ኢስታንቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን - Mierafe Kidusan St. Mary Church

  • Home
  • Turkey
  • Istanbul
  • ኢስታንቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን - Mierafe Kidusan St. Mary Church

ኢስታንቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን - Mierafe Kidusan St. Mary Church የኢስታንቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው። Official page of St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahdo Church in Istanbul, Turkey

የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 50  """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""ወአውፅኦሙ አፍአ እስከ ቢታንያ ወአንስአ እደዊሁ ወአንበረ ወባረከሙ ወ...
09/06/2021

የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 50
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

ወአውፅኦሙ አፍአ እስከ ቢታንያ ወአንስአ እደዊሁ ወአንበረ ወባረከሙ ወእንዘ ይባርኮሙ ተራሐቆሙ ወአርገ ሰማያተ።
እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም አረገ።
እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በአለ እርገት በሰላም በጤና በፍቅር አድርጎ አደረሳችሁ በአሉም የሰላም የጤና የበረከት በዓል ያድርግላችሁ አሜን ።

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ (ቅዱስ ያሬድ )ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአድባረ ሊባኖስ ግንቦት ...
09/05/2021

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ (ቅዱስ ያሬድ )
ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአድባረ ሊባኖስ ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት በዚያን ጊዜ ጠላታቸውን ለመሸሽ በስደት ላይ ስለ ነበሩ ምግብ አልያዙም ፤ ስንቃቸውን ንፍሮ እና ጥራጥሬ ነበር በዚህም ምክንያት የእመቤታችን ማርያምን የልደት በዓል በህዝበ ክርስቲያን ዘንድ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል ። የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ ታላቅ የደስታ ቀን ነው ።እንኳን ለእመቤታችን የልደቷ በዓል አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንላችሁ አሜን ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   ቡሩክ     ዘይመጽእ     በስመ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነውእንዲህም አላቸው ።በፊታችሁ ወዳለችው መንደር...
24/04/2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው
እንዲህም አላቸው ።በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ፈትታችሁ አምጡልኝ ።
ማንም አንዳች ቢላችሁ ።
ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፣
ወዲያውም ይሰዳቸዋል።
ለጽዮን ልጅ።እነሆ ፥ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ ።
ማቴ ፳፩ ፥፩
እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም በጤና በፍቅር አድርጎ አደረሰን አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም የበረከት የጤና ያድርግልን ። ሆሣዕና ማለት አሁን አድን ማለት ነው የዓለሙ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በምህረቱ ይማረን በአዳኝነቹ ያድነን አሜን።

ጥዋት አሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በዚሁ የሆሣዕና ሥነ ሥርዓት እናስተላልፋለን ጠብቁን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል  ማ ር ፲፮÷፲፮።እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ...
17/01/2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል ማ ር ፲፮÷፲፮።እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ።በደብራችን ቱርክ ኢስታቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 11 /5/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ድረስ በዓለ ጥምቀቱን ምክንያት በማድረግ የቅዳሴና የወንጌል የዝማሬ አገልግሎት ስላለ በሰአቱ ተገኝታችሁ የበዓሉን በረከት እንድትካፈሉ ስንል በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።የደብሩ አስተዳደር ሰባካ ጉባኤ ጽ/ ቤት ።

Address

Istanbul
34130

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢስታንቡል ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን - Mierafe Kidusan St. Mary Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share