The Reconciliation Gospel of Jesus Christ

The Reconciliation Gospel of Jesus Christ The ministry of Reconciliation was first performed through Jesus Christ and we are now reconciled with God and we have now given the responsibility.

Gerji Emmanuel አደራው የእኔም ነው!
10/29/2024

Gerji Emmanuel

አደራው የእኔም ነው!

እንግዲህ የትኛው ነው የእግዚአብሔር ቃል? የትኛውስ ነው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ? ትንቢተ ሚልኪያስ ወይስ መጽሃፈ ሲራክ?
06/11/2024

እንግዲህ የትኛው ነው የእግዚአብሔር ቃል? የትኛውስ ነው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ? ትንቢተ ሚልኪያስ ወይስ መጽሃፈ ሲራክ?

ብዙ ሰው ሶፊን ሲያብጠለጥል ብመለከት በመጀመሪያ ከአስቴር በዳኔ ጋር ከዚያም በቢኒያም ሽታዬ በተቀነባበረው የተዋህዶ መምህራን ብቻዋን የሞገቱባትን ቀጥሎም በእግረኛው ሚዲያ ላይ ከተክለሃይማኖ...
02/06/2024

ብዙ ሰው ሶፊን ሲያብጠለጥል ብመለከት በመጀመሪያ ከአስቴር በዳኔ ጋር ከዚያም በቢኒያም ሽታዬ በተቀነባበረው የተዋህዶ መምህራን ብቻዋን የሞገቱባትን ቀጥሎም በእግረኛው ሚዲያ ላይ ከተክለሃይማኖት ጋር ባደረፈችው ውይይት ስመለከት ለሶፊ ትልቅ ክብር አዳብሮብኛል።

ኮርነር ሊያስይዙዋት ሲሞክሩ፣ ሲያንጋጥጡዋት፣ ሊያሸማቅቁዋት ሲሞክሩ አንድ እሱዋን ነጥለው የፕሮቴስታንትን እምነት ሊያጠለሹ ሲጥሩ መድረኩን የተቆጣጠረችበት መንገድ አስደናቂ ነበር።

ከአስቴር ጋር የነበረው ውይይት ለሚድያ ግብዓት ሊውል የሚገባው ሳይሆን በሁለት ጓደኛሞች መካከል ሻይ ቡና እያሉ የሚያወጉትን ጨዋታ በቪድዬ ቀርጾ እዩት እንደማለት ነው የምቆጥረው።

ቢኒያም ሽታዬ (ፍቅረየሱስ) ዓላማው በውል ያላወቀ ቢችል ተዋህዶን ማጽደቅ ባይቻል ፕሮቴስታንትን አጠልሽቶ ለማቅረብ የሄደበትን ጥግ ማየት ይቻላል። እናም ያቀረባቸው አንዳንድ መምህራንና ዲያቆናት ሶፊን በአንደበታቸው እንወድሻለን እናከብርሻለን እያሉ ነገር ግን ንግግራቸው ሽርደዳ የበዛበትና ሊያሸማቅቋት ሱሞክሩ ተመልክቻለሁ። ከሃያ ሰባትና ስምንት ዓመታት በፊት በጨቅላ አንደበቴ ጥያቄን ስጠይቅ ያሸማቅቁኝ እንደነበር አሁንም እንደዚያው መሆናቸው ገርሞኛል።

ከሁሉ የሚደንቀው ግን የተክለሃይማኖት ነው። ጋዜጠኛ እንጂ የኃይማኖት ሰው አይደለሁም እያለ በተደጋጋሚ በፕሮቴስታንት እምነት የተወገዙትንና የተነቀፉትን ሰዎች እያቀረበ በግድ የፕሮቴስታንት እምነት ተወካይ በማድረግ የስም ማጠልሸት ተግባሩን ያለማሰለስ ሲያደርግ ከርሞ አሁንም ከሶፊ ጋር ገለልተኛ ነኝ እያለ በግድ የተዋህዶን መልካምነትና የፕሮቴስታንትን ክፉነት ለማመልከት የሄደበት ጥግ ይገርመኛል። "ጋዜጠኛ ነኝ" "የጋዜጠኝነት ኤቲክስ አይፈቅድልኝም" እያለ ነገር ግን የጋዘኝነትን ኤቲክስ በውል ያልጠበቀ የጭቃ ውስጥ እሾክ ሲሆን ተመልክቻለሁ።

በዚህ ሁሉ ግን ሶፊ ግራውንድሽን ስለጠበቅሽ ሳላደንቅሽ አላልፍም።

የተቀነጫጨበ ቪድዬዎችን የምታዩ ሰዎችም በጽድቅ ትፈርዱ ዘንድ ሙሉውን ቪድዬዎችን ብትመለከቱ መልካም ነው።

አስማማው በክርስቶስ

01/02/2024

የዕለቱ ቃል

"ጻድቅ ሆኖ ..."

ማቴዎስ 1:19
"19: እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።"

ጻድቅ ማለት ከኃጢያት የራቀ ብቻ ሳይሆን የሌላውን ጉድፍ ሊገልጥ የማይወድ ሩህሩህ ሰው ነው።

ምንም እንኳን ማርያም በድንግልናዋ በቅድስና ከመንፈስ ቅዱስ ብትጸንስም ጻድቅ የነበረው ዮሴፍ ከጽድቅ ጎድላ ከሌላ የጸነሰች መስሎት ነበር። ገበናዋን ቢገልጥ በወቅቱ የነበረው ህግ ማርያምን በድንጋይ አስወግሮ የሚያስገድል ቢሆንም፣ እንደ ማንኛውም ሚስት ያጨ ወንድ ተደፈርኩ ብሎ ለበቀልም ባለመነሳት፣ ፍትህንም በመፈለግ ክስ ሳይመሰርት በስውር ሊተዋት አሰበ። እንግዲህ ማርገዟ ሲታወቅ እጮኝነትን በማፍረሱም ባለመክሰሱም በጽንሱ አባትነትነት ግንባር ቀደም ተጠርጣሪ በመሆን ሊደርስበት የሚችለውን ስደት ለመቀበል ቆርጦ ነበር።

ስንቶቻችን በገዛ በደላችን ላለመቀጣት ስንል የመለቀቁን ፍየል (scapegoat) የምንፈልግ እንጂ በዳያችንን በነጻ ለቀን ተበድለን ሳለ እንደ በዳይ ራሳችንን ለቅጣት የማንሰጥ መሆናችን ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

እናም በእውነት ጻድቅ ከሆንን የማንበድል ብቻ ሳይሆን በዳይንም የማንከስ ልንሆን ይገባናል።

1 ቆሮንቶስ 6:6-7
"6: ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን?
7: እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?"

ኢሳይያስ 33:22
"22: እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።"

ማሳሰቢያ፦
ይህ ልጥፍ ተነካሁ ተበደልኩ ብለን በራስ ጉዳይ ፍትህን ስለመፈለግ እንጂ ስለ አቅበተ-ዕምነት አይደለም።

አስማማው
01/01/2024
Happy new years.

12/25/2023

ሉቃስ 2:10-15

10: መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
11: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
12: ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።”
13: ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ እንዲህ አሉ፦
14: “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ።”
15: መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ “እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ፡” ተባባሉ።

08/27/2023

Welcome to Heritage Baptist Church Online! We are a church of broken people, blessed in Christ, to be a blessing to the world, all for the glory of God.For d...

08/18/2023

"God is Great, God is Good;
Let us thank Him for our food.
By His hands, we all are fed,
Give us Lord our Daily Bread.

Amen.

child's mealtime blessing"

Humanity at its best
08/13/2023

Humanity at its best

This seal had a bright blue spool stuck around his neck. He likely played with it under water, and it slipped onto his neck, and he could not get it off by h...

Address

Alexandria, VA
22303

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Reconciliation Gospel of Jesus Christ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to The Reconciliation Gospel of Jesus Christ:

Share