14/10/2020
ክፍል 8
ወይ ካፋ ሁሉ ሞልቶ ከሁሉም የሌለሽ!
ለምለም በጠፈጥሮ የታደለች ምድር በዩኔስኮ በአለም ቅርስነት የተመዘገበ የደን ባለበት ካፋ,ከተፈጥሮ ደን ውስጥ ያሉ ገፀ-በረከቶች ለምሳሌ ቡና የካፋ ማር ኮሮሪማ ጥምዝ እና የተለያዩ ለቁጥር የሚዳግቱ ለባህላዊ መድሃኒት የሚሆኑ እፅዋቶች ያሉባት ምድር ካፋ ,ማንኛውንም እህል ማብቀል የሚችል ለም መሬት ማዳበሪያ እንኳን የማይፈልግ መረት ያላት ምድር ካፋ,ማንኛውንም የቤት እንስሳት ለማርባት ምቹ እና ተስማሚ የሆነች ምድር ካፋ,ለምሳሌ የቦንጋን በግ ማንሳት ይቻላል አጠቃላይጠለሰው ልጆች ለኑሮ የሚስማማ አየር ያላት ምድር ካፋ ህዝቡ ያለውን አካፍሎ የሚበላ ደግ ህዝብ ሰው አክባሪ እንግዳ ተቀባይ ሩህሩህ ከደግነት ውጪ ምንም ክፋት የማያውቅ ኩሩ መለመን የማያውቅ ህዝብ ያላት ምድር ካፋ,ለመዝናኛ ምቹ የሆኑ ቦታወች ያሏት ለምሳሌ ባረታ ፋፋቴ የእግዜር ድልድይ የካፋ ደን በጥቂቱ ታይተው የማይጠገቡ እፅዋቶች መንፈስን የሚያድሱ ንፁ አየር ያለባት ምድር ካፋ ሁሉ ሞልተዋል ግን ሁሉ የላትም፡፡ታዲያ የእኔ ጥያቄ ይህ ሁሉ ሃብት ያላት ምድር ያ ሁሉ ደግ ህዝብ ያላት ምድር ነዋሪዎቿ ለምን ጎስቋላ ኑሮ እንዲገፉ ተፈረደባቸው?ለምንድነው ነዋሪዎቿ ታመው መታከም ሳይችሉ ጎጆአቸው ቁጭ ብለው ሞትን የሚጠብቁት?ለምንድነው በዝህ ዘመን ነዋሪዎቿ 7 ሰዓት እና 8 ሰዓት በእግር የሚጓዙት መኪና መንገድ ባለመኖር?በካፋ ምድር ላይ መኪና መንገድ ለመስራት የሚያስቸገር ቦታ አለ?ለምሳሌ ካፋ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች ክረምት ከበጋ የሚያገናኝ የሰለጠነ መንገድ አለ?ከአድሷ ወረዳ ሽሾ እንዴ ውጪ እሷም ሚዛን መስመር ላይ ስለሆነች አጋጣሚውን ተጠቅማ ነው፡፡በዝህ ጉዳይ የሚሞግተኝ ካለ ዝግጁ ነኝ፡፡ከጎረበት ሸካ ዞን ለመሄድ አንድ ሰዓት በላይ የማይወስድ ድሪማሻ መንገድ ባለመሰራቱ ሸካ ለመሄድ ቀን ሙሉ በመኪና መጓዝ ይጠበቅብሃል ምክንያቱ ወይ በሚዛን ቴፒ ዞረህ ነው ወይም በጅማ መቱ ጎሬ አድርገህ ስትዞር ታመሻለህ ድሪ ማሻ መንገድ ለመስራት ምንም አይነት መሰናክል የለም ላለመስራት ነው የሚያስቸግረው እንጂ ለመስራት ምንም አያስቸግርም ስንት ዓመት እንደፈጄ ሁሉም ሰው ያውቃል እስከመቼ ነው ህዝቡ መንገለታት ያለበት?የዞኑ ሃብት ወዴት እየሄዴ ነው?ለምሳሌ ውሽውሽ ሻይልማት ለህዝቡ ምንድነው የጠቀመው?ተቀጥሮ የሚሰራው የቀን ሰራተኛ ስንት ነው ገቢው?ስንት ብር እየተከፈለው ነው?ወይስ መሄጃ ስሌለው ጉልበቱ ይበዝበዝ?ለመሆኑ ሻይልማቱ ባለቤት ማነው?ለዙኑ ልማት የደገፈው ምንድነው?ነዋሪው የተከለውን ደን ጨፍጭፎ ሻይ እየተከለ ተተኪ ደን ይተክላል ወይ?ነዋሪው ስበሉ እያየ መኖር ነው ያለበት?ይሄ ህዝብ አያሳዝንም?ብዙ ሚሊዮን ብር ገቢ እያስገባ ገበረውን እያፈናቀለ ለገበረው የሰራው ጤና ጣቢያ የታለ?ለገበረ ልጆች የሰራው ትምህርት ቤት የታለ?እሺ ማነው ተጠያቅው?አይበቃም ወይ ይሄ ግፍ?ዙኑን የምትመሩ የመንግስ አካላት እስካሁን ስትመሩ የነበራቹ የመንግስት አካላት ይሄን ሂሳብ ታወራርዳለህ፡፡ብዙ ጠያቂ እየመጣብህ ነው አሁን ያለህ የመንግስት አካላት እንዝህን ጥያቄዎች መልስ ይፈልጋሉ ጥያቄዎቹ ልክ አይደሉም ካልክ የሚሞግቱህ ዝግጁ ናቸው ካልቻልክ ልቀቅ ሃላፊነት ሃብት ማካበቻ ሳይሆን ሃብት እንዲያክብቱ ለተፈቀደላቸው ሰዎች በፍትሃዊ መንገድ ማመቻቸት ነው ሃላፊነት ለህዝብ ማገልገል እንጂ ከህዝብ መገልገል አይደለም፡፡ሃላፊነት ለህዝብ የሚቆምበት እንጂ በተቃራኒ ከቆሙት ተመሳጥረህ ለግልህ የሚትገብርበት አይደለም ይሄ ጊዜ ይቆማል በሰራሄው ልክ ሂሳብ ታወራርዳለህ፡፡