Life Centered Holistic Ministry Ethiopia

Life Centered Holistic Ministry Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Life Centered Holistic Ministry Ethiopia, Religious organisation, Addison, TX.

በጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ/ፋውንዴሽን በአድዋ ሙዝየም በተዘጋጀው የሙሉ ቀን ስልጠና ስለ ጊዜ ወይም Reading the Signs of the time"በሚል ርዕስ የተሰጠን ስልጠና እጅግ አስገራሚ ጊዜ...
08/15/2025

በጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ/ፋውንዴሽን በአድዋ ሙዝየም በተዘጋጀው የሙሉ ቀን ስልጠና ስለ ጊዜ ወይም Reading the Signs of the time"በሚል ርዕስ የተሰጠን ስልጠና እጅግ አስገራሚ ጊዜ ነበረን።ይህንን ስልጠና የሰጡት ዶክተር ለማ ደገፋ,ዶክተር ምህረት ደበበ,ዶክተር ቄስ ሳሙኤል ዮናስ,ዶክተር ገለታ እና ሌሎችም።ቄስ ጉዲና ቱምሳ የምድር ቆይታቸው በጣም አጭር ጊዜ ቢሆንም የሰሩት ሥራ እስከ አሁን እያወራ ነው።የእኝህ ጀግና የእግዚአብሔር አገልጋይ ለብዙዎቻችን ጠቃሚ ትምህርት ሆኖልናል።

"የዘመኑን ምልክቶች ማንበብ የሚለው ቃል ለሁሉም ሰው ወሳኝ መልዕክት ነው።“የእግዚአብሔር ወቅት,ጊዜ ወይም ዘመን”የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ በደንብ አብራርተው አስተምሮናል።ከተማሪነው ውስጥ ጥቅቱን እነሆ።የእግዚአብሔር ጊዜ ወይም ዘመን የሚለው ቃል በግሪክ ቃል እንዲህ ይጠራል,“ካይሮስ” (καιρός)፣ ስሆን እሱም "በእግዚአብሔር የተወሰነ፣ በመለኮት የተወሰነ ጊዜን ወይም ዘመንን ያመለክታል።ይህም ሁነኛና እና ዕድለኛ ጊዜን(Opportune) ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ"ክሮኖስ" (χρόνος) የሚለው ደግሞ ተቆጣሪ እና ተቀማሪ ጊዜ,(Calendar),ሰው የምኖርበትን,በምድር ላይ ያለውን ጊዜ ያሳያል።

የካይሮስ ጽንሰ-ሀሳብ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ጊዜ የመረዳት እና የመለየት አስፈላጊነትን የሚያሳይ እና እግዚአብሔር የሰጠንን በአገባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። በክሮኖስ ዙሪያ የተዋቀሩ ዕቅዶች ሊኖረን ቢችልም፣ የእግዚአብሔርን ግብአት መፈለግ እና ካይሮስን ማወቃችን በእሱ ዋና ዓላማ እና ጊዜ ውስጥ እንድንመላለስ ያስችለናል።

ይህ አጠቃላይ እይታ “የእግዚአብሔር ወቅት” በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የካይሮስን በአማኝ ሕይወት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድንና ፕሮግራሙን እንድንረዳ ያስችለናል።እግዚአብሔር ሆይ የአንተ ካይሮስ እንዳያመልጠን አንተ እርዳን።በሰጠን ዘመንና ጊዜ የአንተን ዕቅድ እንድንፈጽም አንተ እርዳን።

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ባዘጋጀው "ፕሮጀክት ዜሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን  በ2030 እ.ኤ.አ,በአምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦች ...
07/16/2025

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ባዘጋጀው "ፕሮጀክት ዜሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን በ2030 እ.ኤ.አ,በአምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦች ሁሉ ተድርሰው ማየት የሚል አዲስ የወንጌል ንቅናቄ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ ከተለያዩ ቤተ-እምነቶች,አብያተክርስቲያናት,ሚኒስትሪዎች,የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች,እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ገለጻ ተድርጓል።

የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረትን በመወከል ፓስተር ኤልያስ ጳውሎስ (የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት መንፈሳዊ ዘርፍ ደይሬክተር እና ዶክተር ቶማስ መለሰ(የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ምክትል ፕረዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ግንኘነት ኃላፍ ፕሮግራሙን ተካፍለዋል።

ቀጣይም በአንድነት ለመስራት በመነጋገር አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙን ተጠናቋል።

  ስልጠና ይሰጣል !
05/30/2025

ስልጠና ይሰጣል
!

ላይፍ ሴንተርድ ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ ከአያት ወንጌል ብርሃን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአገልጋዮች ስልጠና ከ3:00-7:00 በአያት የወንጌል ብርሃን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ነበረን።በዚህ ስ...
05/17/2025

ላይፍ ሴንተርድ ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ ከአያት ወንጌል ብርሃን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአገልጋዮች ስልጠና ከ3:00-7:00 በአያት የወንጌል ብርሃን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ነበረን።
በዚህ ስልጠና የዘርፍ መሪዎች እና የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢዎች እና መሪዎች ተሳትፈዋል።ታላቁን ተልዕኮ መፈጸም እንዲችሉ የሚያደርግ የግማሽ ቀን ስልጠና ነበረን።ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

  ስልጠና ይሰጣል  !
05/16/2025

ስልጠና ይሰጣል
!

በቦሌ አራብሳ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን በነበረው የአገልጋዮች ስልጠና ወደ 150 ለሚሆኑ በተለያዬ ዘርፍ ለሚያገለግሉ ለፓስተሮች,ለቤተክርስቲያን መሪዎች,ለዲያቆናት,ለኳዋሮች,ለወጣት መ...
05/01/2025

በቦሌ አራብሳ ሙሉወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን በነበረው የአገልጋዮች ስልጠና ወደ 150 ለሚሆኑ በተለያዬ ዘርፍ ለሚያገለግሉ ለፓስተሮች,ለቤተክርስቲያን መሪዎች,ለዲያቆናት,ለኳዋሮች,ለወጣት መሪዎች,ለወንጌላውያን ስልጠና ሰጥቻለሁ።

ከጠዋት 3:00 እና 7:00 በሁለት ክፍሌ ጊዜ ተከፍሎ ቆንጆ የትምህርት እና የስልጠና ጊዜ አሳልፈናል።

ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት,ለታላቁ ተልዕኮ ትውለድን የማዘጋጀት ሥራ ቀጥሉዋል።

ለእረዳኝ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን።የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እና መጋቢዎች አመሰግናለሁ።ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል,ወንጌል ያሸንፋል።

  ስልጠና ይሰጣል
04/30/2025

ስልጠና ይሰጣል

04/27/2025
04/20/2025

ስለ እኛ የተገረፈው,የተሰቀለው,የተወጋው,የሞተው,የተቀበው,,በሶስተኛው ቀን ሞትን,ስኦልን,ኃጢአትን,ድያብሎን ድል አድርጎ የተነሳው ኃያሉ እና ጀግናው ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል።ልወስደን ይመጣል,መምጫውም ቅርብ ነው።

ስለዚህ ሁላችንም እንዘጋጅ።ይህንን የፋስካ/የትንሳኤ በዓል ስናከብር ሆነ ስናስብ ከመብል ያለፈ,የተከፈለውን ዋጋ ማሰብ አለብን።በመብል,በመጠጥ,በስካር,በፌሽታ,በጭፈራ,በዳንካራ,እና በሌላም የሚከበር በዓል ሳይሆን የተደረገልንን,የተከፈለውን ዋጋ,የፈሰሰውን ደም እያሰበን የምናሳልፈው በዓል ነው።

ተዘጋጁ,ጌታ ይመጣል ኢየሱስ ክርስቶስ እመጣለሁ እንዳለ ይመጣል,መጀመሪያ እኛን ከኃጢአት እነ ከዲያብሎስ እስራት ልፈታን,ነፃ ልያወጣን,ልዋጀን,በመገረፉ ቁስል ልፈውሰን,የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች ልያደርገን መጥተዋል።እንዲሁም ነፃ አውጥቶናል,ቀንበራችንን ሰብሩዋል,የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች አደረገን።

በእግዚአብሔር ቃል የተነገሩ ሆነ የተጻፈው ትንቢት ተፈጽሟል።የመጽሐፍ ቅዱሳችን ማዕከሉ የኢየሱስ መምጣት,የኢየሱስ መወለድ,የኢየሱስ አገልግሎት,የኢየሱስ ሞት እና ትንሣኤ ስሆን።መወለዱ ተፈጽሟል,አገልግሎቱ ተፈጽሟል,ሞቱና ትንሣኤ ተፈጽሟል።አሁን የቀረው ዳግም ምጽአቱ(መምጣቱ)ነው።እርሱም ቀርብ ይፈጸማል።ሁላችንም ነቅተን ጌታን እንጠብቅ።በፀሎት,የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት,የወንጌል ስርጭት በማድረግ,አቅሜ ደካሞችን በማሰብ,ጌታን እንጠብቅ።ጌታ ይመጣል።

“ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።”

ሐዋርያት 1፥11
“እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።”
— ራእይ 1፥7
(ፓስተር ኤልያስ ጳውሎስ ቃባ ነኝ)

04/05/2025
  ይሰጣል
04/01/2025

ይሰጣል

Address

Addison, TX
1033/1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Life Centered Holistic Ministry Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share