ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

  • Home
  • Qatar
  • Doha
  • ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው  " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " 💚💛❤️ አምላኬ ኳታር ቅድስት ሥላሴን ሳልጨርስ የትም አትውሰደኝ ::

10/09/2026

ውድ ቤተሠቦቼ እንኳን ለ2019 ዓመተ ምሕረት ለአዲሱ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን !!

ዘመኑ የሠላም የፍቅር የበረከት እንዲሆን እመኛለሁ መልካም በዓል ይሁንልን !!

እንዲህም ዓይነት ክብር አለ ለካ... 🥹🙏🏽የጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም፣ ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን "ልጃችን እንኳን ተወለድክ" ብለው እጅግ ባል...
22/08/2026

እንዲህም ዓይነት ክብር አለ ለካ... 🥹🙏🏽
የጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም፣ ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን "ልጃችን እንኳን ተወለድክ" ብለው እጅግ ባልጠበቅኩት መንገድ ልደቴን ሁለት ጊዜ አከበሩልኝ!
አንደኛ፦ በዕለተ ቀኑ ላይቭ ላይ ረጅም ሰዓት ብቆይባቸውም፣ እስክወጣ በትዕግስት ጠብቀው የማይረሳ ትዝታ እንዲኖረኝ አደረጉኝ።
ሁለተኛ፦ በደብሩ ተገኝቼ «ዛቲ ይእቲ ማርያም» ብለን የዕለቱን መዝሙር አንስተን፣ የእመ አምላክን ፍቅር እና እናትነትን ተምረን ስንወጣ... ፍጹም ባልጠበቅኩት ሁኔታ ዳስ ተጥሎ፣ ህጻናት እና ማዕከላውያን ሰንበት ተማሪዎች ከቅዱስ ያሬድ ማኅበርተኞች ጋር ተጣምረው፣ መዝሙር አዘጋጅተውና ኬክ አስደፍተው ስጦታ አዘጋጅተው ያልተጠበቀ ፈንጠዝያ ፈጠሩብኝ! 🎉🎂

ምን ማለት እንዳለብኝ ራሱ አላውቅም። እኔ ለራሴ አድርጌው የማላውቀውን ነገር በዚህ ልክ እና ክብር አድርገው ማክበራቸው በእጅጉ አስደንቆኛል። ምን እላለሁ... በእውነት ቃላት ያጥሩኛል!

ልዩ እና ከልብ የሆነ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፦
ለደብሩ አስተዳዳሪ ለመልአከ ፀሐይ የኔታ ኢሳኢያስ፦ የኔ ትሑት እና እጅግ የሚያሳሱ አባት ከነልጆቻቸው ክብር ያድልልኝ።

ለቄሰ ገበዝ ግሩም፦ የኔ ብርታት ሁሌም ፍቅርዎ አይለየኝ።
ለመልአከ ህይወት ነቅአጥበብ እና ለመልአከ ሰላም መሠረት።

ለምስኪኑ እና ቅኑ ወንድሜ ለመሪጌታ ዳንኤል ከነእህቱ።
ለዘማሪት ማኅሌት፣ ለቅዱስ ያሬድ ማኅበር ሞተር ለሆነችው ፍርዬ እና ለመምህር ቃልአብ እና ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ።
ለጽጌ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች።
እንዲሁም ዙሪያዬን ከባችሁ በደስታ እና በሳቅ ላደመቃችሁኝ ማኅበረ ምዕመናን በሙሉ... እግዚአብሔር ያክብርልኝ! 🙏🏽✨

እህቶቼ ኤሚዬ ፍርቲ እና ዊዊዬ ከነ ባለቤቶቻችሁ አትጠገቡም

✨  ፌስቡክ ትዝታዬን ቀሰቀሰብኝ! ✨እሼ፤ **ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም.** "ኳታር ሥላሴ መጥቼ አስቀድሳለሁ" ባለ ጊዜ፣ በአካል መጥቶ እስክናየው ድረስ በከፍተኛ ጉጉት ስንጠብቅ ነበር።...
19/08/2026

✨ ፌስቡክ ትዝታዬን ቀሰቀሰብኝ! ✨
እሼ፤ **ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም.** "ኳታር ሥላሴ መጥቼ አስቀድሳለሁ" ባለ ጊዜ፣ በአካል መጥቶ እስክናየው ድረስ በከፍተኛ ጉጉት ስንጠብቅ ነበር። 🥺🙏🏽

ቀኑ ሲደርስ ከወንድሞቹ ጋር በራሳቸው ወጪ መጥተው ከእኛ ጋር አብረው አስቀደሱ። ⛪️🤍 እሼ የዕለቱን መንፈሳዊ ውሎ እና ኳታር ቅድስት ሥላሴ ያለበትን ሁኔታ በሚደንቅ ሁኔታ በዶክመንተሪ መልክ ሠራው፤ 🎥 ከዚያ በኋላ የሆነው ነገር ግን እስከ ዛሬ ይደንቀኛል... ታሪክ ተቀየረ! 📖✨

የነገሩ ፍጻሜ የዘመናት ጥያቄ የተመለሰበት፣ የማይረሳና ደማቅ ታሪክ ተጻፈበት። 🏆🙌🏽
እሽዬ፤ ያደረግኸውን በጎ ነገር እግዚአብሔር በደማቁ መዝግቦልሃል! 📝 እኛ ብንረሳው እንኳን ፌስቡክ "ይሄን ጊዜ አትርሱት" እያለን ነው። 📱💙
እሽዬ እንዳንረሳው እግዚአብሔር ይርዳን!! 🙏🏽✝️

3 years later 🗓⏳👣

የመጨረሻ ቀን ፎቶዎች ክፍል ፩  በ"እናት አለን" ዓለም ዐቀፍ የቀጥታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሳምንት 750,000 ዩሮ እንደተሰበሰበ ተገለጠ! +++ዜና ሀገረ ስብከት+++በኢ/ኦ/ተ/ቤ የጀርመንና...
17/08/2026

የመጨረሻ ቀን ፎቶዎች ክፍል ፩
በ"እናት አለን" ዓለም ዐቀፍ የቀጥታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሳምንት 750,000 ዩሮ እንደተሰበሰበ ተገለጠ!
+++ዜና ሀገረ ስብከት+++
በኢ/ኦ/ተ/ቤ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከዶንኬ ቲዩብ ሚድያ ጋር በመተባበር ከሐምሌ ፳፱ እስከ ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም (5.-11.08.2026) ያከናወነው ዓለም ዐቀፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሳምንት መጠናቀቁ ተገለጠ። "እናት አለን" በሚል መሪ ቃል ሲከናወን የሰነበተው ዓለም ዐቀፍ የቀጥታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሳምንት ዓላማው ሀገረ ስብከቱ በጀርመን ሊመሠርተው ላቀደው የጽሙና፣ የአስተዳደር፣ የትምህርት፣ ሥልጠናና ምርምር ተቋም (ገዳም) ሕንጻ መግዣ ገንዘብ መሰብሰብ ነው።

በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ ተከፍቶ በኮሜድያን እሸቱ መለሰ መሪነት በዶንኪ ቲዩብ አማካኝነት በተደረገው ገንዘብ ማሰባሰቢያ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን መልአከ መዊዕ ልሳነ ወርቅ ውቤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና ገንዘብ የማሰባሰቡ ሳምንት የተካኼደበት የፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም አጥቢያ አስተዳዳሪ ገልጸዋል። ሥራ አስኪያጁ አክለውም "ከተሰበሰበው ገንዘብ በተጨማሪም በሀገረ ስብከታችን ብሎም በመላው ዓለም ያሉ ማኅበረ ካህናትንና ምእመናንን ለአንድ ዓላማ ያስተባበረና ያስተሳሰረ ውጤታማ ሳምንት ነበር" ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት የሚያስተባብረው ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሊ/ኅ ዶ/ር መርሻ አለኸኝ እንደገለጡት "ጉባኤው እስከተጠናቀቀበት ዕለትና ሰዐት ድረስ በአጠቃላይ 750,000 ዩሮ ለመሰብሰብ ተችሏል። ይህም ከታቀደው አንጻር ጥሩ የሚባል ወጤት ነው። ይህ ገንዘብ ቀድሞ በዐቢይ ኮሚቴው ከተሰበሰበው ገንዘብ ጋር ተጨምሮ የተገኘውን ሕንጻ ለመግዛት የመጨረሻ ድርድር አከናውነን ቦታውን የምንረከብበት ዐቅም የፈጠረልን ነው" ብለዋል። ይሁንና የምንገዛው ሕንጻ ምንም እንኳን ሰፊና የምናስባቸውን ማእከላት በጥሩ ሁኔታ ማቋቋም የምንችልበት ቢኾንም ከዕድሜው አንጻር ወጪ የሚጠይቅ ዕድሳት ይፈልጋል። በመኾኑም ገዳሙን ከተረከብን በኋላም የምእመናን ንቁ ሱታፍ እንዳይለየን አደራ" ብለዋል።
[ዜና ሀገረ ስብከት ሚድያ ፥ ነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም ፥ ፍራንክፈርት ጀርመን]
ፎቶ ሚኪ ከፍራንክፈርት
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

15/08/2026

አይ የልዑል እግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው ይህን ምስክርነት እና ምስጋና ስሙ!!

13/08/2026

🔥 ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን ::
ተሳክቷል ከ750,000 ሺ ዩሮ በላይ ተሰብስቧል ይህ ስኬት ኦርቶዶክሳውያን በአንድ መድረክ የታዩበት በአንድ ሳምንት ውስጥ በአውሮፓ የመጀመሪያውን ገዳም የገደሙበት የተሰራብንን ሴራ ደግሞ ያከሸፍንበት ነው እንኳን ደስ አላችሁ ::

12/08/2026

😴 ኑ ዶንኪ ቲዩብ ላይ የመጨረሻ ስጦታችሁን ስጡን እኛም እንረፍ ::

12/08/2026

ቀዳሚዬ እንኳን ደስ አለህ !!

12/08/2026

ከባድ ድካም አሌክስዬ በርታ ጨርሰናል

12/08/2026

🙏 የቀረን ጥቂት ነው ኑ ተረባርበን አዲስ ደማቅ ታሪክ እንጻፍ !!

Address

Doha
90945

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ ":

Shortcuts

Share