መሰረተ ህይወት ሰንበት ት/ቤት

መሰረተ ህይወት ሰንበት ት/ቤት አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስኮ አዲስ ሰፈር ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሠረተ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

04/06/2024

አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስኮ አዲስ ሰፈር ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሠረተ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

አባቴ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ! የልቤን ሀዘን ስነግርህ ፈጥነህ ፀሎቴን ስማኝ ነገሬንም አድምጥ።ያዘኑትን የምታረጋጋ ሆይ !ወደ እኔ ቅረብበአጠገቤም ተገኝተህ አለሁልህ በለኝ።             ...
03/06/2024

አባቴ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ! የልቤን ሀዘን ስነግርህ ፈጥነህ ፀሎቴን ስማኝ ነገሬንም አድምጥ።
ያዘኑትን የምታረጋጋ ሆይ !ወደ እኔ ቅረብበአጠገቤም ተገኝተህ አለሁልህ በለኝ።
መልክአ ጊዮርጊስ

20/12/2023
13/10/2023

“ድንግል ሆይ! ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልኹሽ ምስጋናሽን ግን ለመፈፀም አልቻልኩም፡፡ እግዚአብሔርን ባመሰገንሁ ጊዜ ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ፤ በስምሽም ጸሎቴን በጸለይሁ ጊዜ ጸሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ ዳግመኛም ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ፣ ወደ ክብርሽ ገናንነት ወደብ እደርስ ዘንድ ደከምሁ፣ ያንዲቷን ማእበል ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም። ወደ ጽርሐ አርያም ጠፈር ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባሕር መሠረትስ መዋኘት ማን ይችላል? ድንግል ሆይ! ክብርሽን ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው?''

ቅዱስ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

  / የፅጌ ፆም የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳን...
11/10/2023

/ የፅጌ ፆም

የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ

ለጽጌ ጾም ካላቸው ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ጽጌ ጾም መቼ ነው የሚገባው እያሉ የሚጠይቁ ስላሉ ከወዲሁ ለማስታወስ ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡

በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው "መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና" ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡

ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ "አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ"፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡

እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት "ሰቆቃወ ድንግል" በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”

የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡

ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገ...
11/10/2023

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ที่อยู่

Sukhumvit Soi 3
Klong Toey
10110

เบอร์โทรศัพท์

+251939677114

เว็บไซต์

แจ้งเตือน

รับทราบข่าวสารและโปรโมชั่นของ መሰረተ ህይወት ሰንበት ት/ቤትผ่านทางอีเมล์ของคุณ เราจะเก็บข้อมูลของคุณเป็นความลับ คุณสามารถกดยกเลิกการติดตามได้ตลอดเวลา

ติดต่อ ธุรกิจของเรา

ส่งข้อความของคุณถึง መሰረተ ህይወት ሰንበት ት/ቤት:

แชร์

ประเภท