New Creation Church Of Denver

New Creation Church Of Denver Our passion is Sharing the Grace of the Father as express through Jesus Christ as while as what it mean walking in Freedom over religion and legalism.

ቅዳሜ 4pm -7pm  እና እሁድን 10:30-1pm  ከእኛ ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።  "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው" ዕብ 13:8
10/30/2024

ቅዳሜ 4pm -7pm እና እሁድን 10:30-1pm ከእኛ ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

"ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው" ዕብ 13:8

06/15/2024

የእግዚአብሔር ጸጋ አዳም ካጠፋ በኃላ ሰውን ለማዳን የተፈጠረ አዲስ መፍትሔ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱን እንደ አባት፣ ወልድ እና መንፈስ ለዘለአለም የመስጠት ውጤት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥላሴ ውስጥ እንደ ዘላለማዊ ልጅ ሆኖ የነበረውን ጸጋ ለሰው አመጣ (“ጸጋንና እውነትን የሞላበት፣ ዮሐንስ 1፡14–18)። ስለዚህም “የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ” በመቀበል “በእግዚአብሔር ፍቅር እና በመንፈስ ቅዱስ ኅብረት” መለኮታዊ ሙላት እንሳተፋለን።
"የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።" 2ኛ ቆሮንቶስ13፥14

01/30/2024

በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ ማለት ምን ማለት ነው?

ሰው ሁሉ በኀጢአቱ ሙት ነውና በመጀመሪያ እግዚአብሔር ራሱ የሞተውን ሰው ከሞተበት ካላስነሳው ፤ እንደ አልዓዛር ህይወት ካልሰጠው በቀር ማመን አይችልም ሲባል እንሰማለን። ነገር ግን ሰው ሁሉ በኀጢአቱ ሙት ነው ማለት እግዚአብሔርን አይሰማም ማለት እንዳልሆነ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት የነበሩ አባቶች ምስክሮች ናቸው ። ለምሳሌ ኖህ፣ አብርሃም ፣ ሙሴ---- ነብያት ። እነዚህ ሁሉ ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአት የሆነው ክርስቶስ ደም ከመፍሰሱ በፊት ለእግዚአብሔር ድምፅ ምላሽ ይሰጡ ነበርና።

ሙታን ነበራችሁ የሚለውን ቃል በትክክል የሚፈታልን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 የሚገኘው የአባታችንን ፍቅር የሚያሳየን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ስናነብ ነው።

"አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ፦ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤ የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን፤ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም’። ደስም ይላቸው ጀመር" ሉቃስ 15፥22- 24

አንድ ሰው በኃጢያቱ ሙት ነበር ማለት ጠፍቶ ነበር ማለት እንጂ እንደ አልዓዛር በድን (አስከሬን) ነበር ማለት እንዳልሆነ ይህ ቃል በግልጽ ያስተምረናል!!

ብሩካን ናችሁ!!

01/27/2024

"ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው" ሮሜ 9፥13

የእኔ ጥያቄ እግዚአብሔር ኤሳውን መጥላቱ ሳይሆን (እርሱም ቢሆን ገብቶኛል ለማለት ሳይሆን) የሚገርመኝ ግን ያዕቆብን መውደዱ ነው።
እንዴት ያዕቆብን ወደደው? ምን የሚያስወድድ ነገር ነበረው? ከወንድሙ የባሰ አልነበረም ወይ? ይህ ለትምህርታችን ይሁን። እንደ ያዕቆብ ሁላችን እንዴት ተወደድን? በምን እና ከማን ተሽለን?
ክፉ ሆነ መልካም ስራችን ምክንያት ሳያደርግ ያለ ምንም ምክንያት የወደደን እግዚአብሔር ይመስገን!!!

01/06/2024

መልካም ልደት/ Merry Christmas/

ይህን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ቀን በምናስብበት በዚህ እለት አንዳንዶች ሁኔታው ተመቻችቶላቸው በደስታና የተለያየ የምግብ አይነት በመመገብ ሌሎች ደግሞ ተቸግረው፣ የሚወዱትን ሰው በሞትና በፍች አጥተው ወይም ታመው ሆስፒታል ሆነው ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን ይህ እለት የሚያስታውሰን እግዚአብሔር ወልድ ሰው የሆነው ኃጢአታችንን በራሱ እያነጻ ከእኛ ጋር ለመሆን ነው። በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ብቻችሁን አይደላችሁም! አማኑኤል! እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው!! በዚህ ደስ ይበላችሁ ። Merry Christmas!!

"ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም፡ አማኑኤል፡ ብላ ትጠራዋለች።" ኢሳይያስ 7፥14

ኑ የእግዚአብሔርን ጸጋ እንካፈል! የፊታችን እሁድ/ Jan 7th/
01/04/2024

ኑ የእግዚአብሔርን ጸጋ እንካፈል!
የፊታችን እሁድ/ Jan 7th/

Address

1955 S Telluride Street
Aurora, CO
80013

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Creation Church Of Denver posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to New Creation Church Of Denver:

Share