብዱል ዐዚዝ ልጆችን አደብ አስተማሪ ነበሩ ። ትልቅ ዓሊምና ሊቅ ።
ሴት ልጃቸውን ለትዳር ፈልጎ አንድ ወጣት ወደሳቸው መጣና ጠየቃቸው ።
እሳቸውም : ልጄ ለአንተ አትሆንህም .. ልብስ ትውዳለች አሉት ( ታስቸግርሀለች ማለታቸው ነው )
እሱም : የምትፈልገው ነገር በደንብ አለኝ አላቸው
እሳቸውም : አሁን.. አንተ ለሷ አትሆናትም አሉት
መጀመርያ ልጃቸው ዱንያን ስለምትወድ እንዳታስቸግረው ብለው ነበር ።
ከዛ ግን እሱም ዱንያን እንደሚወድ ሲያውቁ በዱንያ እንዳይፈተኑና ልጃቸው የባሰ የዱንያ ፍቅር ላይ እንዳትዘፈቅ ለልጄ አትሆንም አሉት ።
(ይሄ የዛሬ 1300 አመት ነው የተከሰተው ። በሰይዳችን ﷺ ምስክርነት ምርጥ የተባለው ዘመን ላይ። ለእኛ አላህ ይዘንልን በሰፊ ቸርነቱም ያካበን

09/20/2022

ቢሽር ቢን ወሊድ ( 237 አ.ሂ. )

የኢማም አቡ ሐኒፋ ዒልም ወራሽ የሆኑት የኢማም አቡ ዩሱፍ ልዩ ደረሳ ናቸው ።

እንዲህ ይላሉ :

«እነ ኢብኑ ዑየይናህ ጋር እንቀመጣለን ፣ አንዲት አስቸጋሪ ጥያቄ ሲመጣ ..

እዚህ ከተቀመጣቹት ውስጥ የኢማም አቡሐኒፋን ዕውቀት የተማረ አለ ? ይላሉ ።

ቢሽር አለ ይባላል..

ጥያቄውን መልስ ስጥበት ይሉኝና እመልሳለው ።

ከዛም : " ለፊቅሂ አዋቂዎች እጅ መስጠት ለዲኑ ደህንነት ነው " ይላሉ »

09/15/2022

የፍትሀዊው መሪ የዑመር ቢን ዐብዱል ዐዚዝ ልጆችን አደብ አስተማሪ ነበሩ ። ትልቅ ዓሊምና ሊቅ ።
ሴት ልጃቸውን ለትዳር ፈልጎ አንድ ወጣት ወደሳቸው መጣና ጠየቃቸው ።

እሳቸውም : ልጄ ለአንተ አትሆንህም .. ልብስ ትውዳለች አሉት ( ታስቸግርሀለች ማለታቸው ነው )

እሱም : የምትፈልገው ነገር በደንብ አለኝ አላቸው

እሳቸውም : አሁን.. አንተ ለሷ አትሆናትም አሉት

መጀመርያ ልጃቸው ዱንያን ስለምትወድ እንዳታስቸግረው ብለው ነበር ።
ከዛ ግን እሱም ዱንያን እንደሚወድ ሲያውቁ በዱንያ እንዳይፈተኑና ልጃቸው የባሰ የዱንያ ፍቅር ላይ እንዳትዘፈቅ ለልጄ አትሆንም አሉት ።

(ይሄ የዛሬ 1300 አመት ነው የተከሰተው ። በሰይዳችን ﷺ ምስክርነት ምርጥ የተባለው ዘመን ላይ። ለእኛ አላህ ይዘንልን በሰፊ ቸርነቱም ያካበን

08/30/2022

ሰይደቲና ዓኢሻ ረ.ዐንሀ :

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ አሉኝ : " በእኔ ደስተኛ ስትሆኚና በኔ ላይ ስትከፊ አውቃለው "

" እንዴት አወቃቹ ? " ብዬ ጠየቅኳቸው

እሳቸውም : " ደስተኛ ስትሆኚ ለመማል ስትፈልጊ : [ላ ወረቢ ሙሐመድ / በመሐመድ ጌታ እምላለው ] ትያለሽ ...
ከኔ ጋር ተቆጥተሽ ከሆነ ደሞ [ ላ ወረቢ ኢብራሂም / በኢብራሂም ጌታ.. ] ትያለሽ " አሏት

" አዎ .. ወላሂ ያረሱለላህ ስምህን ብቻ ነው ማኮርፈው [ የምተወው ] " አልኳቸው ..

08/18/2022

ዛሂዱ ተቂዩ ሙጃሂዱ የምርጡ ሰለፎች ዘመን ምርጥ ሰዪዲ ዐብዱሏህ ኢብኑል ሙባረክ ተጠየቁ ..

«ሰዎች ማለት እነማን ናቸው ? »

እሳቸውም : «ዑለማዎች» አሏቸው

«ወራዳዎችስ ?» ተብለው ሲጠየቁ

«እነዛ ዱንያን በዲን ስም የሚበሉ» ብለው መለሱ

📗 ኢማሙል ጓዛሊ'ይ - ኢሕያእ ዑሉሙዲን :v

08/02/2022

" አንድ ጉዳይ ካስጨነቀህ ትግስት አድርግ ፤ ሶብርክ ከደከመ የረህመት በሮችን ከፋች ይሆነውን ጌታህን ጠይቅ ቸር ነው ጭንቀትህን ይገፍልሀል.. ፍጡራንን ግን ዲንህን ክፍያ አድርገህ በማመሳሰል ጥቅምን ከመፈለግ ተጠንቀቅ ! "

📗 ሶይዱል ኻጢር

07/30/2022

«ውሀ ማጠጣት ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ከትልቅ ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው ። አንዳንድ ታቢዒዮች : " ወንጀሉ የበዛ ውሀ ማጠጣትን ያብዛ " ይሉ ነበር። ውሻን ውሀ ያጠጣ ወንጀሉ ከተማረ ሰውን ሙዕሚንን አላህን አንድ ያደረገን ያጠጣና ያዳነስ እንዴት ሊሆን ነው ..»

📗 ኢብኑ በጧል - ሸርሑል ቡኻሪይ : (5/503)
፡=========================

የአንድ ያላወቅከው ሰው አንጀት አርሰህ ነገ የቂያማ ቀን የወንጀልህ መማሪያ ሰበብ ሆኖ ልናገኘው እንችላለን

07/28/2022

ኢማም አስ-ሱዩጢ'ይ ኪታባቸው ላይ " ሙስሐፍ " የምትለውን ቃል ሰሓባዎች ከሀበሻ እንደወሰዷትና ቁርአንን እንደሰየሙባት ሲናገሩ :-

«ሰይዲ አቡ በክር ረ.ዐ ቁርአንን ከሰበሰቡ ቡኋላ ስም ስጡት አሉ ..አንዳንዶቹ "ኢንጂል" እንበለው አሉ.. ግን አልወደዱትም። "ሲፍር" እንበለው አሉ አንዳንዶቹ ። የሁዶች ኪታባቸውን ስለሰየሙበት ይሄንም አልወደዱትም። ሰይዲ ኢብን መስዑድ ረ.ዐ. : " ሐበሻ ውስጥ ኪታብ አላቸው 'ሙስሐፍ' ይሉታል.. በዚህ ሰይሙት " አሉ..በሀሳባቸውም ተስማሙ..»

📗 አል-ኢትቃን ፊ ዑሉሚል ቁርኣን : (1/184)

07/06/2022

አል ኢማም ሸረፉዲን አን-ነወዊይ

ሀጅ ወይም ዑምራ ያደረገና መካ የደረሰ ሰው ስለሚወደድለት ነገር እያወሩ :

{ መካ ውስጥ በክብር የታወቁ ቦታዎችን መዘየር ይወደድለታል ፤ አስራ ስምንት ቦታዎች ናቸው ፤ ከነሱ ውስጥ የተወለዱበት ቤት ፤ የኸድጃ ረ.ዐ ቤት ፤ ዳሩል አርቀም መስጊድ ፤ የሰውር ዋሻ ፤ የሒራ ዋሻ ፤ መናሲክ የተሰኘው ኪታቤ ላይ ዘርዝሬያቸዋለው .}

07/05/2022

" የአላህን ትልቅነት ያወቀ .. ፍራቻው ይጨምራል
የጌታውን ቁጣ የፈራ .. ስራው ያምራል
ፍራቻ ልብ ውስጥ ሲገባ የአሉባልታነትን በሽታ ከልብ አውጥቶ ያድናል .. ሙዕሚን ለሆነ አላህን መፍራት በቂና ምርጥ አደብ ሰጪ ነው .."

- መዋዒዝ ኢብኑል ጀውዚይ

Address

Dallas, TX

Telephone

+14699871814

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zemzem - Ethiopian Muslims Islamic Knowledge Center in Diaspora posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Zemzem - Ethiopian Muslims Islamic Knowledge Center in Diaspora:

Share