Lund Debre Mitmak Kidst Mariam Church

Lund Debre Mitmak Kidst Mariam Church ይህ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስዊ?

ይህ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስዊድን ሀገረ ስብከት የሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ልሳን ነው።
በዚህ ገጽ የቤተክርስቲያኗ የተለያዩ መንፈሳዊ መልዕክቶች፣ ዜናዎች፣ ትምህርቶች እንዲሁም በቤተ ክርስትያኗ የሚከናወኑ ስራዎችን እና የተለያዩ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን ለምዕመናን እናደርሳለን።

23/05/2022
19/04/2022

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች

ከዚህ ቀደም ብለን ሰሙነ ሕማማት/የሕማማት ሳምንት የሚዘከርበትን ሳምንት በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ደንብ መሰረት እንደምንዘክረው አስታውቀን ነበር። በዚህ መሰረትም እነሆ ትላንት ሰሙነ ሕማማትን አሐዱ ብለን ጀምረን በደብረ ምጥማቅ አጸደ ቤተክርስቲያናችን ሉንድ ውስጥ ከቀኑ ስምንት ሰዓት እስከ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ በሱ ፈቃድ ተሳክቶልን ተሰባስበን ስርዓቱን አድርሰናል። ይኸው ስርዓትም እነሆ ዛሪም በዚሁ ሰዓት እንደሚካሄድ እያስታወስን ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በካህን የሚመራ ስርዓተ ቤተክርስቲያን የሚቀጥል ይሆናል።

የፀሎተ ሐሙስ እለትም ንባብና ስግደት እንዳለ ሆኖ ሥርዓተ ሕፅበተ እግር ይከናወናል። ይህም ሥርዓት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ት ህትና ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበት እለት የሚታሰብበት ነው። ከዚያም ሥርዓተ ቅዳሴው ይከናወናል።ለትንሽ ደቂቃዎችም ትምሕርተ ወንጌል ይሰጣል። ስለ ጌታችን መድሐኒታችን ት ህትና ምሳሌነት ተገልጦ ይሰበክል።

የ እለተ አርቡን ፕሮግራም በተመለከተ ስግደቱና ሥርዓቱ በቅደም ተከተል እንደ ሕጉና እና መፅሐፉ እንደሚያዘው ይካሄዳል። ሰለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ስብከተ ወንጌል ይ ሰጣል። ንሴብሖ ተብሎ በጸሎት ይዘጋል። በዋናነት ግን ከሐሙስ አንስቶ ፕሮግራሙ በሙሉ የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ቅደም ተከተሉን በመከተል ይካሄዳል።

የጌታችን የመድሐኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በድምቀት እና በልዩ ዝግጅት ይክበራል። የኢየሱስ ክስቶስ ከሙታን መነሳት እና ሞት ድል መመታቱን ተብስሮልን የስርዓተ ቅዳሴው እንዳለቀ ወደ ተዘጋጀው ድግስ በመሄድ እብረንም እንድንገድፍ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኑልኝ ብላ ጋብዛችኋለች።

ቤ/ክችንን ፈጣሪ ይባርክልን!

የደብረ ምጥማቅ ሉንድ የቅድስት ማርያም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ !!!

18/04/2022

"ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘሰሙነ ሕማማት"
"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !
"ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬዋ ቀን በደስታና በሰላም ያድርሰን አሜን !
በስዊዲን ና ስካንድናቪያን ሀገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ስብከት
የደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያ ም ቤተ ክርስቲያን ከ 14 : 00 ስዓት እስከ 17 : 00 ስዓት ክፍት ነው።
ከጸሎት ሀሙስ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን በካህን የሚመራ ሙሉ አገልግሎት ( ስርዓት ቤተ ክርስቲያን ) ትሰጣለች ። ስዓቱን ና ፕሮግራሙን እናሳውቃለን !

ቤ/ክችንን ፈጣሪ ይባርክልን!!!

የደብረ ምጥማቅ ሉንድ የቅድስት ማርያም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ !!!

28/01/2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን !

የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም ወዳጆች የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታ ይድረሳችሁ

ነገ ቅዳሜ ፡ ጥር 21 የአስትሪዮ ማርያም በዓል ከጥዋቱ 7 ስዓት ጀምሮ በደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያም ይከበራል ሁላችሁም የበዓሉ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችኅል።

እሁድም መደበኛው ቅዳሴ አለ ።

ሆኖም ግን አሁንም በከባድ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለውን መጥፎ ወረርሽኝ በሽታ በጣም ስላስቸገረና ስላስፈራ ቤ/ክችን ማሳሰቢያ ማቅረብ ተገዳለች::
በሰው ልጅ አቅም ከፈጣሪ በረከትጋር ይኽንኑ ችግር ለመቋቋም እንድንችል ሁለት አበይት ነጥቦችን አስቀምጠናል::

1-የጉንፋን ምልክት በእኛም ሆነ በተለዬ በልጆቻችን ስንገነዘብ ለቤ/ክችን ደህንነት ሲባል ፀሎታችን ቤታችን ይሁን!!!

2- ለራሳችንም ሆነ ለሌላው ምዕመን: በተለይ ደግሞ ለእኛ ብለው አገልግሎቱን ለሚያደርጉልን የቤ/ክንዋ አባትና አገልጋዬች ደህንነት ሲባል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ(ጭንብል) ማድረግ ፍፁም ተፈላጊ ነው መንፈሳዊ ኃላፊነትም አለብን!!!

እንደተለመደው ላልሰሙት እንድታሰሙ አደራ እንላለን!!!
ቤ/ክችንን ፈጣሪ ይባርክልን!!!

የደብረ ምጥማቅ ሉንድ የቅድስት ማርያም ቤ/ክን ሰበካ ጉባኤ::

17/12/2021

በጣም ለተከበራችሁ የእመቤታችን የድንግል ማርያም ወዳጆች በመጀመሪያ የከበረ የልዑል እግዚአብሔር ሰላምታችን ይድረሳችሁ::

በየዜና ማሰራጫዎቹ እንደተገለፀው ከዚህ ቀደም ከተከሰተው ኮቪድ19 ሌላ ሌላም "ኦሚክሮን የተባለ የቫይረስ ዘር በመከሰቱ ምክንያት የስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ተሰብስቦ የጥንቃቄ ግዴታዎችን ወስኗል::
ይኸውም ለራሳችንም ሆነ ለሁላችንም የህይወት ደህንነት ሲባል ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው አስፈላጊውን ጥንቃቄዎች ማድረግ በጥብቅ ይገባናል!!!

ምንም እንኳን ብዙዎቻችን ክትባትም ብንወስድም በሽታው አይዘንም ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው!በተጨማሪም አስተላላፊዎች ስለሆን በቤ/ክችን ውስጥም ሆነ በአካባቢው በኮቪድ19 ሆነ በአዲሱ ቫይረስ ምክንያት አደጋ እንዳይከሰት ስለምንፈልግ!!!

1- የጉንፋን ስሜት ሲሰማን ወደ ቤ/ክን መምጣት ፍፁም አይኖርብንም::

2- ቤ/ክን ውስጥ ስንገባ
የአፍ-ጭንብል ማድረግ ግዴታችን መሆኑን ፈፅሞ መዘንጋት የለብንም!!!ይኽንንም የምናደግበት ምክንያቱ ግልፅ እንዲሆን ያስፈልጋል "እኔ ጤነኛ ነኝና አላጋባም ብለን እርግጠኛ መሆን የማይቻል ስለሆነና ለሁላችንም ደህነት ሲባል የአፍ ጭንብሉን የግድ እንድንጠቀም በጥብቅ እናሳስባለን!!!

ይኽንን ጥብቅ የማሳሰቢያ ለሌሎች ቤተሰቦች በሙሉ እንድታካፍሉልን በትህትና እናሳስባለን!!

አገራችንን ፈጣሪ ሰላም እንዲያደርግልን ወረርሽኙን እንዲያጠፋልን ፀሎታችንን ፈጣሪያችን አብዝቶ ይባርክልን🙏🏾🙏🏾🙏🏾

የደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት::

2014 ዓ/ም  የመስቀል ዳመራ በዓል በደብረ ምጥማቅ  ሉንድ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።የአመት ሰው ይበለን 🙏🙏🙏
26/09/2021

2014 ዓ/ም የመስቀል ዳመራ በዓል በደብረ ምጥማቅ ሉንድ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።የአመት ሰው ይበለን 🙏🙏🙏

Adress

Norra Promenaden, Norra Kyrkogården
Lund
SKÅNE

Telefon

+46790388226

Webbplats

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när Lund Debre Mitmak Kidst Mariam Church postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Heliga Platser

Skicka ett meddelande till Lund Debre Mitmak Kidst Mariam Church:

Dela