መንፈሳዊ ቃል Spiritual Word Fasil Getachew

መንፈሳዊ ቃል Spiritual Word  Fasil Getachew "The Spirit gives life; the flesh counts for nothing. The words I have spoken to you—they are full of the Spirit and life."

https://youtu.be/mIyXhMa_5Ww?si=lQbudllUiVUIAfOX
08/14/2025

https://youtu.be/mIyXhMa_5Ww?si=lQbudllUiVUIAfOX

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XXI. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info visi...

08/08/2025
https://youtu.be/jcsxY0LHnG8?si=b41DAbVWLst1w85O
07/08/2025

https://youtu.be/jcsxY0LHnG8?si=b41DAbVWLst1w85O

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XVI. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info visi...

https://youtu.be/v9R78LmQ1Fk?si=f9B9N7ZPzf7pAjkr
07/08/2025

https://youtu.be/v9R78LmQ1Fk?si=f9B9N7ZPzf7pAjkr

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XVII. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info vis...

https://youtu.be/aPUGXUHK7mY?si=cxM-4WJvVB6BuvE8
07/08/2025

https://youtu.be/aPUGXUHK7mY?si=cxM-4WJvVB6BuvE8

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XVIII. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info vi...

““ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ ...
07/08/2025

““ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ።”
— ዘጸአት /Exo 6፥6
“"Therefore, say to the Israelites: 'I am the Lord, and I will bring you out from under the yoke of the Egyptians. I will free you from being slaves to them, and I will redeem you with an outstretched arm and with mighty acts of judgment.”

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XIX. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info visi...

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤”  — መዝሙር 6፥4“Turn, O Lord, and deliver me; save me because of your unfa...
04/14/2025

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤”
— መዝሙር 6፥4
“Turn, O Lord, and deliver me; save me because of your unfailing love.”
— Ps 6፥4
“ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤ በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው።”
— መኃልየ. 2፥4
“He has taken me to the banquet hall, and his banner over me is love.”
— Song 2፥4

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part XII. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info visi...

https://youtu.be/75T5iDqMvgc?si=v3WKExeX__Cbk-QO
04/05/2025

https://youtu.be/75T5iDqMvgc?si=v3WKExeX__Cbk-QO

"እግዚአብሔርን ማወቅ!" "Knowing God!" Part X. Pastor Fasil G. Tafesse ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ/ መጋቢ/ . Sunday Worship Amanuel Church አማኑኤል ቤተክርስቲያን ባፍሎ ኒዮርክFor more info visit ...

ቅዱሳን ወገኖቼ፤ እንኳን ለአዲስ ዓመት በሰላም አብሮ አደረሰን። መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።የዘመናትና የአመታት ሁሉ ባለቤት የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር መጪውን አዲስ ዘመን ይባርክላ...
09/11/2024

ቅዱሳን ወገኖቼ፤ እንኳን ለአዲስ ዓመት በሰላም አብሮ አደረሰን። መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።

የዘመናትና የአመታት ሁሉ ባለቤት የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር መጪውን አዲስ ዘመን ይባርክላችሁ።

ዳንኤል 2፥20 “ጥበብና ኀይል የእርሱ ነውና፣ የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ።
²¹ ጊዜንና ወቅትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን በዙፋን ያስቀምጣል፣ ደግሞም ያወርዳቸዋል፤ ጥበብን ለጠቢባን፣ ዕውቀትንም ለሚያስተውሉ ይሰጣል።
²² የጠለቀውንና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፤ ብርሃንም ከእርሱ ጋር ይኖራል።

የእግዚአብሔር የጽድቅ ብርሃን በላያችን ላይ ደምቆ የሚበራበት፤ ጨለማና የጨለማው ሥራ የሚገፈፍበት የክብር ዘመን ይሁንልን።

መጋቢ ፋሲል ጌታቸው
አማኑኤል ቤ/ክር ባፎሎ, ኒዮርክ

አስራ ስምንተኛ ቀን ሐሙስ ኦክቶበር 26/2023 ከጌታ በረት ውጪ ያለው ህዝብ በዓለም ካለው ድንዛዜ አምልጦ ነፍሳቸውን የሚያድኑበትን መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ አጥብቀን እንፀልያለን።  ...
10/29/2023

አስራ ስምንተኛ ቀን ሐሙስ ኦክቶበር 26/2023 ከጌታ በረት ውጪ ያለው ህዝብ በዓለም ካለው ድንዛዜ አምልጦ ነፍሳቸውን የሚያድኑበትን መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ አጥብቀን እንፀልያለን።
✝️እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ስለሚፈልግ፤ አሳቡም ሆነ አደራረጉ የመዳኛቸውን መንገድ መቀየስ ነው። 1ጢሞቴዎስ 2፡4 እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። 5አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 6ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 7እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።
🕎 እግዚአብሔርም ዘወትር ለዚህም ታላቅ የምሥራች ሰባኪና አዋጅ ነጋሪዎችን በመምረጥ እያሰማራ፤ መልዕክቱን ለህዝብ ሁሉ እያደረሰ ይገኛል። የቤተክርስቲያንም ትልቁ ታልዕኮዋ በክህነት ተግባሯ ጸንታ በመቆም ለምድር ህዝብ ሁሉ መማለድ ነው።
ዮሐንስ /John/ 3፡16 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤
¹⁷ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።
¹⁶ "For God so loved the world that he gave his one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life.
¹⁷ For God did not send his Son into the world to condemn the world, but to save the world through him.

🔔 ጌታ ኢየሱስ ከዚህ በረት ያልሆኑ በጎች አሉኝ ሲል፤ በውጭ ያሉት እየታዩትና እየጠበቁት እንደሆነ ስለተረዳ ነው። በአሁኑ ጊዜም የእኛን ጸሎትና ልመና መልስ የሚጠብቁ ከበረታችን ውጪ የሆኑ ብዙ ነፍሳት እንዳሉ ማወቅ አገልግሎታችንን ያፋጥነዋል።
— ዮሐንስ /John/ 10፥16
“ከዚህ ጒረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት አለብኝ። እነርሱም ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ።”
“I have other sheep that are not of this sheep pen. I must bring them also. They too will listen to my voice, and there shall be one flock and one shepherd.”
ዘካርያስ 9 :9 “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
¹⁰ ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።

ሐዋርያት ሥራ 13፡46 “ጳውሎስና በርናባስም በድፍረት እንዲህ አሏቸው፤ “የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገር አለበት፤ እናንተ ግን ናቃችሁት፤ በዚህም የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ ስለ ፈረዳችሁ፣ እኛም ወደ አሕዛብ ዞር ለማለት እንገደዳለን። 47ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤
“ ‘ድነትን እስከ ምድር ዳርቻ ታደርስ ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ።’ ”
48አሕዛብ ይህን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቃል ክብርን ሰጡ፤ ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁትም ሁሉ አመኑ።

✔️ሐዋሪያው ጳውሎስ በሰጠው የማሳሰቢያ ምክር ውስጥ ከሁሉ አስቀድሞ እንዲጸለይላቸው ካዘዘን ነገሮች መካከል አንዱ “ለሰዎች ሁሉ” መጸለይ ነው። ሰዎች ሁሉ ሲል ሁሉንም ያጠቃልላል። እምነታቸው፤ፀባያቸው፤እውቀታቸው፤አኗኗራቸው ሁሉ ይለይያያል። ሁሉም የእኛ ልመና፤ጸሎትና ምልጃ ያስፈልጋቸዋል።
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1 እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤
ኢሳይያስ 65 ፡1 “ላልለመኑኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው። ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣ ‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት።
² ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣

🔯 ከአይሁድ ወገን እንኳን፤ በአሁኑ ጊዜ የተመረጡ ስላሉ መጸለይ አለብን። አምላካቸውን ያላወቁና በድርጊታቸውም የሚያስቆጡ ቢሆኑም፤ እኛ መዳንን በነፃ እንደተቀበሉ አማኞች በሁሉም ዓይነት እምነት ውስጥ ለሚገኙ የዓለም ህዝቦች መጸለይ ያስፈልገናል። ከእንቅልፍ የሚነሱበት ወቅት ሊሆን ይችላል።
ሮሜ 11፡1 እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ።
² እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። ኤልያስ በእስራኤል ላይ ክስ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንዳቀረበ፣ መጽሐፍ ስለ እርሱ ምን እንደሚል አታውቁምን?

⁵ በአሁኑ ጊዜም እንደዚሁ በጸጋ የተመረጡ ትሩፋን አሉ።

🔔 በጨለማ ውስጥ ባሉ ሰዎች መፍረድ እጅግ ከባድ ነው። በርግጥ መጽሐፍ ቅዱስም ፍረዱባቸው አይለንም። በውስጥ /በዳኑት/ ወገኖች አድራጎት ላይ ልንፈርድ፤ልንወቃቀስ፤ልንገስጽ፤ልንመክር እና ልንዘልፍ እንችላለን። በውጪ ላሉት ግን ማድረግ ያለብን፤ ጌታ እንዲያበራላቸው፤ ለመዳን እንዲያዘጋጃቸው፤ እንዲያነቃቸው፤ እንዲቀሰቅሳቸው እና ወንጌሉን እንዲልክላቸው አጥብቀን መጸለይ ነው።
ኤፌሶን 5፡14 “ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣
“አንተ የተኛህ ንቃ፤ከሙታን ተነሣ፤ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።
እንዲሁም በኢሳያስ ትንቢት ላይ ምዕራፍ 9፡2 “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤
በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው” ተብሏል።

🙏 ዛሬም የእግዚአብሔር ብርሃን በህዝብ ሁሉ ላይ ይብራ! ለሞት የተኛው ህዝብ ከእንቅልፉ ነቅቶ እንዲዘጋጅ ጌታ መንፈስ ቅዱስ የሚቀሰቅሰውን ደወል በነፍሳት ጆሮ ላይ ያጮኸው ዘንድ እንማልዳለን። እግዚአብሔርም ይሰማናል። ለእርሱ ክብር ይሁንለት አሜን!

Address

Buffalo, NY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንፈሳዊ ቃል Spiritual Word Fasil Getachew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to መንፈሳዊ ቃል Spiritual Word Fasil Getachew:

Share

Category