12/09/2024
ከሞተ አንድ ሳምንት በኋላ ለባሏ ገዳዮች እንዲህ ስትል ጻፈች፡፡ ይቅር ብያችኋለሁ፡፡ ደግሞም እወዳችኋለሁ፡፡ ይህንን መልዕክት ያስተላለፈችው አኒታ ሰሚዝ ትባላለች፡፡ ሊቢያ ቤንጋዚ ውስጥ የ10 ዓመት የትዳር አጋሯን ለገደሉት የእስልምና አክራሪዎች ነው፡፡
ባሏ ሩኒ ሰሚዝ ይባላል፡፡ ከአሜሪካ ቴክሳስ በኬሜስትሪ መምህርነት እና በወንጌል አጋይነት ወደ ሊቢያ መጣ፡፡ ይህንን ውሳኔ እንዲወስን ያደረገው ጆን ፓይፐር የተባለ ሰባኪ የሰበከው ስብከት ነው፡፡ ስብከቱ ጥቅም ባለው ሞት ውስጥ ተልዕኮን መፈጸም /Doing mission when dying is gain/ የሚል ነው፡፡ ከዚህ ስብከት በኋላ ሚስቱን እና ጨቅላ ልጁን ይዞ ወደ ሊቢያ አቀና፡፡ ከመምህርነቱ ጎን ለጎን ወንጌል ስራው ነው፡፡
ሩኒ ሰሚዝ አጭር ጊዜ ነው በምድር የኖረው ነገር ግን በኖራት አጭር ዘመን እንዲሁም በሞቱም ጭምር ወንጌልን ሰብኮ ተሰውቷል፡፡ በቤንጋዚ የነበሩ ተማሪዎቹ ስለሱ ብዙ ይናገራሉ፡፡
ይቅር ብያችኋለሁ፡፡ ደግሞም እወዳችኋለሁ ፡፡ ከኢየሱስ የተማርኩት ይህንን ነው፡፡ ትላለች አኒታ ስሚዝ ለባሏ ገዳዮች፡፡
ጣቶቻቻሁን ውደዱ ሉቃ 6፡35