St Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

St Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from St Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, Religious organisation, 26 Winthrop Street, Boston, MA.

https://www.facebook.com/735465573315241/posts/1311506852377774/
03/18/2020

https://www.facebook.com/735465573315241/posts/1311506852377774/

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ወደፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ፀልዩ "ማቴ.26÷41

በቦስተን እና አካባቢው የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ እንደሚታወቀው በከተማችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መንግስት በአንድ ቦታ ላይ ከ 10 ሰው በላይ መሰብሰብ እንደማይቻል ማስታወቁ ይታወቃል። ይህንንም መሰረት በማድረግ ምንም እንኳን ቤተክርስቲያን የመዳኛ ቦታ መሆኑ ብናቅም ህግን ተከትለን መንቀሳቀሳችን ደሞ ተገቢ በመሆኑ ቤተክርስቲያናችን መንግስት አዲስ የተሻሻለ ህግ እስኪያወጣ ድረስ ለአገልግሎት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ እያሳወቅን ነገር ግን የእለተ ሰንበት አገልግሎት በቀጥታ በቤተክርስቲያንዋ ፌስፑክ ወይም ዩቲውብ የሚተላለፍ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን ።
ስለዚህም ቤተክርስቲያንናችን ለአገልግሎት ክፍት እስክትሆን ድረስ ከቤተክርስቲያንዋ የሚተላለፈውን መልእክት የቤተክርስቲያንዋን ፌስፑክ ላይክ ወይም ፎሎው በማድረግ እንድትከታተሉ እና ባላችሁበት ቦታ በፀሎት እና በሱባዔ በመሆን ትቆዩ ዘንድ ቤተክርስቲያን መልእክቷን ታስተላልፋለች።

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐ 5÷4

የቦስተን መካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ወኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

01/03/2019

ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ በአዲ አበባ

Video credit : Daniel Haileyesus Abegaz

10/14/2018

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

08/14/2018
08/09/2018

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በሎሳንጀለስ ከተማ በጥምቀት በዓል ያቀረቡት መዝሙር። እመቤታችንን ውብ በሆነ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ተመልከቱ። ቅዱስ አባታችን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን።

አማን በአማን(2) የአምላክ እናቱ
ተማጽነናል ባንቺ(2) ድንግል ወላዲቱ

የተዋህዶ ልጆች በአንድነት ቆመን/2/
ሰዓሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን· · ·

07/13/2018
12/12/2017

የህወሃት አገዛዝ ትዕግስተኛውንና በፈሪሃ እግዚአብሔር በተመሠረተ ጨዋነት ላይ የሚኖረውን ሕዝባችንን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እንዲያመራ እየገፋፋው ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ።
“ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም ”በሚል ርዕስ መግለጫ ያወጣው በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ፖለቲካ አገርን ለመምራት መሞክር በዘመኑ ያለመኖርን ያህል ይቆጠራል በዓለም መድረክ ፊትም ያጋልጣል ብሏል ።
ቅዱስ ሲኖዶሱ እግዚእብሔርን አጋዥ በማድረግ እርስ በርሳችሁ እየተረዳዳችሁ፥ በጸሎትና በምህላ ይህን ክፉ ቀን አሳልፉ ሲል በእግዚአብሔር ስም ጥሪውን አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ “ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም”በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫው ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ስም የዕለት ጥቅም ለማግኘት የሚጥሩ ፖለቲከኞች እንዳያታልሏችሁ ሲል አደራውን አስቀምጧል።

በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው ቅዱስ የሲኖዶሱ መግለጫ ሲቀጥልም የህወሃት አገዛዝ ወደ ስልጣን ሲመጣ አስፈሪውን ደርግ አባሮ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ እየፈጸመው ያለው ተግባር ግን ከደርግ እጅጉን ይከፋ ሆኗል ብሏል።
ሲኖዶሱ እንደሚለው ዜጎቻችን በእንግልትና በስደት ላይ ሆነው ለሽያጭ ሲቀርቡ ማየት፣የመቶ አመት አሮጊት በራሳቸው ዜጎች በግፍ ተደብድበው እንዲገደሉ ሲደረግና የዕለት ተዕለት የህዝብን ሰቆቃ መስማት ልብን የሚያደማ ድርጊት ነው ብሏል ሲኖዶሱ።
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ፥ ሥልጣንንም እርሱ ካላከበረ በቀር የጠነከረ ወታደር በማቆምና መሣሪያ በማስታጠቅ ሥልጣንን ማቆየት በፍጹም አይቻልም ብሏል ሲኖዶሱ በመግለጫው።
ሲኖዶሱ እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ ሕዝባችን አንድ በመሆንና በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለማስጠበቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።
አገዛዙ ደግሞ ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ትዕግሥተኛውንና በፈሪሃ እግዚአብሔር ላይ በተመሠረተ ጨዋነት የሚኖረውን ሕዝብ ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እየገፋፋው ነው ብሏል።
ይህ ደግሞ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ፖለቲካ ሀገርን የመምራት ያህል ይቆጠራል ይላል የሲኖዶሱ መግለጫ።
ከየትኛውም የሕወሃት ፖለቲከኛ አንደበት ኢትዮጵያ የሚል ቃል ሰምተን አናውቅም ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ የዚህ አገዛዝ ዋናው መለያ በህዝብ ውስጥ ልዩነትና ዘረኝነትን ማስፈን ነው ሲል ገልጿል።
እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብራችሁ የኖራችሁ አሁንም የምትኖሩ ናችሁ ፣ለዕለት ጥቅም የቆሙ ፖለቲከኞች አያታሏችሁ ፣ እነርሱ ያልፋሉ እናንተ ግን ሁልጊዜ ትኖራላችሁ ፣ እናንተ ስታልፉ ልጆቻችሁ ይተካሉ በማለት ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ትማጸናለች ብሏል መግለጫው።
መግለጫው በፖለቲካ ስም የዕለት ጥቅም ለማግኘት የሚጥሩ ፖለቲከኞች እንዳያታልሏችሁ አደራ ብላለች ቤተክርስቲያኗ ብሏል ።
እናንተ የተለያየ ቋንቋ የምትናገሩ ነገር ግን በአንድ ምድር የምትኖሩ አንድ ሕዝብ ናችሁ ፣ ታሪክ የሚያስረዳው ይህንን ሀቅ ነው ።
ልዩ ናችሁ የሚሏችሁ ፖለቲከኞች ሌላ ሥራ አጥተው የናንተን ልዩነት ለሥራ ማግኛ ለማድረግ ነውና ተጠንቀቁ ብላለች ቤተክርስቲያኗ።
እናንተ አብራችሁ የኖራችሁ ፣ለወደፊትም አብራችሁ የምትኖሩ ጨዋና ኩሩ ሕዝብ ናችሁ በሚል ጽሁፉን ያሰፈረው የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ እግዚእብሔርን አጋዥ አድርጋችሁ ፣ እርስ በርሳችሁ እየተረዳዳችሁ በጸሎትና በምህላ ይህን ክፉ ቀን አሳልፉ ሲል በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል።

Address

26 Winthrop Street
Boston, MA
02119

Telephone

+16174270068

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share