I Worship አመልክሃለሁ

I Worship  አመልክሃለሁ The aim of the page is to avail and promote best collection of gospel songs with their lyrics.

The songs that we are going to post are all Gospel songs including protestant, Orthodox, Catholic in different languages English, Amharic, Oromiffa, Tigrigna

የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ...ነህምያ 8: 10
10/31/2024

የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ...

ነህምያ 8: 10

09/15/2024

Remember not the former things, nor consider the things of old

ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18-19

የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።

እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥

እናንተም አታውቁትምን?????

“በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ። “

09/08/2024

When all hope fades, God’s promises still stand firm.

ዘሪ ሊዘራ ወጣ። እግዚአብሄርም ይዘራል ጅኒዉም ይዘራልለየትኛ ዘር የሚመች ልብ ነው ያለን ??ጌታ ይርዳን ። በኢየሱስ ስም የክፉን ዘር የሚያቃጥል፣ የሚያከሽፍ የመንፈስ ቅዱስ እሳት ልባችን ...
07/28/2024

ዘሪ ሊዘራ ወጣ።

እግዚአብሄርም ይዘራል
ጅኒዉም ይዘራል

ለየትኛ ዘር የሚመች ልብ ነው ያለን ??

ጌታ ይርዳን ።

በኢየሱስ ስም የክፉን ዘር የሚያቃጥል፣ የሚያከሽፍ የመንፈስ ቅዱስ እሳት ልባችን ውስጥ ይንደድ ። አሜን !!!

We are living in a very crazy world so, we need a Holy fire 🔥 to defeat 🙌

07/06/2024

የዘላለም ሕይወት በነፃ ! ! የእግዚአብሔር ስጦታ ነው
———————————. ————————————
The most valuable asset in this life is : to have an “eternal life”

How can we get it ???

የዮሐንስ ወንጌል 3:16

በእርሱ የሚያምን ሁሉ “የዘላለም ሕይወት” እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth in him should not perish, but have everlasting life.

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ For by grace are ye saved through faith; and that not of yourselves: it is the gift of God:

07/05/2024

Worshiping the most high God is a privilege!

እግዚአብሄርን ማምለክ መቻል እድል ነው

ነገን የማንፈራው ባለን ነገር ሳይሆን ባለን ጌታ ነው ።  ተስፋን የሰጠን እርሱ የታመነ ነው።ተስፋችን ለነገ ብቻ አይደለም ደግሞ ለዘላለም ሂዎት ከኢየሱስ ጋር አብሮ ለመኖር ነው።ተስፋ ሰጭ ...
06/25/2024

ነገን የማንፈራው ባለን ነገር ሳይሆን ባለን ጌታ ነው ። ተስፋን የሰጠን እርሱ የታመነ ነው።

ተስፋችን ለነገ ብቻ አይደለም ደግሞ ለዘላለም ሂዎት ከኢየሱስ ጋር አብሮ ለመኖር ነው።

ተስፋ ሰጭ ኢየሱስ ብቻ ነው ።

ዕብራውያን 10:23 የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤

የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው።…….በኢየሱስ እግር ስር መቀመጥ ….. ቃሉን መስማት የሉቃስ ወንጌል 10:41 ኢየሱስም መልሶ። ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታ...
06/22/2024

የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው።

…….በኢየሱስ እግር ስር መቀመጥ ….. ቃሉን መስማት

የሉቃስ ወንጌል 10:41

ኢየሱስም መልሶ። ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።

Let’s make a choice to seat at Jesus’s feet and listen to his word.

እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ---------------------------------------------------------የማቴዎስ ወንጌል 1128 እናንተ ደካ...
06/20/2024

እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ
---------------------------------------------------------

የማቴዎስ ወንጌል 11

28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

30 ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።

06/03/2024

...የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።

ኢያሱ 24:15

05/31/2024

ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።

መዝሙረ ዳዊት 37:25

05/28/2024

ሰይጣን ባለጌ ነው ; እግዚአብሔር ግን ጨዋ ነው።
————————————————————————

ሰይጣን ባለጌ ነው ባዶ ቦታ ልብህ ውስጥ ካየ ሳያስፈቅድ ይቀመጣል።

እግዚአብሔር ግን ጨዋ ነው ፈቃዳችን ይፈልጋል በደጅ ቆሞ ያንኳኳል።

ፈቃዳችን ለእግዚአብሔር ሰተን እሱ ይቆጣጠረን ።

የዮሐንስ ራእይ 3:20

እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
————————————————————————
ስለዚህ፣
ለእግዚአብሔር ወይ ለሰይጣን አልሆንም ብንል ቦታው እስኪለቀቅ የሚጠብቅ ሳያንኳኳ ዘው ብሎ የሚገባ ሰይጣን እሱ ይገባል🥹

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:8

በመጠን ኑሩ ንቁም፥
ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤

Address

Baltimore, MD
21207

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when I Worship አመልክሃለሁ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category